ፈልግ

በስደተኞች ላይ ከደረሰው የመርከብ አደጋ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመስቀል መንገድ ጸሎት ላይ ተሳትፈዋል

በደቡብ ጣሊያን ፥ የስደተኞች አደጋ በተከሰተበት ቦታ አምስት ሺህ ያህል ሰዎች በመስቀል መንገድ ጸሎት ላይ ተሳትፈዋል። ሥነ ሥርዓቱን የመሩት ሊቀ ጳጳስ የእንኳን ደህና መጣችሁ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ሥነ ስርአቱ ሁሉንም የአውሮፓ ሃገራት ያሳተፈ ነበር። እንደሚታወቀው እስካሁን ድረስ 70 አስከሬኖች ተገኝተዋል፤ ቢያንስ 27 እና ከዛ በላይ እስካሁን ያልተገኙ ሲሆን ከአደጋው 80 ሰዎች ተርፈዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ - አዲስ አበባ

ትንሽ ግራጫ ሹራብ በስቴቻቶ ዲ ኩትሮ የባህር ዳርቻ ላይ ትገኛለች ፣ በከፊል በአሸዋ ተሸፍኗል ፣ አንድ ሰው ከጎኑ ትንሽ ሻማ ፣ አበባና መስቀል ያለው መሠዊያ ሠርቷል። የካቲት 19 እሁድ ቀን ረፋድ ላይ በአዮኒያ ባህር ውሃ ላይ የሞቱትን ስደተኞችን ለማስታወስ በክሮንቴ ሳንታ ሰቨሪና ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከተዘጋጁት 14 የመስቀል መንገድ ማረፍያዎች መካከል አንዱ የሆነውን አሳዛኝ ማስታወሻ ያሳያል። ከቱርኳ የባህር ሰርጥ የተነሳው መርከብ በባህሩ ሞገድ ከተመታ በኋላ ፥ መርከቧ ወደ ቁርጥራጮች ከመቀየሯ በፊት ፥ ወንዶች፣ ሴቶች እና ሕፃናት ወደ ውሃ ውስጥ ተወርዉረው አስከፊ የተባለው አደጋ መድረሱ ይታወቃል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሑድ የካቲት 26/2015 ዓ. ም.  በጣሊያን ደቡባዊ ካላብሪያ ክልል የባሕር ዳርቻ ላይ አደጋው ሲደርስ በጣም ማዘናቸዉን እንደገለፁ ሁሉ ፥ ከሳምንት በኋላም “ሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ከሥራቸው ሊገቱ ይገባል ፣ እናም የብዙ ንጹሐን ዜጎችን ሕይወት እየቀጠፉ መቀጠል የለባቸውም!” ብለው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በአብዛኛው የአፍጋኒስታውያንና የፓኪታዊያን የሆነው 71 የስደተኞች አስከሬን ፥በሞገዱ ሃይለኛነት የተነሳ የአብዛኛው ራቁታቸውን ነበር ፥  ከባህር ዳርቻው ላይ በተሰበሰበበት ቦታ፥ የክሮቶን እና አካባቢው ህዝብ እጅግ በጣም ግዙፍ የሆነ የእንጨት መስቀል ይዘው በሰልፍ ይራመዳሉ። መስቀሉም አደጋው ከደረሰ ከሰአታት በኋላ በአካባቢው በሚገኝ አናጺ የተሰራ ሲሆን ፥ ከተሰራም በኋላ  በሌ ካስቴላ ደብር ውስጥ እንዲቆይ ተደርጓል። የቁምስናው ቄስ የሆኑት አባ ዶን ፍራንቸስኮ ሎፕሬት እንደተናገሩት የኢየሱስን መስቀል እንደሚያስታውሳቸው እና ‘ይህ ሻካራና ቀዝቃዛ እንጨት የብዙ ንጹሐን ሰዎችን ፣ ምንም ባልሠሩት ኃጢአት የሞቱትን የወንድሞቻችንንና የእህቶቻችንን ሕልም ተምሳሌት ያሳየናል።  ቀናት እያለፉ በሄዱ ቁጥር ባሕሩ ሁሉንም ነገር እየወሰደ ይሄዳል።’ ብለዋል።

