ፈልግ

ብፁዕ ካርዲናል ፍሪዶሊን አምቦንጎ በጉባኤው ላይ ንግግር ሲያደርጉ ብፁዕ ካርዲናል ፍሪዶሊን አምቦንጎ በጉባኤው ላይ ንግግር ሲያደርጉ 

የአፍሪካ ሲኖዶስ ጉባኤ፡ ቤተ ክርስቲያንን ለማደስ ‘ካይሮስ’ (ምቹ ጊዜ) ነበር ተባለ።

“ካይሮስ” የግሪክ ቃል ሲሆን ለሲኖዶሳዊነት የሚሆን መልካም ጊዜ (THE KAIRÓS OF SYNODALITY) (ለውሳኔ ወይም ለድርጊት የሚሆን መልካም ወይም ምቹ ወቅት/ጊዜ የሚለውን ያመለክታል)።

እ.አ.አ ከመጋቢት 1-6/2023 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ሲኖዶሳዊ ቤተ ክርስቲያን፡ ሕብረት፣ ተሳትፎ እና ተልዕኮ” በሚል መሪ ቃል የአፍሪካና የማዳጋስካር ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ህብረት ጉባሄ እና የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በጋራ ያሰናዱት የአፍሪካ ሲኖዶሳዊ ጉባኤ ሲፖዝዬም በአዲስ አበባ ፤ ዲ ሊኦፖል ኢንተርናሽናል ሆቴል ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል። በአፍሪካ ውስጥ ያለችው የካቶሊክ ቤተክርስትያን ቅድሚያ የሚትሰጣቸውን ጉዳዮች ስብሰባው ሲጠናቀቅ በሲኖዶሳዊው አህጉራዊ ጉባኤ ላይ ለአፍሪካ ልዑካን ቀላል ቀን አልነበረም።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ሲኖዶሳዊው መንገድ ከባድ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን የግድ አስፈላጊ ነው። አንዳንድ ጊዜ በወንድሞችና እህቶች መካከል አስቸጋሪ ንግግሮች ይነሳሉ። ለአፍሪካ ቤተክርስቲያን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ግንዛቤ በተመለከተ የብዙዎች ተሞክሮ ይህ ነበር። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ በአዲስ አበባ ዲ ሊዮፖል ሆቴል አዳራሽ ውስጥ የነበረው ስሜት፣ ቅዳሜ ከሰአት በኋላ የአፍሪካ ሲኖዶሳዊ ሲፖዝዬም ረቂቅ ሰነድ ለማጽደቅ ልዑካኑ በድጋሚ በተሰበሰቡበት ወቅት ውጥረት ውስጥ እንደነበሩ ሊገለጽ ይችላል።

የእግዚአብሔር ቤተሰብ በአፍሪካ

ሲስተር አስቴር ሉካስ ጆሴ ማሪያ ልዑካኑን “በዚህ ጊዜ እንደ እኔ ሳይሆን እንደ አንድ የአፍሪካ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ቤተሰብ ማሰብ አለብን” በማለት ልዑካኑን አሳስበዋል። እርስ በርሳችን እና መንፈስ ቅዱስን ከመስማት በቀር ሊደረግ የሚገባው ደረጃ ላይ ገና አልደረስንም። እንደ አፍሪካ ቤተክርስቲያን የምናቀርበው ይህንን ነው። እናም ቅድሚያ የሚሰጠው ማለት በጣም አስፈላጊው ነገር ነው፣ ሁሉም ነገር አይደለም። 15 ቡድኖች ስላለን 15 ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ቦታዎች ማግኘት እንፈልጋለን ይህም ወደ አምስት ዝቅ እናደርጋለን” ሲሉ ተናግረዋል።

ተሻጋሪ ርዕሶችን ማስቀደም

ሆኖም እንደተለመደው በመንፈሳዊ ማስተዋል፣ ከአስራ አምስቱ ውስጥ ጥቂት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች መምረጥ ፈታኝ ነበር። ለቅዳሜ ከሰአት በኋላ ለሚካሄደው የአመቻች ቡድን፣ ጉባኤውን በስምንቱ አቋራጭ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ወደ መግባባት ለመምራት ችኮላ ነበር።

ከብዙ ማዳመጥ በኋላ በስተመጨረሻ ከአስራ አምስቱ የስራ ቡድኖች የተውጣጣው ሐሳብ በአፍሪካ ላሉ ቤተክርስትያን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች አጉልቶ አሳይቷል።

