ፈልግ

ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን  የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት 

ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ በአቡነ መርቆሪዮ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ!

ብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ፍራንቸሰኮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የአስከሬን ሽኝት መርሐግብር እየተካሄደ ሲሆን ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካዉያን

በሽኝቱ ላይ በመገኘት መልዕክት አስተላልፈዋል።ብፁዕ ካርዲናል አንተ ደግና ታማኝ አገልጋይ ና ወደተዘጋጀልህ ስፍራ ግባ በተባለው መሰረት ብፁዕ አባታችን ወደ ዘላለማዊ እረፍት ሄደዋል እኛም በሞታቸው ብናዝንም ወደሚወዱት አምላክ እና ወደ አምላክ እናት ጋር ስለሄዱ እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን ብለዋል። በዕለቱም የብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ፍራንቸሰኮስ የሀዘን መገለጫ መልዕክት በኢትዮጵያ የቫቲካን ኢምባሲ ዋና ጸኃፊ ቀርቧል። ክቡር አባ ተሾመ ፍቅሬ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጸኃፊ የመልዕክቱን የአማርኛ ትርጉም አስተላልፈዋል። ብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ፍራንቸሰኮስ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህልፈት ይተሰማቸውን ሀዘን ገለጸው

ለመላው ለአኢተ‍እዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት፣ ሊቀጳጳሳት፣ካህናት፣መነኮሳት እና ምዕመናን ሁሉ በዚህ ሃዘን በወንድምነት ከጎናቸው መሆናቸውን ገልጸዋል። እግዚአብሔር በቀኙ እንዲያኖራቸው እና ነፍሳቸውም የዘላለም እረፍት እንዲያገኝ እመኛለሁ ብለዋል።

የብፁዕነታቸው የቀብር ስነስርዓት በነገው እለት እንደሚፈጸም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በትላንትናው እለት በብጹዕ አቡነ ማርቆስ የጅማ ቦንጋ ሀገረስብከት የተመራ ቡድን ከክቡር አባ ተሾመ ፍቅሬ እና ክቡር አባ ገብርኤል ጋር በጋራ የሀዘን መግለጫቸውን በጽሁፍ አስፍረዋል።

12 March 2022, 09:07