ፈልግ

በኒካራጓ የማታጋልፓ አገረ ስብከት ጳጳስ ሮላንዶ አልቫሬዝ በኒካራጓ የማታጋልፓ አገረ ስብከት ጳጳስ ሮላንዶ አልቫሬዝ   (AFP or licensors)

ቤተክርስቲያን የጸሎት ቀን ስታውጅ የኒካራጓ ጳጳስ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እርግጠኛ ሊኮን አልተቻለም።

በኒካራጓ የማታጋልፓ አገረ ስብከት ጳጳስ ሮላንዶ አልቫሬዝ በቁም እስር የሚገኙ ሲሆን ከኒካራጓ መንግሥት ጋር በመተባበር የታጠቁ ቡድኖች በጳጳሳት እና በቀሳውስቱ ላይ የሚደርሱት ጥቃት በአካባቢው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ቀጥሏል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የኒካራጓዋ ቤተክርስትያን በላቲን አሜሪካ ሀገር በሚገኙ ደብሮች ውስጥ በዚህ አመት እ.አ.አ ነሐሴ 11 ቀን በጸሎት እና በቅዱስ ቁርባን አምልኮ ይከበራል።

እ.አ.አ ከነሐሴ 7-15 የሚካሄደው የብሔራዊ የማርያም ኮንግረስ አካል ሆኖ ነው የሚከበረው፣ ምክንያቱም የአጥቢያ ቤተክርስትያን በ6 የካቶሊክ ሬድዮ ጣቢያዎች መዘጋት እና በመታጋልፓ ኤጲስ ቆጶስ ላይ የመንግስት ጫና ቀጣይነት ያለው ችግር ስላጋጠማት ነው።

በግልጽ ችግሮችን የሚተቹ ጳጳስ

በኒካራጓ በፕሬዚዳንት ዳንኤል ኦርቴጋ መንግስት ኢላማ የተደረጉት የጳጳስ ሮላንዶ አልቫሬዝ እጣ ፈንታ በእርግጠኝነት አለመታወቁ ቀጥሏል።

በሀገሪቱ የሚገኙ የካቶሊክ ሬድዮ ጣቢያዎችን በመንግስት መዘጋታቸውን በመቃወም የተናገረሩት ጳጳስ በቁም እስር ላይ ውለዋል።

በአለም ዙሪያ በስፋት በተሰራጨው ምስል ላይ ጳጳስ አልቫሬዝ ተንበርክከው ምህረትን ሲለምኑ የታዩ ሲሆን የታጠቁ የፖሊስ አባላት ከበዋቸው የሚያሳይ ምስል በቅርቡ ይፋ መሆኑ ይታወሳል።

ክስተቱ የተከሰተው እ.ኤ.አ. ነሐሴ 4 ቀን ጳጳስ አልቫሬዝ ከስድስት ቄሶች እና ስድስት ካቶሊክ ምዕመናን ጋር በመሆን መስዋዕተ ቅዳሴ ለማድረግ ባሰቡበት ወቅት መስዋዕተ ቅዳሴውን እንዳያከናውኑ ታግዶ በቁምስናው ቤተክርስቲያን ውስጥ በር ተቆልፎባቸው በነበረበት ወቅት ነበር።

ጳጳስ አልቫሬዝ በመገናኛ ብዙኃን እና በማህበራዊ ድረ-ገጾች ሕዝቡ የኃይል እርምጃ እንዲወስድ እና ሀገሪቱን ለማተራመስ ተጠቅመዋል በሚል በባለስልጣናቱ ተከሰዋል።

ለእስር የተሰጠው ምላሽ

በርካታ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና የቤተክርስቲያን ቁርኝት ያላቸው ቡድኖች እስሩን አውግዘዋል፣ ጳጳሳት እና ሌሎች ቡድኖች ደግሞ በቤታቸው ተዘግተው ከሚገኙት ጳጳስ አልቫሬዝ ጋር ያላቸውን ቅርበት ገልጸዋል።

የላቲን አሜሪካ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባሄ ከኒካራጓ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን አጋርነት እና ቅርበት ገልጿል፣ ቤተክርስቲያኗ "የሰላምን ወንጌል ታውጃለች" እናም ከዚህ አንፃር ከሀገር ውስጥ እና ከዓለም አቀፋዊ ባለስልጣናት ጋር በትብብር ለመስራት ሁል ጊዜ ክፍት እና ዝግጁ እንደ ሆነች ተናግረዋል።

በቤተክርስቲያን እና በመንግስት መካከል ያለው ግጭት

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳትን እና የካህናትን ትንኮሳ ጨምሮ የቤተክርስቲያን መሪዎችን ዝም ለማሰኘት የበርካታ ጥቃቶች እና ሙከራዎች ኢላማ ሆና ቀጥላለች።

ኤጲስ ቆጶስ አልቫሬዝ እ.አ.አ በነሐሴ 4 የቁም እስረኛ ከሆኑበት ጊዜ ጀምሮ፣ የኒካራጓ መንግስት ሌላ የካቶሊክ ሬዲዮ ጣቢያ እና አንድ መቶ ተጨማሪ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በመዝጋት የካቶሊክን ድምጽ በሀገሪቱ ውስጥ ዝም ማሰኘቱን ቀጥሏል።

የኒካራጓ መንግስት የቤተክርስቲያን ተወካዮችን ዝም ለማሰኘት፣ አብያተ ክርስቲያናት እንዲከበቡ እና ቀሳውስትን እና ምእመናንን በማዋረድ ተከሷል።

12 August 2022, 14:37