ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በካናዳ የጎበኙት የኢቃሉይት ግዛት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በካናዳ የጎበኙት የኢቃሉይት ግዛት 

ካናዳ ውስጥ በካቶሊክ ምዕመናን ላይ የሚፈጸም ወንጀል መጨመሩ ተገለጸ

በሃይማኖት፣ በፆታ፣ በዘር ወይም በጎሳ ላይ ያነጣጠሩ የጥላቻ ወንጀሎች ካናዳ ውስጥ መጨመራቸውን በአገሪቱ የተካሄደውን ጥናት ዋቢ በማድረግ ፖሊስ ገልጿል። በካናዳ በተካሄደው ጥናት መሠረት 3,360 የጥላቻ ወንጀሎች መፈጸማቸውን ሪፖርቱ ገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ካናዳ ውስጥ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2021 ዓ. ም. የወጡት የጥላቻ ወንጀል ሪፖርቶች ካለፈው ዓመት ጋር ሲወዳደር 27 በመቶ መጨመሩን ገልጸው፣ ወንጀሉ በካቶሊክ ምዕመናን ላይ 260 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ታውቋል። ካናዳ ውስጥ በተደረገው ጥናት መሠረት ወንጀሎቹ እንዴት እንደሚፈጸሙ እና በአንድ ሃይማኖት ላይ ያነጣጠሩ፣ በጾታ እና በዘር ወይም በጎሳ ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸውን ጥናቱ አመላክቷል።

የጥላቻ ወንጀሎች ዓይነት

ያለፉትን ዓመታት መረጃ ተከትሎ የተመዘገቡት የጥላቻ ወንጀሎች ከግማሽ በላይ (56%) የሚሆኑት በዋናነት ጥቃትን የማያካትቱ ተንኮሎች መሆናቸው ታውቋል። እንደ ሪፖርቱ ከሆነ፣ ሃይማኖታዊ ጥቃቶችን መሠረት በማድረግ የተገኙት ግኝቶች ያለፉ ሦስት ተከታታይ ዓመታትን መሠረት ያደረጉ መሆናቨው ተመልክቷል። በተለይም በአይሁዳውያን ላይ የሚፈጸሙ የጥላቻ ወንጀሎች በ47 በመቶ፣ በሙስሊሞች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በ71 በመቶ እና በካቶሊኮች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች 260 በመቶ መጨመራቸውን ሪፖርቱ አመላክቷል።

የወንጀሉ ሰለባዎች

ጾታዊ እና ዘርን ወይም ጎሳን ካነጣጠሩ የጥቃት አዝማሚያዎች ቀጥሎ ጎልማሶች እና ወንድ ልጆች በሃይማኖት ላይ ያነጣጠሩ የጥላቻ ወንጀሎች ሰለባ የመሆን ዕድላቸው ከፍተኛ መሆኑን ሪፖርቱ ገልጿል። በአንጻሩ "በፆታ ላይ ያነጣጠሩ የጥላቻ ወንጀሎች ሰለባ ከሆኑት መካከል ወደ ሦስት አራተኛ የሚጠጉት ሴቶች እና ልጃገረዶች መሆናቸውን ሪፖርቱ አክሎ አስታውቋል። የካናዳ የስታቲስቲክስ ቢሮ ይፋ ያደረገው መረጃ፣ ፖሊስ ከጥላቻ ወንጀሎች ጋር የመደቧቸው ክስተቶች መሆናቸው ታውቋል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2020 ዓ. ም. በማኅበራዊ ማንነት ላይ በተደረገ አጠቃላይ ዳሰሳ ጥናት መሠረት፣ በዘር የተከፋፈሉ ቡድኖች አባል መሆናቸውን የሚገልትጹ ካናዳውያን፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ መድልዎ ካጋጠማቸው ከሌሎች በዘር ከተከፋፈሉ አጋሮቻቸው ከሁለት እጥፍ በላይ መጨመራቸውን ሪፖርቱ ገልጿል።

ነባር ካናዳውያብ እና ፖሊስ

ብዙ ምክንያቶች ወንጀል ለፖሊስ ሪፖርት በሚደረግበት ዕድል ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ እና በኋላም ከፖሊስ በሚቀርብ የስታቲስቲክስ መረጃን የሚያንጸባርቅ መሆኑን ሪፖርቱ በተጨማሪ ገልጿል። ከነዚህም መካከል የአካባቢው ፖሊስ ልምድ፣ የኅብረተሰቡ አጠቃላይ ግንዛቤ እና ከራሱ ከፖሊስ ጋር ያለው ግንኙነትም ጭምር እንደሆነ ታውቋል።

ከቅኝ ግዛት እና ተዛማጅ ፖሊሲዎች የተነሳ በትውልዶች መካከል እንዲሁም በግለሰብ እና በተደራጀ ዘረኝነት በሚደርስ ጉዳት ምክንያት በርካታ የካናዳ ነባር ተወላጆች ከፍተኛ የወንጀል ሰለባነት፣ መድልዎ፣ ወንጀልን ለመከላከል በተቋቋሙ የፍትህ ሥርዓት ውስጥ ያላቸው ውክልና፣ በፖሊስ እና በሌሎች ተቋማት ላይ ያላቸው እምነት ዝቅተኛነትን ጨምሮ ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች እንደሚያጋጥማቸው ታውቋል። ሪፖርቱ በማጠቃለያው እነዚህ እና ሌሎች ምክንያቶች፣ የጥላቻ ወንጀል በፖሊስ ትኩረት ውስጥ አለመግባቱ ተጽዕኖን ሊያሳድሩ እንደሚችሉ አሳይቷል።

 

27 March 2023, 18:10