1. በዘመናችን ባሉ ተግዳሮቶች ላይ የሚያተኩር ለቤተሰብ የሚደረግ ሐዋርያዊ እንክብካቤ እንደ ፍቺ፣ በፍቺ የተለያዩ ትዳሮች እና እንደገና ያገቡ ሰዎች፣ አማራጭ መንገዶች እና ከትዳር ተፋተው ብቻቸውን የሚኖሩ ቤተሰቦች የተመለከቱ ጉዳዮች።

2. እ.ኤ.አ. በ1995 ከመጀመሪያው የአፍሪካ ሲኖዶስ ጀምሮ በቤተክርስቲያኒቷ እንደ እግዚአብሔር ቤተሰብ ጽንሰ-ሀሳብ ውስጥ እንደተገለጸው የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ ችላ ሳይባል የአፍሪካን ባህላዊ እሴቶች ማጠናከር የተመለኩቱ ጉዳዮች።

3. እንደ ኡቡንቱ፣ ኡጃማአ፣ ኢንዳባ እና ፓላቨር ባሉ ፍልስፍናዎች ውስጥ እንደተገለጸው የአፍሪካን ማሕበረሰብ ባህል ግምት ውስጥ በማስገባት የጋራ ኃላፊነት እና ተመጋጋቢነት ቁልፍ መርሆዎች የተመለከቱ ጉዳዮች።

4. በአህጉሪቱ ብዙ ጊዜ ወደ ጦርነት እና ማህበራዊ ግጭቶች የሚመራውን የተፈጥሮ ሃብት ብዝበዛን ለመዋጋት ቁርጠኛ መሆን የተመለከቱ ጉዳዮች።

5. የስርዓተ አምልኮ መመሪያዎችን በተመለከተ ለምእመናን ንቁ ተሳትፎ መስጠት እና ስርዓተ አምልኮን ወቅቱን በዋጀ መልኩ የሚደረገውን እድሳትን ማሳደግ የተመለከቱ ጉዳዮች።

6. በቤተክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ ሲኖዶሳዊነትን ለማስፋፋት የመደመር እሳቤ ጎልቶ የሚታይበት የእግዚአብሔር ሕዝብ መመስረት የተመለከቱ ጉዳዮች።

7. ሴቶችን፣ ወጣቶችን እና ሁሉንም እንደ ተገለሉ ሆኖ የሚሰማቸውን የእግዚአብሔርን ህዝቦች ማካተት እና ማሳደግ የተመለከቱ ጉዳዮች።

8. የስነ-ምህዳር ፍትህ እና ተመጋጋቢነት የስነ-ምህዳር ችግርን ለመቅረፍ እንደ ሲኖዶሳዊ ለውጥ የህይወት መንገድ አድርጎ መመልከት የተመለከቱ ጉዳዮች በቀዳሚነት ተሰንደዋል።

ወንድሞች በአንድነት አብረው ሲኖሩ ምንኛ ጥሩ እና አስደሳች ነው!

ከሦስት ሰአታት በላይ የፈጀው የመጨረሻው ክፍለ ጊዜ ሲጠናቀቅ፣ በጉባኤው ላይ የተገኙት የቤተክርስቲያን መሪዎች ተራ በተራ የመዝጊያ ንግግር አድርገው ነበር።

ዝግጅቱን ያስተናገደው የአዲስ አበባው ሊቀ ጳጳስ እና የካቶሊክ የኢትዮጵያ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፊኤል በበኩላቸው፣ የአፍሪካ እና ማዳጋስካር ኤጲስ ቆጶሳት ሕብረት ጉባኤ (ሴካም) ሲምፖዚየም አድናቆታቸውን ገልጸዋል። የካቶሊክ ሲኖዶስ ጉባኤ ልዑካኑ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ደረጃ ሰነድ ለማቅረብ በማሰብ በጉዳዩ ላይ በጋራ እንዲያስቡበት እና ውይይት እንዲያደርጉ” ጥሪ አቅርበዋል።

