ፈልግ

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተገኙት ምዕመናን በመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ላይ በተሳተፉበት ወቅት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተገኙት ምዕመናን በመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ላይ በተሳተፉበት ወቅት  (Vatican Media)

ካቶሊካዊ ድርጊት የሰላም እንቅስቃሴ አባላት በቴሌቪዥን ትርኢት ላይ መሳተቸው ተገለጸ

በካቶሊካዊ ድርጊት የሰላም እንቅስቃሴ ዘንድሮ በወሰደው ተነሳሽነት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተወሰዱ እርምጃዎችን አስመልክቶ በተዘጋጀው የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ የሕፃናት ቡድኖች እንዲመለከቱት መጋበዛቸው ታውቋል። "ሰላምን እንገምባ" በሚለው የዘንድሮ መሪ ሃሳብ ላይ በሮማ ሀገረ ስብከት የሚገኙ ቁምስናዎች መሳተፋቸው ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት በአውታረ መረብ አማካይነት የተካሄደው ካቶሊካዊ ድርጊት የሰላም ወር እሑድ ጥር 15/2014 ዓ. ም. በተፈጸመው የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት መጠናቀቁ ታውቋል። በቴሌቭዥን በኩል በየዓመቱ ሲቀርብ የቆየው "የሰላም ትርዕት" ወቅታዊ የጤና እና የደህንነት ደንቦችን መከበራቸውን ለማረጋገጥ "ሰላምን እንገንባ" በሚል ርዕስ መካሄዱ ታውቋል።

በሮም ሀገረ ስብከት ማህበራዊ ግንኙነት ቢሮ ድጋፍ የሚቀርብ የቴሌቪዥን ትርዕት በሮም ካቶሊካዊ ድርጊት እንቅስቃሴ ማኅበራዊ ሚዲያዎችም የሚሰራጭ ሲሆን በዝግጅቱ ሁለት ልጆች እንደሚሳተፉ ታውቋል። በዝግጅቱ ላይ የሮም ሀገረ ስብከት ረዳት ጳጳስ ብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ ዴ ዶናቲስ እና ካቶሊካዊ ድርጊት የሰላም እንቅስቃሴ ብሔራዊ ኃላፊ ወ/ሮ አናማሪያ ቦንጆ መሳተፋቸው ታውቋል።

በዝግጅቱ መካከል 55ኛውን ዓለም የሰላም ቀን ምክንያት በማድረግ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባስተላለፉትን መልእክት እና ሁሉም የሮም ሀገረ ስብከት ቁምስናዎች በተጋበዙት የሰላም መልዕክት ቪዲዮ ላይ ጥልቀት ጥናት መደረጉ ታውቋል። ዕለቱን ለማስታወስ አንድ ላይ ተሰፍቶ የተዘጋጀው ጨርቅ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ የሚሰቀል መሆኑ ታውቋል። በመቀጠልም ሁለት ወጣቶች ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የተላከውን ግልጽ ደብዳቤ ያነበቡ ሲሆን እንደተለመደው እኩለ ቀን ላይ ር. ሊ ጳ ፍራንችስኮስ በመሩት የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ላይ መሳተፋቸው ታውቋል።

ለሲኖዶሱ ጉዞ አስተዋጽኦ ለማድረግ

ለቴሌቪዥን ትርዕት ዝግጅት አንድ የልብስ ስፌት ሱቅ ታስቦ እንደነበር የገለጹት ሀገረ ስብከት ምክትል ኃላፊ አቶ አንቶኒዮ ኩላ፣ ልጆችን ስለ ሰላም ለማስተማር የጨርቅ መቁረጥ እና የስፌት ሥራ የበለጠ ተጨባጭ ሀሳብ የሚሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ አንቶኒዮ በማከልም የትርዕቱ ዋና ግቡ ወጣቶች በጓደኝነት ውቅት የሚከሰቱ ችግሮች ሊጠገኑ እንደሚችሉ ለማስገንዘብ እና ከኅብረተሰቡ መካከል ለሚገለሉ ብዙ ሰዎች ትኩረት እና እንክብካቤ ለመስጠት ቃል እንዲገቡ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል። ወጣቶች በሚሰጡት ክርስቲያናዊ ምስክርነት፣ የተለያዩ የጨርቅ ብጣሾች ለአዳዲስ ፈጠራዎች እንዴት ቁልፍ መሆን እንደሚችሉ ለማስረዳት መሆኑን አስረድተዋል።

ሕጻናት በዕለት ተዕለት ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ እንዴት የወንጌል ልኡካን መሆን እንደሚችሉ ለማሳሰብ እና በሲኖዶሳዊው ጉዞ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማድረግ ሲሆን፣ ሌላው  በሮም የሚገኝ ካቶሊካዊ ድርጊት የሰላም እንቅስቃሴ ሁለት የተግባር መርሃ ግብሮች እንዳሉት ገልጾ፣ የመጀመሪያው በጣሊያን ከሚገኝ ካቶሊዊ ድርጊት ብሔራዊ እንቅስቃሴ ጋር በመተባበር በካይሮ የሚገኘውን ሕጻኑ ኢየሱስ ማኅበር እና የሕጻናት መንከባከቢያ ማዕከል ግንባታን ለመደገፍ መሆኑ ታውቋል። 

26 January 2022, 16:28