ፈልግ

GREECE-TRANSPORT-RAIL-ACCIDENT

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግሪክ በተከሰተው የባቡር አደጋ በተጎዱ ሰዎች ማዘናቸውን ገለጹ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየካቲት 26/2015 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ካጠናቀቁ በኋላ ለታዳሚዎች ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት በቅርቡ በግሪክ በተከሰተው የባቡር አደጋ በተጎዱ ሰዎች ማዘናቸው ይገለጹ ሲሆን ለተጎጂዎች እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተው ጸሎት ማድረጋቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

“የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እሕቶቼ፣ ሃሳቤ ባለፉት ቀናት በግሪክ በደረሰው የባቡር አደጋ ሰለባ በሆኑት ሰዎች ላይ ነው። ብዙዎቹ ወጣት ተማሪዎች ነበሩ። ለሟቾች እየጸለይኩ ነው። እኔ ከቆሰሉት እና ከዘመዶቻቸው ጎን ነኝ። እመቤታችን ታጽናናቸው” ስሉ መልእክታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው በመቀጠልም “አሁን በክሮቶን አቅራቢያ በሚገኘው በኩትሮ ውሃ ውስጥ ለተፈጠረው አሳዛኝ ሁኔታ ሀዘኔን እገልጻለሁ። በመርከብ መሰበር አደጋ ለተጎዱት፣ ለዘመዶቻቸው እና ለተረፉት ሰዎች እጸልያለሁ። ለእነዚህ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን መልካም ትብብር ላደረጉላቸው  እና መስተንግዶ ለአካባቢው ህዝብ እና ተቋማት ያለኝን አድናቆት እና ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ተመሳሳይ አሳዛኝ ሁኔታዎች እንዳይደገሙ ለሁሉም ሰዎች የማቀርበውን አቤቱታዬን አድሳለሁ። የብዙ ንፁሃን ዜጎችን ህይወት እያጠፉ እንዳይቀጥል ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተግባር ይቁም! የተስፋ ጉዞዎች ወደ ሞት ጉዞዎች አይለወጡ። እንደዚህ ባሉ አሰቃቂ አደጋዎች የሜዲትራኒያን ንፁህ ውሃ ከእንግዲህ አይድማ! ጌታ የመረዳት እና በእዚህ ጉዳይ የማልቀስ ጥንካሬን ይስጠን” ብለዋል።

በመጨረሻም ቅዱስነታቸው ለሁላችሁም መልካም እለተ ሰንበት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፣ እባካችሁ ለእኔ መጸለይን እንዳትዘነጉ፣ ብለው ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ከሰጡ በኋላ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

05 March 2023, 11:20