ፈልግ

የኩኖአ ፕሮጀክት ተሳታፊዎች ስለ አመጋገብ እና የምግብ አሰራር ማሳያ በኋላ ወደ ቤት የሚወስዱት የምግብ አዘገጃጀት ቡክሌት እና የኩኖአ ቦርሳ ይዘው የኩኖአ ፕሮጀክት ተሳታፊዎች ስለ አመጋገብ እና የምግብ አሰራር ማሳያ በኋላ ወደ ቤት የሚወስዱት የምግብ አዘገጃጀት ቡክሌት እና የኩኖአ ቦርሳ ይዘው  (Foto Credit Catherine McWilliams)

‘ምግብ መድኃኒትህ ይሁን’፡ የኲኖአ ፕሮጀክት ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ያበረታታል።

በኒውዮርክ ሎንግ ደሴት ላይ የሚኖሩ ስደተኞች ርሃብን ለማሸነፍ የሚያደርጉት ትግል ፥ ሲስተር ማሪያ ጄስን ‘ኩኖአ ወሳኝ ምግብ ነው’ (Quinoa is Super Food) የተባለ የአመጋገብ ዘይቤ ላይ የሚሠራ ሰብአዊ ድርጅት እንዲመሰርቱ አነሳስቷቸዋል።

አዘጋጅ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ
የ ‘ጥበብ ሴት ልጆች ማህበር’ አባል የሆኑት ሲስተር ማሪያ ጄሱስ ፒኒዶ አጉይላር ፥ ኩኖአን (የስደተኞቹ ባህላዊ ምግብ) በማዘጋጀ የሚገኘውን ደስታን እና የዚህን ጥንታዊ ምርጥ ምግብ አስደናቂ የስነ-ምግብ ጥቅማ ጥቅሞች ኒው ዮርክ ከሚገኘው በሃንቲንግተን ጣቢያ ፥ የስደተኛ ክርስትያን ማህበረሰብ በብዛት የሚገኙበት ሴንት ሂዩ የሊንከን ደብር ከስደተኞቹ ጋር ሲካፈሉ ቆይተዋል።
በሎንግ ደሴት ውስጥ የሚኖሩት ስደተኞች የድህነት ኑሮን እየታገሉ የሚኖሩ ቤተሰቦች ሲሆኑ ፥ በወረርሽኙ እና የዋጋ ንረቱ ባስከተለው የኢኮኖሚ መዛባት ምክንያት ደግሞ ችግራቸው ከቀን ወደ ቀን ተባብሷል። ለዚህ ሲስተር ማሪያ ያቋቋሙት የተራድኦ ድርጅት ድጋፍ ምስጋና ይግባውና እነዚህን ቤተሰቦች ‘ኩኖአ ምርጥ ምግብ ነው’ (Quinoa is Super Food) በሚል መጠሪያ የተቋቋመው ድርጅት ጠቃሚ የሆነ የአመጋገብ ዘይቤ እንዲኖራቸው ፕሮጀክቱ እየረዳቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል ነ። የፕሮቲን ፣ የማእድናት ፣ የቪታሚኖች እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች ምንጭ የሆነው ኩኖአ ለብዙ የጤና ጥቅሞቹ ተወዳጅነትን እያገኘ መጥቷል።
ከፕሮጀክቱ ጀርባ ያለው መነሳሳት
ሲስተር ማሪያ ፕሮጀክቱን ለማቋቋም ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰቡት ፥ የቁምስናውን ስደተኛ ክርስቲያን ማህበረሰብ ሲያገለግሉ ነበር። በዚያን ወቅት ስደተኞቹ ከሥራ ቦታዎቻቸው ረጅም ሰዓት በመስራት ደክመው ወደ ቤት ከመጡ በኋላ ለቤተሰቦቻቸው ጤናማ ምግብ ለማቅረብ ሲሉ ስለሚያደርጉት ተጋድሎ ይነግሯቸው ነበር።
