ፈልግ

በዩክሬን ውስጥ የሚገኝ መካነ መቃብር በዩክሬን ውስጥ የሚገኝ መካነ መቃብር  

ፓትሪያርክ በርተሎሜዎስ፡- የሰውን ልጅ ታላቅ የጦርነት ሽንፈት ያጋጠመው መሆኑን ገለጹ

የቁንስጥንጥንያው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ በርተሎሜዎስ፣ በምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ሚያዝያ 16/2014 ዓ. ም. የተከበረውን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የሰውን ልጅ ታላቅ የጦርነት ሽንፈት ያጋጠመው መሆኑን ገልጸዋል። በዓለማችን ውስጥ ሰላም እና ፍትህ እንዲወርድ የጠየቁት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ በርተሎሜዎስ፣ የሰው ልጅ ክብር ዝቅ በሚደረግበት ጊዜ የታየውን የክርስቲያኖች ዝምታ አውግዘዋል። ቅዱስነታቸው አክለውም ኢ-ፍትሃዊነትን የሚለውጥ ክርስቲያናዊ አስተሳሰብ ብቻ መሆኑንም ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

“የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንጸባራቂ የትንሳኤ ዜና በድጋሚ የተሰማው፣ በመካከላችን ብዙ የጦርነት ጥቃት ሰለባ የሆኑ ንጹሐን ሰዎች እና ስደተኞች በሚገኙበት የጭንቀት ወቅት ነው” በማለት ገልጸዋል። የቁስጥንጥንያው ፓትሪያርክ፣ ብጹዕ ወቅዱስ በርተሎሜዎስ ለምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት፣ ከነዚህም መካከል ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ባስተላለፉት የትንሳኤው በዓል መልዕክታቸው አማካይነት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። በዩክሬን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በመልዕክታቸው ያስታወሱት ፓትሪያርክ በርትርሎሜዎስ፣ "የዩክሬን ሕዝብ ከባድ የጦርነት መስቀል መሸከሙን" እና በቅርቡ በፖላንድ ያገኟቸውን ስደተኞች አስታውሰዋል። “ለሰላምና ፍትሕ ለጎደላቸው በሙሉ እንጸልይ” ያሉት ፓትሪያርኩ፣ የሰውን ልጅ ክብር ውድቀት ሲያጋጥመው የታየውን የክርስቲያኖች ዝምታ አውግዘዋል።

የቁስጥንጥንያው የክርስቲያኖች አንድነት ፓትርያርክ፣ የብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ በርተሎሜዎስ ተንታኝ፣ ኒቆስ ጾይቲስ እንደገለጸው፣ ምንም እንኳን የሰው ልጅ ሁል ጊዜ በሰላም ለመኖር ጥረት ቢያደርግም፣ ቀጣይነት ባለው ጦርነት ውስጥ እንደሚገኝ አስረድቶ፣ የሰው ልጅ ስብዕና መውደቁ እና በዓለም ላይ ሰላም መጥፋት የሚያሳዝን መሆኑን ገልጿል። ታላላቅ ፈላስፋዎች፣ በሰው ልጅ የታሪክ ሂደት፣ የሰው ልጅ ሕይወት የሚወሰነው የሰው ልጅ ራሱ በሕይወት ለመኖር ያለውን ፍላጎት እንደሚያካትት፣ ሆኖም ግን የቅርብ ጊዜ እውነታዎችን ስንመለከት፣ በዓለማችን ውስጥ ሞት አሸናፊነትን የተጎናጸፈ ይመስላል ብሏል።

ክርስቲያናዊ አስተሳሰብ ኢ-ፍትሃዊነትን ያግዳል

ብጹዕ ወቅዱስ በርተሎሜዎስ በትንሳኤ በዓል መልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸው፣ ከተጎዱት ጋር የሰው ልጅ በጦርነት ውስጥ ትልቅ ሽንፈት እድናጋጠመው እና የሰው ልጅ በረጅም ታሪኩ ጦርነትን ማስወገድ እንዳልቻለ፣ ችግሮችን ለመፍታት አለማቻል ብቻ ሳይሆን አዳዲስ እና የበለጠ ውስብስብ ችግሮችን መፈጠሩንም አስታውሰዋል። ቅዱስነታቸው በመልዕክታቸው፣ የሰው ልጅ መለያየትንን እና ጥላቻን ይዘራል፣ በህዝቦች መካከል ያለውን ልዩነት ያሰፋል” ማለታቸውን ያስታወሰው ኒቆስ ጾይቲስ በመቀጠልም፣ እነዚያን ግፍች ሊለውጣቸው የሚችለው ክርስቲያናዊ አስተሳሰብ ብቻ እንደሆነ ግልጽ በሆነ መንገድ ከልብ ለመግለጽ እንደሚፈልጉ፣ ይሁን እንጂ በሚያሳዝን ሁኔታ በክርስቲያኖች መካከል ያለው መለያየት ቤተክርስቲያናችን የጋራ ድምጽ እንዲኖራት እና ሁኔታዎችን በጥብቅ ለመቃወም እንደማይፈቅድ መናገራቸውን አስታውቋል።