“አደገኛው ነገር ይህንን በጥልቅ የነካንን አሳዛኝ ክስተት ከአእምሮአችን ማጥፋት አለመቻሉ ነው ዪላሉ ቄስ ዶን።

መስቀል
መስቀል

ምእመናንና ከንቲባዎች መስቀሉን ተሸክመዋል

በዚህ በተደረገው ሥነ ስርዓትም ፥ ከቦትሪሴሎ ፣ ሮካ በርናርዳ ፣ ቤልካስትሮ ፣ ለ ካስቴላ ፣ ኢሶላ ካፖ ሪዙቶ ፣ ሳን ሊዮናርዶ እና ሁሉም አጎራባች ማዘጋጃ ቤቶች ምእመናን ተራ በተራ መስቀሉን በትከሻቸው ተቸክመዋል። ምክንያቱም የአንዳንድ ስደተኞች አስከሬን ከጥቂት ጊዜያት በፊት የእነዚህን አንዳንድ መንደሮች የባህር ዳርቻዎች በደም አጥቧልና። ከንቲባዎቹም ሳይቀሩ በዚህ የስቅለት መንገድ መስቀሉን በትክሻቸው ተሸክመዋል።

 ሊቀ ጳጳሱ እና ኢማሙ

ከከንቲባዎቹ ቀጥሎ በመስቀሉ የእንጨት እጅጌ ጥላ ሥር ፥ሊቀ ጳጳስ አንጀሎ ራፋኤል ፓንዜታ እና በኩትሮ የሚገኘው መስጂድ ኢማም ሙስጠፋ አቺክ ጎን ለጎን እየተጓዙ ለተጎጂዎች ነፍስ አብረው ጸልየዋል።፣ ከተጊጂዎችም መካከል አብዛኞቹ የሙስሊም እምነት ተከታዮች ነበሩ።  ኤጲስ ቆጶስ አንጀሎ በጸሎታቸው ወቅት እጆቻቸውን አንድ ላይ አያይዘው ነበር ፤ ኢማሙም ከ14 ዓመቷ ሴት ልጃቸው ማላክ ጎን ሙስሊሞች በቀን አምስቴ ሲሰግዱ የሚሰግዱበትን ምንጣፍ እንደያዙ አብረው ይጓዛሉ።

በ 66 ቱ አስከሬን ፊት ለፊት ሁለቱ አንድ ላይ ተንበርክከው ሲጸሊዩ ሲታይ ልዩ ስሜት ይፈጥራል። ኤጲስ ቆጶስ ፓንዜታ ወደ ባህር ዳርቻው እንደደረሱ ፥ መስቀሉን ስመው ፥ በቦታው የተገኙትንም ሁሉ ከባረኩበት በኋላ ፤ በመስቀል መንገዱ የጸሎት ሥነ ስርአት ከሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር ለተጎጂዎች አብረን በአንድነት ወደ አምላካችን እንጸልያለን ብለዋል።

አቡነ ፓንዜታ እና ኢማም ሙስጠፋ አቺክ
አቡነ ፓንዜታ እና ኢማም ሙስጠፋ አቺክ

ጥልቅ ስሜት ያለው ተሳትፎ

ተሳትፎው በጣም ትልቅ እና ያልተጠበቀ ነበር። የስደተኞች ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው በሺዎች የሚቆጠሩ በዝምታ የተዋጡ ዜጎች መገኘት ግዴታቸው እንደሆነ ተሰምቷቸዋል። ከባለቤቷ ጋር በመሆን ለተጎጂዎች ሃዘኗን ለመግለጽ የመጣች አንዲት ሴት “በራችንን ያንኳኳው በዚህ አደጋ በግሏ እንደተሳተፈች ተናግራለች።” በባህር ዳርቻው አሸዋ ላይ የሚሄደው ህዝብ ከሁሉም አቅጣጫ የተውጣጡ ሰዎችን ያቀፈ ነው። የእሳት አደጋ ተከላካዮች፣ የስፖርት ቡድኖች፣ የአካባቢው ባለሱቆች፣ ሕፃናት፣ አረጋውያን፣ ሙሉ ቤተሰቦች፣ ሁለት ወንድ ልጆች በዊልቸር ላይ ሁነው ፣ የኮሴንዛ ሊቀ ጳጳስ ጆቫኒ ቼቺናቶ እና የላሜዚያ ቴርሜ ጳጳስ ሴራፊኖ ፓሪስ ተገኝተዋል።

