ፈልግ

በጥር ወር በአሜርካ ኦርላንዶ ግዛት 100,000 ሴቶች ከሥራ ገበታ ተወግደዋል በጥር ወር በአሜርካ ኦርላንዶ ግዛት 100,000 ሴቶች ከሥራ ገበታ ተወግደዋል  (ANSA)

ሴቶች በዓለም ዙሪያ የተስፋ ምንጮች መሆናቸው ተገለጸ

የካቲት 25/2014 ዓ. ም. የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማስድረግ የዓለም ካቶሊካዊ ሴቶች ማኅበራት ኅብረት፣ በመሪነት ደረጃ የሚገኙ የልዩ ልዩ አብያተ ክርስቲያናት ሴቶችን እና አንዳንድ የቅድስት መንበር አምባሳደሮችን ያሳተፈ የአውታረ መረብ ላይ ስብሰባ ማዘጋጀቱ ታውቋል። በስብሰባው ላይ የቀረቡት አስተያየቶችም ሴቶች የተቸገሩትን ተቀብለው የማስተናገድ፣ ችግሮችን የመቋቋም እና በአመጽ ውስጥ ያሉትን የማስታረቅ ችሎታቸው ከፍተኛ መሆኑን አጉልቶ በማሳየት፣ በዚህም የወንድማማችነት አዲስ ተስፋ ዋና ተዋናይነታቸው እየጨመረ መምጣቱን አብራርተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

"ሴቶች፣ ማኅበራዊ ቀውስ እና መረጋጋት" በሚል ርዕሥ የተዘጋጀውን የአውታረ መረብ ላይ ስብሰባን በቅድስት መንበር ስር የሚገኙ የአርጄንቲና፣ የአውስትራሊያ፣ የኮሎምቢያ፣ የአይርላንድ እና የሆላንድ ኤምባሲዎች አስተባባሪነት በጋራ ያዘጋጁት፣ የዓለም ካቶሊካዊ ሴቶች ማኅበራት ኅብረት እና በጳጳሳዊ ምክር ቤት የሐይማኖት ተቋማት የጋራ ውይይት አስተባባሪ ጽሕፈት ቤት መሆናቸው ታውቋል። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ የካቲት 25/2014 ዓ. ም. ከሰዓት በኋላ የተዘጋጀው ስብሰባ ዋና ዓላማ፣ ሴቶች በአሁን ወቅት በዓለማች የተከሰቱ ቀውሶችን ለማርገብ ያሳዩትን ችሎታ ለማንፀባረቅ ያለመ መሆኑ ታውቋል።

ልዩ ልዩ የሃይማኖት ተቋማትን ያሳተፈ ዝግጅት ነበር

ሃይማኖታዊ ባህሪ የነበረው የአውታረ መረብ ላይ ስብሰባው የሙስሊም፣ የሂንዱ፣ የቡድሂስት፣ የአይሁድ፣ የማኅበረ ቅዱሳን እና የካቶሊክ ሃይማኖታዊ ማኅበረሰቦችን እና በቅድስት መንበር በኩል የተለያዩ አገራት ሴት አምባሳደሮችን ያሳተፈ እንደነበር ታውቋል። በስብሰባው ላይ የቀረቡት የውይይቱ ርዕሦች በሙሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የዚህ ዓለም አቀፍ ቀን ዋና ርዕሠ ጉዳይ የነበሩ የሰብዓዊ ወንድማማችነት፣ የዓለም ሰላም፣ የጋራ መኖሪያ ምድራችን እና “ሁላችን ወንድማማቾች ነን” በሚለው የር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ሰነድ ውስጥ በሚገኙት እሴቶች ላይ ያተኮረ እንደነበር ታውቋል።

የሰላም ጸሎት

በዝግጅቱ መክፈቻ ላይ ሁሉም ተናጋሪዎች በሕዝቦች መካከል ሰብዓዊ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንዲቻል፣ በጦርነት ውስጥ በምትገኝ ዩክሬን ሰላምን እንዲያመጣ በማለት የእግዚአብሔር ዕርዳታ በጸሎታቸው ጠይቀዋል። ቀጥለውም በጳጳሳዊ ምክር ቤት፣ የሐይማኖት ተቋማት የጋራ ውይይት አስተባባሪ ጽሕፈት ቤት ፕሬዚደንት ብጹዕ ካርዲናል ሚገል አንገል ኣዩሶ፣ የቅድስት መንበርን መልካም ምኞት በመግለጽ ባደረጉት ንግግር፣ ሴቶች በሰዎች መካከል ፍቅር እንዲበዛ ጉልበት ለሚሆናቸው ይቅር ባይነት ከፍተኛ ግምት የሚሰጡ መሆናቸውን አስረድተዋል።

እንግዳን የመቀበል ተፈጥሯዊ ስጦታ

ከብጹዕ ካርዲናል ሚገል አንገል ኣዩሶ ንግግር በኋላ የተለያዩ ሃይማኖቶችን ወክለው የተገኙት ሴት መሪዎች ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የሰሜን አሜሪካ የሴቶች መብት እና ሰብዓዊ ክብር እንቅስቃሴ ተወካይ ወ/ሮ ሜሪ ኤልሳቤጥ ስትዋርት በንግግራቸው፣ ሴቶች “ሁላችንም ወንድማማቾች እና እህትማማቾች ነን” የሚለውን አመለካከት ለማራመድ የሚያስችል ጽናት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ሴቶች የግጭት አስታራቂዎች ናቸው

በጣሊያን የቡዳ እምነት ተከታዮች ኅብረት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ኤሌና ሴሺን፣ የቡዳ እምነት ተከታይ ማኅበረሰብ ተነሳሽነት በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ስቃይ ለማርገብ የሚደረጉ ጥረቶችን በመርዳት ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸው፣ ጥረታቸው በገዳማት እና ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሥርዓተ ፆታ እኩልነትን ማሳደግ እንደሆነ አስረድተዋል።

የአፍሪካ ሴቶች በኮቪድ-19 ወረርሽ ወቅት

የዓለም አቀፍ የአይሁድ ሴቶች ምክር ቤት የሃይማኖቶች እና የባህላዊ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆንት ወ/ሮ ናዲን ያርኪ፣ የአብርሐም ሚስት የሳራን ምሳሌ በመከተል፣ እምነቷ ባሏን እንድታምን የሚያደርጋት መሆኑን በመግለጽ፣ የአይሁድ ሴቶች እምነት በስፔን ስደት ወቅት እና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ያስተላልፈውን ጽናት አስታውሰው፣ ከዚያ ፅናት የሚገኘው አንድነት በሰው ልጆች እና በሕዝቦች መካከል ያለውን አብሮነት ማመን መሆኑን አረጋግጠዋል።

የአምባሳደሮቹ ንግግር

"ካቶሊካዊ አመለካከት" እንቅስቃሴ ቃል አቀባይ ሆና የሠራችው ሞኒካ ሳንታማሪና ሴት መሪዎችን በመወከል ባደረገችው ንግግር፣ የድርጅታቸው ዓላማ የሴቶችን ሁለንተናዊ እድገት ለማምጣት ያለመ መሆኑን ገልዘው፣ ከሰሜን አሜሪካ ብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጋር በመተባበር ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሴቶች ላይ በሚያሳድረው ተጽዕኖ ላይ የተለያዩ ሥራዎች መካሄዳቸውን፣ ከዚህም ጋር ትኩረትን የሚሹ ጉዳዮች ለምሳሌ የሴት ሥራ አጥነት መጨመር፣ ጾታዊ ጥቃት እና ድህነት የሚሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

05 March 2022, 16:18