ፈልግ

የዓለም ገዳማውያት የበላይ አለቆች ኅብረት የዓለም ገዳማውያት የበላይ አለቆች ኅብረት 

ሲኖዶሳዊነት በገዳም ሕይወት ውስጥ ማዕከላዊ ሥፍራ እንዳለው ተገለጸ

“ከደካማነት ተነስተን ሲኖዶሳዊ ጉዞን መጀመር" የሚል መሪ ሃሳብ በመያዝ፡ የዓለም ገዳማውያት የበላይ አለቆች ከሚያዝያ 24 – 28/2014 ዓ. ም. ድርስ በሮም 22ኛ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንደሚያደርጉ ታውቋል። ገዳማውያቱ በጉባኤው ቀናት ውስጥ የሚወያዩባቸው ርዕሠ ጉዳዮች ዓርብ ሚያዝያ 21/2014 ዓ. ም በቫቲካን በሚቀርብ ጋዜጣዊ መግለጫ በኩል ይፋ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ከ71 አገራት የተወጣጡ ወደ 700 የሚጠጉ ገዳማውያት በሮም በሚካሄድ 22ኛ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ እንደሚካፈሉ ታውቋል። “በሲኖዶሳዊ ሂደት ወቅት ደካማነትን እንገንዘባለን” በሚል ርዕሥ የሚካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ 520 የገዳማውያት የበላይ አለቆች እንደሚካፈሉት ታውቋል። ሲኖዶሳዊነት ጭብጥ ባላቸው አምስት ቁልፍ ሃሳቦች ላይ እነርሱም ተጋላጭነት፣ ሲኖዶሳዊ ጉዞ፣ የገዳም ሕይወት እና ሲኖዶሳዊነት፣ ወደ ሌሎች ዘንድ መሄድ እና የለውጥ ጥሪዎች የሚሉት የጉባኤው ዋና ሃሳቦች መሆናቸው ታውቋል። ከ10 ተናጋሪዎች በላይ የሚቀርቡበትን የጉባኤው ዝግጅት፣ በቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል በኩል፣ ዓርብ ሚያዝያ 21/2014 ዓ. ም. እኩለ ቀን ላይ የኅብረቱ ፕሬዝደንት እህት ዮላንታ ካፍካ፣ ዋና ጸሃፊዋ እህት ፓትሪሲያ መሬይ፣ የእመቤታችን ማርያም እህቶች ማኅበር የበላይ አለቃ እህት ፍራንካ ዞንታ እና የኖትር ዳም የትምህርት ቤት እህቶች ማኅበር ጠቅላይ አለቃ እህት ሮክሳን ሻሬስ መግለጫ እንደሚሰጡ ታውቋል።     

ጉባኤው ለመደማመጥ እና ለምርምር ልዩ ቦታ የሚሰጠው ነው

ሲኖዶሳዊነት የሚገለጽባቸው ብዙ መንገዶች ናቸው ያሉት የኅብረቱ ፕሬዚደንት እህት ዮላንታ፣ ጉባኤያቸው የሚካሄድበት ዘዴ እና ይዘት የገዳማውያትን የምንኩስና ሕይወት እና ልምድ የሚገልጽ እንደሆነ ምልአተ ጉባኤው ያስረዳል ብለው፣ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ አማካይነት እርስ በእርስ የመደማመጥ ዕድልን እንደሚያገኙ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። ለቤተክርስቲያን ሲኖዶሳዊ ሂደት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ እንዳላቸው የገለጹት የኅብረቱ ፕሬዚደንት እህት ዮላንታ አክለውም፣ በሲኖዶሳዊ ዘይቤ መደማመጥን እንዴት ማበረታታት እንደሚቻል፣ ተጋላጭነትን እንደ አንድ ሰብዓዊ ባሕርይ በመገንዘብ፣ ጥበብ በታከለበት የጋራ የማስተዋል ዘዴ፣ እንደ ቤተ ክርስቲያንም ተጋላጭነትን እንዴት መመልከት እንደሚገባ እንወያይበታለን" ብለዋል።

የዓለም አቀፍ የበላይ አለቆች ህብረት አባላት ብዛት

እ. አ. አ ከ 1965 ዓ. ጀምሮ በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኝ ዓለም አቀፍ የገዳማውያት የበላይ አለቆች ኅብረት፣ በርቀት፣ በቋንቋ እና በባሕል ልዩነቶች ሳይገደብ ለመግባባት የሚያስችሏቸውን አዳዲስ ስልቶች በመቀየስ ከኅብረቱ ጠቅላይ አለቃ ጋር ለመገናኘት የሚያስችሉ ድልድዮችን እና መረቦችን የሚያበጅ የጋራ መሰብሰቢያ ቦታ ሆኖ ሲያገለግል መቆየቱ ታውቋል። የኅብረቱ አካል የሆኑ የገዳማውያት ጠቅላይ ቤቶች በዓለም ዙሪያ በ 97 አገሮች ውስጥ እንደሚገኙ እና 1900 አለቆችን የሚያካትት መሆኑ ታውቋል። በአውሮፓ ውስጥ በ25 አገሮች 1046 አለቆች እንዳሉ፣ በእስያ በ16 አገሮች 184 አለቆች፣ በአሜሪካ በ30 ግዛቶች 479 አለቆች፣ በአፍሪካ ውስጥ በ22 አገሮች 166 አለቆች፣ በኦሽንያ በሚገኙ 4 አገሮች 28 አለቆች እንደሚገኙ ታውቋል። በምልአተ ጉባኤው ላይ ከፍተኛ ቁጥር የሚይዙት ከአውሮፓ አህጉር የተወከሉት ሲሆን ከአፍሪካ አህጉር በብዛት ከፍተኛ የተወካይ ቁጥር ያላት አገር ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ መሆኗ ታውቋል። ከእስያ አህጉር ሕንድ፣ ቀጥለውም ሰሜን አሜሪካ፣ መካከለኛው እና ደቡብ አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ብራዚል መሆናቸው ታውቋል።

27 April 2022, 15:01