ከጉባኤው በፊት በአክራ (ጋና) እና በናይሮቢ (ኬንያ) የተከናወኑትን ሁለት የዝግጅት ክፍለ ጊዜዎች ጨምሮ አጠቃላይ ሂደቱን የመሩት የአፍሪካ እና ማዳጋስካር ኤጲስ ቆጶሳት ሕብረት ጉባኤ (ሴካም) ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት የሞዛምቢክ ጳጳስ ሉሲዮ ሙአንዳላ የሚከተለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ምንባብ ጠቅሰዋል “ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣ እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል! በራስ ላይ ፈስሶ፣ እስከ ጢም እንደሚዘልቅ፣ እስከ አሮን ጢም እንደሚወርድ፣ እስከ ልብሱም ዐንገትጌ እንደሚደርስ ውድ ሽቱ ነው” (መዝሙር 133፡1) ሲሉ ተናግረዋል። ምንባቡ ጳጳስ ሙአንዳላ እንዳሉት በአፍሪካ አህጉራዊ ሲኖዶስ ጉባኤ ወቅት የነበረውን ተሞክሮ ጠቅለል አድርጎ አስቀምጧል ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

ሲኖዶሳዊነት፣ ሕብረት፣ ተሳትፎ እና ተልእኮ

የጳጳሳት ሲኖዶስ 16ኛ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ ዋና አስተዳዳሪ ብፁዕ ካርዲናል ሆለሪች ልዑካንን ባነጋገሩበት ወቅት በተለይ በረቂቅ ሰነዱ ላይ በተካሄደው ውይይት ወቅት ጉባኤውን ያሳየው መንፈስ እና ተነሳሽነት አድንቀዋል። እንዲህ ብለው ነበር “ውድ እህቶች እና ወንድሞች፣ ለዚህ አስደናቂ የማዳመጥ ጊዜ እግዚአብሔርን እና እናንተን ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። እዚህ ለተነጋገራችሁት እና ስለተወያያችበት ነገር በሙሉ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ስለዚህ አስፈላጊ በእርግጥም ሲኖዶሳዊነት፣ ኅብረት፣ ተሳትፎ እና ተልእኮ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የአፍሪካና የማዳጋስካር ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ህብረት ጉባሄ (ሴካም) ፕረዚዳንት ብፁዕ ካርዲናል ፍሪዶሊን አምቦንጎ ጉባኤውን በመጨረሻ ሲዘጉ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የአጥቢያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ላደረጉላቸው አቀባበል አመስግነዋል። በጉባኤው ላይ ከቫቲካን፣ ሴካም እና ከአፍሪካ እና ደሴቶች የተውጣጡ ልዑካንን ጨምሮ የባለሙያዎች ቴክኒካል ቡድን ጎብኚዎችን አመስግነዋል።

የካይሮስ ወቅት (“ካይሮስ” ‘KAIRÓS’ የግሪክ ቃል ሲሆን  ለውሳኔ ወይም ለድርጊት የሚሆን መልካም ወይም ምቹ ወቅት/ጊዜ የሚለውን ያመለክታል)

“በአፍሪካ ቤተክርስቲያንን ለማደስ ካይሮስ የመጀመሪያው ጉባኤ ነው። ለማጥናት ግን ደግሞ ሲኖዶሳዊነት ለመኖር ጊዜው ነበር። በአፍሪካ ውስጥ የእግዚአብሔርን ቤተሰብ ስሜት ለመለማመድ ጊዜ ነበር። የአፍሪካን አህጉር በሚመለከቱ ስስ ጉዳዮች ላይ መንፈስ ቅዱስን ለመስማት እርስ በርሳችን የምንደማመጥበት ጊዜ ነበር። እዚህ አፍሪካ ውስጥ ያለንን ተልዕኮ በጋራ የምናድስ ሲኖዶሳዊ ጉባኤ ነው” ብለዋል ብፁዕ ካርዲናል አምቦንጎ።

“አሁን የአፍሪካ አህጉር አቀፍ ደረጃ አብቅቶ የሲኖዶሱ ሂደት በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀጥሏል። ምናልባትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን እና ለአፍሪካ ቤተክርስቲያን እና ህዝቦች ትልቅ ስጋት የሆነውን እንደ ሃይማኖታዊ ርዕዮተ ዓለም አክራሪነት ያሉ የማይታለፉ ጉዳዮችን ለማስወገድ በቂ ጊዜ አልነበረም” በማለት ተናግረዋል።

የአህጉራዊው ሲኖዶስ ጉባኤ የመዝጊያ ፍጻሜውም እ.አ.አ እሁድ መጋቢት 5 ቀን 2023 በቅዱስ ገብርኤል ካቶሊካዊት በደብር የተካሄደው መስዋዕተ ቅዳሴ ስነ ስረዓት ተጠናቋል።

 

06 March 2023, 13:34