በክሩቶ የቀረበ የመስቀሉል መንገድ ጸሎት
በክሩቶ የቀረበ የመስቀሉል መንገድ ጸሎት

መዝሙሮችና እና ጸሎቶች

አደጋው በተከሰተ ጊዜ ቀድመው ወደ ባህር ዳርቻው ከደረሱት ዉስጥ አንዱ የነበሩትን ቄስ ሮዛሪኦ ሞሮኔን እየተከተሉ “አንተ ከእኔ ጋር ከሆንክ ዬትኛዉም ወጀብ አያገኘኝም” የሚለዉን የምስጋና መዝሙር በእንባ እይታጠቡ ሲዘምሩና ሲጸሊዩም ነበር። ክርስቶስ በመስቀል እለት ወደ ቀራንዮ ተራራ ያደረገውን የመስቀል መንገድ በሚዘክርበት የመስቀል መንገድ ላይ በግፍ ለሚሞቱ ንፁሀን ህጻናት፣ በአለም አሳዛኝ ሁኔታ ለሚሰቃዩ ወይም ልዩ እና ራስ ወዳድነት በሚንጸባረቅባቸው ፖሊሲዎች ምክንያት ለሚሰቃዩ እና ልጆቻቸውን ላጡ እናቶችም ጸሎት ቀርቧል።

ለመስቀል መንገድ ጸሎት የተሰበሰበ ሕዝብብ
ለመስቀል መንገድ ጸሎት የተሰበሰበ ሕዝብብ

የአሸዋው ላይ እንባ

ሰማዩ መጀመሪያ ላይ ጥርት ብሎ ነበር ፣ ህዝቡ ሲደርስ ግን ዳመና ጋርዶት እንደመጨለም ሆነ ፣ የመርከቧ መስመጥ አደጋ መከሰትን ተከትሎ ለነበረው አሳዛኝ ድባብ አስተዋፅዖ ለማድረግ ይመስላል። የማይዛመዱ ጫማዎች፣ አልባሳት፣ መንሳፈፍያዎች ፣ መጫወቻ አሻንጉሊቶች እና የምግብ አቅርቦቶች የባህሩ የታችኛው ክፍል ሁሉንም ነገር ወደ ባህር ዳርቻው ተፍቶታል።  ከቅርብ ቀናት ወዲህ 'የሀዘን ባህር' እየተባለ የሚጠራውን ስፍራ የጎበኙት የተጎጂዎች ዘመዶች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና እራሳቸው በህይወት የተረፉ ሰዎች እነዚህን አሳዛኝ እቃዎች በማሰባሰብ ከእንጨትና ከሽቦ በተሰሩ መስቀሎች ስር ቀብረዋቸዋል። ከእነዚህ መስቀሎች በአንዱ ላይ አንዲት አሮጊት ሴት ተንበርክከው እያማተቡ የመቁጠሪያ ጸሎት ያደርጋሉ።ከዚያም የሊቀ ጳጳሱን የመዝጊያ ቃል ለማዳመጥ በዙርያው ካሉት ኮረብታዎች ከሚመጡ ሌሎች ህዝቦች ጋር ተቀላቅለዋል።

በ ‘ላምፔዱሳ’ እንዳለው ባህር ውስጥ ያለ የአበባ ጉንጉን

የመስቀል መንገዱ ሥነ ስርአት በዘላለማዊው የእረፍት ጸሎት አብቅቷል። ኢማሙ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ለተደረገው ድጋፍ ሁሉንም አመስግነዋል ፤ ከአባ ሮዛሪዮ ጋር በመሆንም ነጭ የአበባ ጉንጉን ወደ ባሕሩ ወርዉረዋል ፤ ይሄም ትዕይንት የዛሬ አስር ዓመት ፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ በላምፐዱሳ ከምድር ስር ሳይሆን ከሜድተራኒያን ባህር ስር የተቀበሩትን ሙታንን መታሰቢያ ለማክበር ያደረጉትን ተመሳሳይ ምሳሌያዊ ምልክት ሁሉም ሰው እንዲያስታውሰው አድርጓል።

ኢማሙ እና ካህኑ የአበባ ጉንጉን ወደ ባሕሩ ወርውረዋል
ኢማሙ እና ካህኑ የአበባ ጉንጉን ወደ ባሕሩ ወርውረዋል

 

07 March 2023, 16:50