ፈልግ

2019.03.31 Merciful Jesus per la riflessione della domenica della Divina Misericordia

የሁለት ወንድማማቾች ምሳሌ

ኢየሱስ አይሁዳውያን ስለ እምነታቸው እንዲገለጥላቸው የሚከተለውን ምሳሌ ነገራቸው፡፡ “አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፤ አንድ ቀን የመጀመሪያውን እስቲ ና ወደ እርሻዬ ሂድና እረስልኝ አለው፡፡ እርሱም መጀመሪያ እምቢ አልሄድም አለ፤ በኋላ ግን ተጸጽቶ ሄደ፡፡ እንዲሁም ደግሞ ሁለተኛውን ተናገረው፤ እርሱም እሺ ጌታዬ ሲል መለሰለት፤ ነገር ግን አልሄደም፡፡ ታዲያ የአባቱን ፈቃድ የፈጸመ ከሁለቱ የትኛው ነው;$ አላቸው፡፡ የመጀመሪው ነዋ ሲሉ መለሱለት፡፡ ቀጥሎም ኢየሱስ “እውነት ልንገራችሁ ኃጢአተኞችና ዘማውያን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል አላቸው፡፡ ዮሐንስ በጽድቅ መጣ አላመናችሁትም፣ ኃጢአተኞችና ዘማውያን ግን አመኑት፡፡ እነርሱን እንኳ አይታችሁ አላመናችሁም እንደ እነርሱ ንሰሐ አልገባችሁም” (ማቴ. 21፣28-32) እያለ አጥብቆ ወቀሳቸው፡፡

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የመጀመሪያው ልጅ የኃጢአተኞች የቀራጮችና የዘማውያን ምሳሌ ነው፡፡ እነዚህ በኑሮአቸው ሁሉ ይጸየፉአቸው ነበር፣ ከሁሉ የባሱ በንሰሐ ተስፋ የሌላቸው መሰለው ይታዩ ነበር፤ ሆኖም ግን አይተው ሲታዩ የተስፋ ሰዎችና ይነቅፉዋቸው ከነበሩ የታይታ የጻድቃን የተሻሉ ሆነው ተገኙ፡፡ ሁለተኛው የፈሪሳውያን የሰዱቃውያን የሽማግሌዋችና የካህናት አለቆች ምሳሌ ነው፡፡

እንግዲህ የበለጠ ወግና የሕግ አጥባቂዎች አክባሪዎች ንጹሐን ይመስሉ ነበር፡፡ በውጭ ንጹሐን ሆነው የሚታዩ በሕዝብ ፊት የተፈሩና የተከበሩ ነበሩ፡፡ ከሁሉ በላይ የበለጡ ይመስላቸው ስለነበር ሕዝብ በተለይ የሙሴ ሕግ መምህራን እነዚያን ኃጢአተኞችና እርኩሶች አድርገው ይቆጥሩዋቸው ነበር፡፡ እነርሱ ግን በኢየሱስ አባባል ኃጢአቶኞች ዘማውያን ብለው ይንቁዋቸው ከነበሩት እጅግ የባሱ ሆነው ተገኙ፡፡ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ እንዲመሩ ብሎ በየጊዜው ነቢያትን ይልካቸው ነበር፡፡ እነርሱ እግዚአብሔር እፍ ባለባቸው መሠረት የእስራኤልን ሕዝብ በመንፈስ ይመሩዋቸው ነበር፡፡ የአምላክ ፈቃድ ይገለጥላቸው ሲሳሳቱ ይመክሩዋቸውና ይገስጹዋቸው ነበር፡፡ ሕዝቡ አብዛኛውን በነቢያት ስብከት ይጠቀሙ ነበር፡፡ ካህናት ጸሐፊዎችና ሊቃውንት ግን በትዕቢታቸው አይጠቀሙበትም ነበር፡፡ እነዚያ ኃጢአተኞች ይባሉ የነበሩ ግን በነቢያት ቃል ተቀስቅሰው ንሰሐ ይገቡና ሕይወታቸውን በማሻሻል ይለወጡ ነበር፡፡ በተቃራኒው ፈሪሳውያን በቀድሞ ሕይወታቸውንና መንገዳቸው ሙጭጭ ብለው ይቀሩ ነበር፡፡ ኢየሱስ ከመምጣት እንደዚሁ ነበሩ፤ ሕዝቡ ይሰማው ነበር እነርሱ ግን አይሰሙትም፡፡ 

ይህንን ከተመለከተ በኋላ በጣም አዝኖ “ቀራጮችና ኃጢአተኞች ዘማውያን ወደ መንግሥተ ሰማያት በመግባት ይቀድሙአችኋል፣ እነርሱ በነቢያት ስብከት ንሰሐ ገብተዋል፣ እናንተ ግን ንስሐ አልገባችሁም” እያለ ይገስጻቸው ነበር፡፡ ይነቅፉአቸው ከነበሩት ኃጢአተኞች እነርሱ እንደሚብሱ አስታቃቸው፡፡ ትዕቢታቸውን የልባቸውን ድንዳኔ ትተው እንደነዚህ ንሰሐ እንዲያደርጉ አነቃቃቸው፣ ቀሰቀሰቸው፡፡ ይህ የፈሪሳውያን ጉድለት አይደለም እኛስ እንደ እነርሱ ራሳችንን እንደ ጻድቃን ቆጥረን ሌሎችን ግን እንደ ኃጢአተኞች እንኮንናቸውም; ራሳችን እንደ እስራኤል ሕዝብ መሪዎች በውጫዊ ቅዱሳን በውስጣዊ ግን የዲያብሎስ አገልጋዮች ከሆንን ፈጥነን እንታረም፡፡ የክርስቶስ እውነተኛ አገልጋዮች እንሁን፡፡ እንደ ቅዱሳን እኛ የባስን ሌሎች የበለጡ እኛ ኃጢአተኞች ሌሎችን ግን እንደ ጻድቃን አድርገን እንመልከተ፡፡

 

 

25 January 2023, 15:50