በፕሮጄክቱ ፕሮፖዛል ላይ “ከስደተኞች ጋር ባደረግኩት ውይይት ተስፋቸውን ፣ ጭንቀታቸውን እና መከራቸውን ተረድቻለሁ” በማለት ጽፈዋል። ሲስተር ማሪያ ከማህበረሰቡ ውስጥ አንዷ የሆነችውን ስደተኛ ምእመን “ከሥራ ሰዓት በኋላ ደክሞኝ ወደ ቤት እመለሳለሁ ፥ ብቻ ማረፍ ፣ መተኛት እፈልጋለሁ ፥ ግን ደግሞ ርቦኛል ፥ ሻወር ከወሰድኩ በኋላ አነስተኛ ዋጋ ያለው ምግብ ለመግዛት እወጣለሁ ፥ ነገር ግን በአነስተኛ ዋጋ የምገዛው ምግብ በቂ አልሚ ንጥረ ነገር ስለሌለው እጨነቃለሁ” ብላ ያለቺዉን በመጥቀስ ስደተኞቹ ያለባቸውን ችግር አብራርተዋል። ሲስተር ማሪያ ይህንን ችግር ለመፍታት እና የስደተኛው ማህበረሰብ ጤናማ ምግቦችን እንዲመገብ መርዳት እንዳለባቸውም ተገነዘቡ ።
ለብዙ ዓመታት አብረዋቸው ሲያገለግሉ ከነበሩት የ ‘ጥበብ ሴት ልጆች ማህበር’ እህቶች መሃከል ከማሪሊን ሶይደር ፣ በርናዴት ሳሶኔ እና ቴሬዛ ዴ ጄሱስ አጊላር አቪላ ጋር እ.አ.አ. በ2015 የጀመረው እና ዓላማው ሰብአዊ እና መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ለስደተኛው ክርስቲያን ማህበረሰብ ማቅረብ የሆነው የማህበረሰቡ ስነ ባህል ትሥሥር ጉባኤ አካል በመሆን የስደተኛ ማህበረሰቡን በቤተክርስቲያን ውስጥ በታማኝነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
ከፕሮጀክቱ በስተጀርባ ያለው ማህበረሰብ
ሲስተር ማሪያ የስደተኛው ማህበረሰብ ዘንድ ያለውን የአመጋገብ ችግር ለመፍታት እንዴት መርዳት እንደሚችሉ አሰላሰሉና አምላክም እንዲረዳቸው ተግተው ጸሎት ሲያደርጉ ነበር። በመቀጠልም ይህንን የኩኖአ የስነ ምግብ ፕሮጀክታቸውን ሃሳብ የደገፉትን የቁምስናው ካህን የሆኑትን አባ ሮበርት ስሚዝን አነጋግረዋል።
የ ‘ጥበብ ሴት ልጆች ማህበር’ አመራር ቡድንን ኩኖአን በመግዛት ማገዝ ይችሉ እንደሆን እና የምግብ አዘገጃጀት ቡክሌቶችን ለቤተሰቦች ለማሰራጨት የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ይችሉ እንደሆነ ጠይቀዋቸዋል ፥ የአመራር አባላቱም ለፕሮጀክቱ ድጋፍ እንደሚያደርጉ በማሳወቅ እና ማረጋገጫ በመስጠት ምላሽ ሰጥተዋቸዋል። ከዚያም ሲስተር ማሪያ የኩኖአ ቦርሳዎችን በቅናሽ ዋጋ ለማቅረብ የተስማማ አንድ አከፋፋይ አገኙ።
በጎ አድራጊዎች ፕሮጀክቱን ይደግፋሉ
ለበጎ አድራጊዎች እገዛ ምስጋና ይግባውና ፕሮጀክቱ ውጤታማ እንዲሆን ተችሏል። እንደ ግሪጎሳዊያኑ አቆጣጠር ከግንቦት 2021 ጀምሮ ሲስተር ማሪያ የስደተኛውን ማህበረሰብ አባላት ስለ ኩኖአ የጤና ጥቅሞች ማብራሪያ እንዲሰጡ ጋብዘዋቸዋል። እሳቸውም ከኩኖአ ጋር የተዘጋጁ ምግቦችን እና ጤናማ የፍራፍሬ መጠጦችን ከስደተኛው ማህበረሰብ ጋር ተጋርተዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለሴቶች እና ወንዶች ቡድን እንዲሁም ለቁምስናው ወጣቶች ቡድን ስለ ፕሮጄክቱ ገለጻ በማድረግ ፕሮግራሙ በታላቅ ስኬት ቀጥሏል። ጸሎት የዝግጅቱ አስፈላጊ አካል ሲሆን ፥ ሲስተር ማሪያ ደግሞ “ሕይወት አምላክ በፍቅር የሚሰጠን ልዩ ስጦታ ነው” ሲሉ አበክረው ይናገራሉ።
