ፈልግ

2019.03.11 Siria profughi bambini guerra Caritas 2019.03.11 Siria profughi bambini guerra Caritas  (Caritas italiana)

ካሪታስ ሶሪያ ሶሪያን መከራ ጊዜያቶቿ ወቅት እናስታውሳት

የኢኮኖሚ ውድቀት እና የኑሮ ማሽቆልቆል ፥ እንዲሁም ግጭቶች እና ከፍተኛ መዘዞቻቸው በሶሪያ ህዝብ ላይ እየተፈራረቁ ይገኛሉ። በተጨማሪም በየካቲት ወር የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥም ያለውን ሁኔታ እንዳባባሰው እና መሰረታዊ ፍላጎቶች እጅግ እየበዙ መምጣታቸውን የካሪታስ ሶሪያ የፕሮግራሞች ኃላፊ የሆኑት ሳራ ሃዚም ተናግረዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ አዲስ አበባ

ከአስር ዓመታት በላይ በዘለቀው ጦርነት ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ፣ እያሽቆለቆለ ያለው የኢኮኖሚ ቀውስ እና አሁን የተከሰተው ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ፥ ሶሪያውያን እርዳታ እና የረጅም ጊዜ የልማት ድጋፍ ፈላጊ አድርጓቸዋል።

የካሪታስ አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ፥ ከሀገር ውስጥ ካሪታስ ሀገረ ስብከቶች የተውጣጡ ፣ እንዲሁም የካሪታስ ሰራተኞች እና ዓለም አቀፍ በጎ ፍቃደኞች ፣ በችግር የተጠቃች ሊባኖስን ጨምሮ ባደረጉት ጥምር ሥራ ምስጋናዉን አቅርቧል።

ነገር ግን ይላሉ ፥ የካሪታስ ሶሪያ የፕሮግራም ኃላፊ እንዳብራሩት ፥ ካሪታስ አሁን የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲቀጥል ከተፈለገ እና በሚቀጥሉት ወራት ምግብ ፣ የህክምና አቅርቦቶች ፣ መጠለያ እና ሌሎች አስፈላጊ አቅርቦቶችን ለማቅረብ እንዲችል ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የገንዘብ ድጋፍ በጣም ይስፈልገዋል ብለዋል።

እነዚህ ገንዘቦች የረዥም ጊዜ ፍላጎቶችን ለማሟላት እና ቤተሰቦች ወደ የተረጋጋ ህይወት እንዲመለሱ ለመርዳት እንዲሁም ሶሪያ ራሷን ችላ እንድትቆምም ያግዛል ሲሉ ሳራ ሃዚም ይናገራሉ።

ካሪታስ ሶሪያ ከ12 ዓመታት በፊት የሶሪያ ቀውስ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሀገሪቱ ውስጥ የህዝቡን ፍላጎቶች ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራትን ሲሰራ ቆይቷል። ዛሬም ይላሉ ሳራ ሃዚም ፥ የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ በተከሰተው አደጋ ቡድኖቻች ስፍራው ድረስ በመሄድ ሥራውችን እየሰሩ ይገኛሉ። በአሌፖ ፣ ላታኪያ ፣ ታርቱስ እና ሃማ የተጎዱ ማህበረሰቦችን ለመርዳት ቦታው ላይ ተገኝተዋል

የተዘጋጁ ምግቦችን ፣ የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎችን ፣ የህፃናት ወተት እና የመጠጥ ውሃ በተጎዱ አካባቢዎች በሚገኙ የጋራ መጠለያዎች በማከፋፈል ላይ ይገኛሉ

ሃዚም አክለውም የመሬት መንቀጥቀጡ ቀውስ የመጣው በጦርነቱ ምክንያት የተከሰቱት በርካታ ድንገተኛ አደጋዎች መቋጫ ሳያገኙ መሆኑን ገልፀው እጅግ በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸው ተፈናቃዮች ፣ በአገር ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎችን ጨምሮ ፣ ከፍተኛ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ፣ “ቅድመ ማገገም እና መተዳደሪያ” ፕሮጀክቶችን ጨምሮ እልባት ሳያገኝ መሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል ብለዋል።

"ካሪታስ ሶሪያ በተለያዩ ዘርፎች እንቅስቃሴዎችን በመተግበር ላይ ትገኛለች"

የኢኮኖሚ ቀውስ

 እናም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት፥ ዘር እና ሃይማኖት ሳይለይ የመድኃኒት ፣ የመጠለያ እና የትምህርት እጦት ለማሟላት እየሞከረ ሳለ እና እርስ በእርስ ግጭቱ ባበቃበት ሠአት ነው ይህ የተፈጥሮ አደጋ ተከስቶ አገሪቱን እያሽመደመደው የሚገኘው።

