ፈልግ

እህት ማርያ ሮዛ ሌጎል እህት ማርያ ሮዛ ሌጎል  

የእህት ማርያ ሮዛ ሌጎል የሕይወት ትሩፋት የሚተርክ ጥናታዊ ፊልም ይፋ ሆነ

በላቲን አሜሪካ አገር ሆንዱራስ ወደ 90,000 የሚጠጉ ልጆችን ከድህነት እና እንግልት እንዲወጡ የረዱት የእህት ማርያ ሮዛ ሌጎል ሕይወት እና ትሩፋት የሚተርክ ጥናታዊ ፊልም ሰኞ መጋቢት 26/2014 ዓ. ም. ለዕይታ ቀርቧል። በቫቲካን ውስጥ የታየውን ፊልም የታደሙትም በቅድስት መንበር የሚገኙ የልዩ ልዩ አገራት አምባሳደሮች መሆናቸው ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በሆንዱራስ እንደ ውድ ትሩፋት ትተውት የሄዱት እና “በዚህ ብርሃን” የሚል ርዕሥ የተሰጠው የእህት ማርያ ሮዛ ሌጎል የሕጻንነት ታሪክ ገላጭ ፊልሙ፣ በቅድስት መንበር ሥር የሆንዱራስ ኤምባሲ እና “ኦዜርቫቶሬ ሮማኖ” የተባለ በቅድስት መንበር የስፓኒሽ ቋንቋ ጋዜጣ አዘጋጅ ክፍል የጋራ አስተባባሪነት ሰኞ መጋቢት 26/2014 ዓ. ም. ለእይታ መቅረቡ ታውቋል። ከዘጋቢ ፊልሙ ዋና አዘጋጅ ከሆኑት ጄሲካ ሶሮዊትዝ እና ከተባባሪ ዳይሬክተሮቻቸው ኒኮሌ ቤርናርዲ እና ላውራ ቤርሙዴዝ፣ የእህት ማርያ ሮዛ ሌጎል ሕይወት አስመልከትው በዕለቱ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀርበው የበለጠ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሁሉ ዘርፍ የታየ የሴቶች ብልህነት

እህት ማርያ ሮዛ ሌጎል የመሠረቱት የመጀመሪያው የሕጻናት ማሳደጊያ እ. አ. አ በ1964 ዓ. ም. ማለትም ማዕከሉ ከተቋቋመ ከሁለት ዓመት በኋላ አገልግሎት መጀመሩ ታውቋል። ከመጀመሪያዎቹ የሕጻናት ማሳደጊያ ተሞክሮዎች በመነሳት በመላው የላቲን አሜሪካ አገራት ከ500 በላይ የሕጻናት ማሳደጊያዎች ሊቋቋም መቻላቸው ታውቋል። በሕጻናት ሕይወት ላይ በጎ ተጽእኖን ላሳደረው ሁለንተናዊ አቀራረብ ምስጋና ይግባውና፣ ለሕጻናቱ ዘመዶች እና ለማኅበረሰባቸው የሥራ ዕድል በመፍጠር በወቅቱ ትምህርታዊ ፕሮግራሞችን በማበረታታት የእህት ማርያ ሮዛ ሌጎል እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋጾን ማበርከቱ ታውቋል። በወቅቱ ለነበረው አምባገነናዊ ሥርዓት፣ ለወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት እና ለአካባቢያዊ አደጋዎች ያልትንበረከኩት እህት ማርያ ሮዛ ሌጎል፣ ሥፍር ቁጥር ለሌላቸው ድሃ ማኅበረሰብ የሥራ እድሎችን ከከፈቱላቸው በኋላ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተይዘው በተወለዱ 93 ዓመታቸው፣ ጥቅምት ወር 2013 ዓ. ም. ማረፋቸው ታውቋል።

የብጽዕና አዋጅ ጥረት

የሆንዱራስ ዋና ከተማ ቴጉሲጋልፓ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ካርዲናል ኦስካር አንድሬስ ሮድሪጌዝ ማራዲያጋ የእህት ማሪያ ሮዛ ሌጎል ብጽዕናን ለማሳወቅ የሚደረግ ጥረት እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልጸው፣ ምስክርነት ያላቸው በሙሉ ቀርበው ምስክርነታቸውን እንዲገጹ አደራ ብለዋል። እህት ማርያ ሮዛ ሌጎል በሰባ የአገልግሎት ዓመታት ውስጥ እጅግ በርካታ ሥራዎችን ማከናወናቸውን የገለጹት ኒኮሌ ቤርናርዲ፣ ከሥራዎቻቸው ብዛት የተነሳ የተሟላ ዝርዝር ለማውጣት ሞክረው ያልተሳካላቸው መሆኑን አስረድተዋል። “እሷ እራሷ በስድስት ዓመቷ ወላጅ አልባ ሆና ነበር” ያሉት ኒኮሌ ቤርናርዲ፣ በልጅነታቸው ወላጆችን ላጡት ሕጻናት መኖሪያ ቤት ለመስጠት እንደምትፈልግ አስታውሳለች። “ሰዎች የሕክምና አገልግሎትን ብቻ ሳይሆን ክብርም ሊሰጣቸው እንደሚፈልጉ ይገባት ነበር” ያሉት ኒኮሌ፣ መነኩሴዋ የኤች አይ ቪ ሕመም ላለባቸው ሕጻናት መጠለያን አዘጋጅታ መስጠቷን ተናግራለች። እ. አ. አ. በ2001 ዓ. ም. በሆንዱራስ ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር እኩል የትምህርት ዕድል እንዲኖራቸው በመፈለግ ለአንዳንድ ድሃ ሴቶች ትምህርት ቤት እንዲከፈት ማድረጓን ገልጻለች።

የእህት ማርያ ሮዛ ሌጎል ሕይወት የሚተርክ ጥናታዊ ፊልም በመሰራቱ የተሰማትን ደስታ የገለጸችው ኒኮሌ ቤርናርዲ፣ ጥናታዊ ፊልሙን ለመሥራት የሆንዱራስ ሕዝብ በትክክል እጅግ መሠረታዊ ተሳትፎ ማበርከቱን አስረድተዋል።

07 April 2022, 17:13