ሲስተሯ “ምግብህ መድኃኒትህ ይሁን” የሚለውን የስነ መድኃኒት አባት የሆነውን የሂፖክራተስን አባባል በመጥቀስም ይናገራሉ።
የፕሮጀክቱ ትምህርታዊ ክፍል
ሲስተር ማሪያ በፖታስየም ፣ ማግኒዥየም ፣ ፕሮቲን ፣ ጠቃሚ ቅባቶች፣ ፋይበር ፣ በቫይታሚን ኤ ፣ ሲ እና ዲ የበለጸጉ ምግቦችን የመመገብን አስፈላጊነት በተመለከተ ለአንድ የስፓኒሽ ተናጋሪ ወጣት ጎልማሶች ቡድን ሲናገሩ “ሰውነታችን የተዋጣለት ማሽን ነው ፥ ለልብ ጤንነት የተመጣጠነ እና የተለያዩ ቀለማት ያላቸውን አትክልቶች ፣ ፍራፍሬ ፣ ባቄላ እና ጥራጥሬዎችን እንዲሁም ኩኖአን መመገብ ጠቃሚ እንደሆነ አብራርተዋል። በማከልም “ኩኖአ ለጤና ጠቃሚ የሆኑ ብዙ ንጥረ ነገሮች እንዳሉት በመግለፅ በጣም አስደናቂ የሆነ እጅግ በጣም ጥሩ ምግብ ነው” ሲሉ ለወጣቶቹ ነግረዋቸዋል።
የወጣቶቹ ቡድን መሪ የሆነው ጁሊዮ ቬላስኩዝ እንደሚናገረው የሲስተር ማሪያን ስለ ኩኖአ የሚያቀርቡት ትምህርታዊ ፕሮግራም ወደ ቁምስናው አዘውትረው የሚመጡትን የሂስፓኒክ ስደተኛ ቤተሰቦች በመርዳት ላይ ትልቅ ለውጥ እያመጣ ነው ብሏል። አሁን ላይም የተሻሉ የምግብ ምርጫዎችን በማድረግ ጤናማ ህይወት እየመሩ ይገኛሉ።
በማከልም “ይህ ድርጅት ቤተሰቦቻችን ጤናማ እንዲሆኑ እየረዳቸው ነው ፥ ቤተሰቦቻችንን ምን መመገብ እንዳለብን የተሻለ ምርጫ እንዲያደርጉ ረድቷቸዋል” ተናግሯል።
“ሲስተር ማሪያ ስለ ስነ ምግብ እና አመጋገብ ዘይቤ ስለሚያስተምሩን እጅግ አርጌ ከልቤ አመሰግናቸዋለው ፥ ምግቡም ግሩም ነበር” ስትል በዝግጅቱ ላይ የተሳተፈችው ፓትሪሻ አልካንታራ ተናግራለች። “ዛሬ ምግብ እንዴት መድኃኒት ሊሆን እንደሚችል እና ስለ ምግብ ከዚህ በፊት የማላውቃቸውን ብዙ ነገሮች ተምሬያለሁ” በማለትም አክላለች።
ስለ ሲስተር ማሪያ
በፔሩ ያደጉት ሲስተር ማሪያ እናታቸው ምርጡ ኩኖአን በሾርባ ፣ ሰላጣ እና ጣፋጭ ምግቦችን ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለጓደኞቻቸው እና ለተቸገሩ ጎረቤቶች ሲያዘጋጁ እያዩ ነው ያደጉት።
ሲስተር ማሪያ ስለ እናታቸው ሲያስታዉሱ “እናቴ የተወለደችው እና ያደገችው ኩኖአ በሚበቅልበት በአንዲስ ክልል ነው ፥ ኩኖአ አሪፍ ምግብ እንደሆነ ታውቅ ነበር ፥ በጸሎቴ እናቴን አስባለሁ እንዲሁም በየቀኑ ምግብ በደስታ እና በመስዋዕትነት እንዴት እንደምታዘጋጅ አስታውሳለው ፥ እነሱን እንዴት እንደ ስነ ምግብነት ይዘታቸው እንደምታዋህዳቸው ታውቃለች ፥ እናም ጣፋጭ ነበሩ” በማለት አክለውም “እናቴ በትጋት ትሰራ ነበር ፤ ብዙ ድሆችንም ትረዳ ነበር” በማለት ሃሳባቸውን ደምድመዋል ሲስተር ማሪያ ጄስ ።
 

08 June 2023, 13:55