በጦርነቱ ምክንያት እና በሶሪያ ላይ በተጣለው ማዕቀብ ሳቢያ በተፈጠረው የነዳጅ ፣ የኤሌክትሪክ እና የምግብ እጥረት በመከሰቱ ምክንያት ሶሪያ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ዉድቀት ተዳርጋለች ይላሉ ሃዚም።  

ከእነዚህ ውስጥ አንዳቸውም የሉም ሲሉ አክለው ከጦርነቱ በኋላ ድህነት እየተባባሰ መምጣቱን ገልጸዋል።

“ከዚህ ሁሉ በላይ አሁን የመሬት መንቀጥቀጡ አጋጥሞናል። ስለዚህ ከበፊቱ የባሰ ነው” ብለዋል።

 ከዓለም አቀፍ ትኩረት ውጪ መሆን

ስቃዩን ማባባስ ‘ለለጋሾች ድካም’ እና የዓለም አቀፉን ትኩረት ወደ ሌላ ቦታ ማዞርን ያመጣል ነው የተባለው።

ከጦርነቱ በኋላ ከብዙ አጋሮች እንደሰማነው ‘ከአስር ዓመታት ጦርነት በኋላ ሶሪያ 'ህፃን' አይደለችም’ የሚለውን አባባል ነው ፤ ይህም ማለት ራስዋን መቻል አለባት እንደማለት ነው።በመቀጠል በዩክሬን እና በሊባኖስ ከተከሰቱት ቀውሶች በኋላ የቤሩት ፍንዳታን በመጥቀስ ከዚህ የከፋው ደግሞ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዕርዳታ አሰጣጡ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደሩን ገልፀዋል ሃዚም።

እነዚያ ሁሉ ጉዳዮች በሶሪያ በሚደረገው እርዳታ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አሳድረዋል ሲሉ በዚህም የተነሳ ካሪታስ ሶሪያ ብዙ ፈተናዎች   እየገጠማት ነው ብለዋል።

“አሁንም እየተቀበልን ነው ፥ ነገር ግን በእነዚህ ሁሉ ቀውሶች ምክንያት በሌሎች ክልሎች ድጋፍ ለማድረግ የገንዘብ እጥረት አለ” ሆኖም ሌሎች የካሪታስ ቤተሰብ አባላት እና ለጋሾቻቸው የድርጅቱ ዋና የገንዘብ ምንጮች እንደሆኑም ገልጸዋል።

 በማገዝ ላይ ያሉ ወሳኝ አጋሮች

ሃዚም ፥ ካሪታስ ከሌሎች የእርዳታ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ምርጥ አጋርነት በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚደግፉት ገልጸዋል።

"በእርዳታ ውስጥ ማናቸውንም የዕርዳታ መደጋገምን ለማስወገድ አንድ ላይ ተቀናጅቶ መሥራቱ እና እያንዳንዱ ድርጅት ምን እና ዬት እየሰራ እንደሆነ ለማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው" ብለዋል።

 ሁሉም ነገር ያስፈልጋል

በአሁኑ ጊዜ የካሪታስ ሶሪያ ትልቁ ፍላጎት ምን እንደሆነ ሲጠየቁ ሳራ በማመንታት “ፍላጎቱ በጣም ትልቅ ስለሆነ ለመናገር ቀላል አይደለም” በማለት መልሰዋል።

ይሁን እንጂ በቅርቡ በመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ድንገተኛ አደጋ ብዙ ሰዎች ቤታቸውን በማጣታቸውና መተዳደሪያ ንብረታቸውን በማጣታቸው የከፋ የኢኮኖሚ ሁኔታን እንዳባባሰው አክለው ተናግረዋል።

“ብዙዎቹ በመጠለያ ውስጥ ናቸው። ስለዚህ ይህ የመጀመሪያው ፍላጎታቸው ነው”

ስለዚህ ፥ ከምግብና ከውሃ ባለፈ ፥ ካሪታስ በኪራይ ገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ እየጣረች እንደሆነ እና ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለማቋቋምና ኑሮን መልሶ ለመገንባት ፕሮጀክቶችን በመተግበር ላይ እንደምትገኝ ሃዚም ተናግሯል።

 መልዕክት

 ሳራ ሃዚም በዚህ ቃለ መጠይቅ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት እንዳለ ተጠይቀው "ባለፉት ዓመታት እና በተለይም አሁን ላይ ላደረጉልን ለጋስ ድጋፍ ሁሉንም አጋሮቻችንን ለማመስገን እፈልጋለሁ" እንዲሁም "ሶሪያን እንዳይረሱ ለማበረታታት እፈልጋለሁ ፥ ምክንያቱም አሁን አዳዲስ ቀውሶች እና አዳዲስ ችግሮች አሉብንና” በማለት ሃሳባቸውን ደምድመዋል።

“ሶሪያ ለረጅም ጊዜ ስትሰቃይ በመቆየቷ ምክንያት ቶሎ ለማገገም ይከብዳታል”

 

        

27 March 2023, 22:37