ፈልግ

2021.07.29 Santa Marta

ጌታ ሆይ ይህች እህቴ ሥራውን ሁሉ ለእኔ ትታ ብቻዬን ስደክም እያየህ ዝም ትላለህ?

ማርታ እየሱስ ወደ ቤቷ ስለመጣ የሚበላ ምግብ ልታዘጋጅለት ትጣደፍ ነበር። እርስዋ ስትንጐዳጐድ እህቷ ግን እርሷን ከማገዝ ይልቅ በእግሩ ሥር ተቀመጣ የእየሱስን ንግግር ትሰማ ነበር። ማርታ ይህ ሁኔታ በጣም ስላሳዘናት «ይህች እህቴ ሥራውን ሁሉ ለእኔ ትታ ብቻዬን ስደክም እያየህ ዝም ትላለህ? እባክህን እንድታግዘኝ ንገራት» አለችው (ሉቃ. 10፣ 38 – 41)።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ኢየሱስ እርስዋ እንደጠበቀችውና እንዳሰበችው እህትዋን በመገሰጽ ሂጅና ከእርስዋ ጋር ሥሪ ከማለት ይልቅ እርስዋ አላፊውን ነገር በማሰብዋ ገሰጻት፣ የማርያምን መንፈሳዊነት በማመስገን ተከላከላት። ማርያም እህትዋ ብቸዋን ሰትሠራ ዝም ያለቻት ታክታ ሳይሆን የእየሱስ ትምህርት ስለሳባት ነው። እህቷ ከምታዘጋጅም ምግብ ይልቅ የጌታ ኢየሱስ ክርሰቶስ ትምህርት የሚበልጥ ሆኖ ስለታያት ነው። ደግመ ሥራዋ የኢየሱስን ድጋፍ ስላገኘ የበለጠ መሆኑን ይገልጣል። እኛስ ስንት ጊዜ ባልንጀራችንን «ጌታ ሆይ ባልንጀራዬ ስሠራ ብቻዬን ሲተወኝ እያየህ ዝም ትላለህን? እኔ ይህን ሁሉ ስደክምና ስለፋ ትንሽ አታስብልኝምን? እንዲረዳኝ ለምን አትነግረውም?» እያልን እንዲቆጣ እናደርገዋለን። ማርያም ክፉ ወይም ቸልተኛ አይደለችም፤ አህትዋ ብቻዋን ስትሰራ የተወቻት የተሻለ ሥራ ይዛ ስለነበረ ነው።

በኢየሱስና በንግግሩ ስለተሳበች ነው። አኛ ግን በልንጀራችንን በቸልተኛነት፣ በሃኬት፣ በክፋት ብቻውን እንዲሠራ እንተዋለን። ሥራ ከብዶት እያየን «ምንቸገረኝ በማለት በማን አለብኝነት» በመጥፎ መንፈስ ብቻውን ሲታገል ሲለፋና ሲደክም ከመርዳቱ ይልቅ ዝም ብለን እንመለከተዋለን። እርሱ ብቻውን የሚሠራው ሥራ የሁላችንም በመሆኑ እንዘነጋለን። ተጋግዘን ማድረግ የሚገባን ነው። አብዛኛዎቹ አፈ ጮሌዎች እየሳቁና እየተሽለኰለኩ ሁሉን ከሚመለከት ሥራ ያመልጣሉ፤ በሕሊና የሚሠሩትን ጥቂቆች ዝም ብለው ይመለከቷቸዋል። በገበታ ቤት ግን ሁሉ ጐበዝ ሠራተኛ ነው፤ የሚሠራ እንጂ ተመልካች የለም። መስቀል ሁሉ በጥቂቶች የእግዚአብሔር ፍራቻ ባላቸው ላይ ይጫናል።

ሌሎች የሚበልጡ ተንኰለኞችና የእግዚአብሔር ፍራቻ የሌላቸው እንደ ምንም ብለው ያለና የሌለውን ምክንያት በመፍጠር በአፈ ጮሌነትና በመሹለክለክ ሲያመልጡ ሥራ ሁሉ በጥቂቶች ላይ ይጭኑበታል። አቤት ጭካኔ! አቤት ተንኰል። ጠንክሮ የሚሠራ ሰው ቢያጋጥመው አንድ ልግማመኛና በሃኬት የሚሠራ ይጐዳዋል። ያን ጊዜ «ጌታ ሆይ! እንዴት ያለ ክፉ ባልንጀራ ገጠመኝ? ምን ዓይነት ዕድል ነው? እንዴት ያለ መዓት ወረደብኝ? ከእኔ የማይርቅ በማለት ቁጣ ይመጣል። ባልንጀራችን ሲሠራ ሲያሳምር እኛ ስናበላሽ እርሱ ሲታገል እኛ ተመልካቾች ብቻ ሆነን ሳንረባረብ ስንቀር ትጉህ ሠራተኛው ባልንጀራችን ያለመጠን ይሰቃያል፤ በብርቱ ፈተና ይወድቃል። «በራሳችን ላይ ሊደረግ የማንፈልገው በሌሎች አናደርጋለን»።

ይኸውም ለራስህ እንዲደረግ የማትፈልገውን ነገር ለሌላ አታድርግ የሚለውን አባባል ይቃወማል። እና ብቻችንን ስንታገል በአጠገባችን ቆመው ዝም ብለው እንዲመለከቱን የማንፈልግ ከሆነ እኛም በተመሳሳይ ለሌሎች እንዲሁ እናድርግላቸው። ሌሎች እንዲጐዱን የማንፈልግ ከሆነ እኛም እንጉዳቸው በክፋታችንና በሃኬታችን በቸልተኛነታችን ባለንጀራችን እንዳይጐዳና እንዲያጉረመርምብን አናድርግ፣ በሥራ እንርዳው፣ በችግር፣ በፈተናና በስቃይ ጊዜ አጠገቡ ሆነን እንራራለት። ባልንጀራችን የሥራ ጓደኛችን የማኀበራችን አባል በእኛ እንዲደሰት እንጂ እንዲያዝን አናድርግ።

 

 

22 May 2023, 11:47