“የሰው ልጅ ያለ ጦርነትና ዓመፅ መኖር ይችላል” የሚለው የብጹዕ ወቅዱስ በርተሎሜዎስ ምልክት፣ ነገር ግን ለክርስቲያን ማኅበረሰብ ከሁሉ አስቀድሞ ለፍጥረታት በሙሉ የ “ሰላም ፈጣሪ” መሆን ተገቢ እንደሆነ አስታውሰዋል። ነገር ግን ይህ እንዳይሆን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ግለሰባዊነት በመኖሩ የሰው ልጅም ለዚህ ዋጋ እየከፈለ መሆኑን፣ የብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ በርተሎሜዎስ ተንታኝ ኒቆስ ጾይቲስ አስረድቶ፣ የተከፋፈለ ቤተ ክርስቲያን የሞትን አስከፊነት እንዴት ማሰማት እንዳለበት አያውቅም ማለታቸውን ገልጿል። ብጹዕ ወቅዱስ በርተሎሜዎስ ለምዕመናን ባስተላለፉት መልዕክት “ክርስትና ርዕዮተ ዓለም ሳይሆን የሕይወት እውነታ ነው” ማለታቸውንም አስታውሷል። የቤተ ክርስቲያንነት ስሜት ሊኖር እንደሚገባ የጠየቀው የብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ በርተሎሜዎስ መልዕክት፣ ቤተ ክርስቲያን ማለት “የእኔ መኖር የሚታወቀው የጎረቤቴ መኖር ሲረጋገጥ ማለት እንደሆነ እና ሌላውን በትዕቢት መቀበል ሳይሆን እንክብካቤ በማድረግ እስከ መስዋዕትነት መድረስ መሆኑን እና ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ክሪሶስቶሞን በማስታወስ ባቀረቡት መልዕክታቸው፣ ሁሉም ሰው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የአንድ መንጋ አካል ስለሆንን የአንድ እናት ቤተ ክርስቲያን ልጆች በመሆናችንም እርስ በእርስ በትሕትና መገናኘት አለብን እንጂ ከራስ ወዳድነት ጋር መሆን አይገባንም ማለታቸውን አስረድቷል።

የሲኖዶሳዊነት አስፈላጊነት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያር በርተሎሜዎስ፣ እ. አ. አ. በ 2014 ዓ. ም. በኢየሩሳሌም በተገናኙበት ወቅት፣ በቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ እና በወቅቱ የቁስጥንጥንያው የውህደት ፓትርያርክ በነበሩ በብጹዕ ወቅዱስ አጥናጎረስ መካከል የተከበረውን 50ኛ ዓመት የወዳጅነት በዓል ፓትሪያርክ በርተሎሜዎ ቀዳማዊ ለመላው ክርስቲያኖች አስታውሰዋል። እ. አ. አ. በ 2014 ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ እና ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ በርተሎሜዎስ፣ ክርስቲያኖችን ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ ዓመታት በኋላ እ. አ. አ በ 2025 ዓ. ም. በኒቂያ እንዲገናኙ መጋበዛቸው እና የሃይማኖት መግለጫው የተቋቋመበትን የቤተክርስቲያን ሲኖዶሳዊነት ለማክበር ማቀዳቸው ይታወሳል። የቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊነት ማለት አብሮ መኖር ማለት እንደሆነ እና ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው በኅብረት መጓዝ ማለት እንደሆነ የገለጸው የብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ በርተሎሜዎስ ተንታኝ፣ ኒቆስ ጾይቲስ፣ ማስታወስ ያለብን፣ የቤተ ክርስቲያን ታላላቅ አባቶች እንደተናገሩት ሁሉ፣ ሲኖዶሳዊነት እውነተኛ የሕይወት ፍጻሜ ትርጉም የሚገኝበት መሆኑን በግለጽ ትንታኔውን ደምድሟል።

25 April 2022, 17:47