ፈልግ

ታሊታ ኩም የተሰኘው ድርጅት በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠየቀ! ታሊታ ኩም የተሰኘው ድርጅት በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠየቀ! 

ታሊታ ኩም የተሰኘው ድርጅት በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠየቀ!

በአሁኑ ወቅት በበይነ መረብ አማካይነት እና በአካል የተካሄደ በሚገኘው ስብሰባ የተጠራው ሕግወጥ የሰዎች ዝውውርን በሚቃወመው ታሊታ ኩም በተሰኘው በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥር በሚተዳደረው ድርጅት አማካይነት ሲሆን በዚህ ስብሰባ ላይ ከሕግወጥ የሰዎች ዝውውር መረብ የተረፉ ሰዎች ፍትህ እንዲያገኙ፣ ሴቶችን ማብቃት፣ ህጋዊ የስደተኞች መንገዶችን መፍጠር እና የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ሰለባዎች እና በህይወት የተረፉ ሰዎች እንክብካቤ ማደረግ እና ኢኮኖሚያቸውን መደገፍ አስፈላጊነት ላይ እየተነጋገሩ እንደ ሆነ ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ዙሪያ ላይ የጋራ ጥረቶችን ማደረግ

ታሊታ ኩም የተሰኘው አለም አቀፍ  ድርጅት የበላይ ተቆጣጣሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ሲስተር ጆላንታ ካፍካ  ይህንን በአካል እና በበይነ መረብ አማካይነት ትላንት ኅዳር 16/2014 ዓ.ም የተከፈተውን አውደ ርዕይ አስመልክተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር "የድርጊት መርሃግብር" ወደ ዘር ወይም ተጨባጭ ሁኔታ መቀየሩ የታላቅ ሥራ ፍሬ ውጤት ነው ብለዋል። ዘር ከእግዚአብሔር መንግሥት ጋር የሚመሳሰል - አንድ ጊዜ ሲዘራ በቅሎ እና አብቦ ወፎች እንኳ የሚጠለሉበት ዛፍ ይሆናል ብለዋል።

ታሊታ ኩም ድርጅት ባልተቀናጀ መልኩ የተጀመረው ከብዙ አመታት በፊት ቢሆንም ቅሉ በአሁኑ ወቅት ከ90 በላይ በሚሆኑ ሀገራት ውስጥ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ሰለባዎችን በመንከባከብ ጠንካራ የሆነ ትስስር መፍጠሩን እና ለዚህ መብቃቱን አክለው ገልጸዋል። ሰዎችን ሕግወጥ በሆነ መልኩ ማዘዋወር ወንጀል በሰብአዊነት ላይ የተፈፀመ ትልቅ ወንጀል መሆኑን በመግለጽ፣ ህገወጥ ዝውውርን ለመዋጋት ባለስልጣናትን ጨምሮ ሁሉም ሰው “በከፍተኛ ደረጃ” ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ቁርጠኝነት እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ታሊታ ኩም ለተጎጂዎች የሚሰጠው አገልግሎት

የቫቲካን ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የታሊታ ኩም ማሕበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሲስተር ካፍካ የእንኳን ደህና መጣችሁ የመክፈቻ ንግግር ካደረጉ በኋላ እራሳቸው በበኩላቸው ባስተላለፉት መልእክት ሴቶች ሃይማኖታዊ እና ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ባጠቃላይ የኢየሱስን ጥሪ በተጨባጭ ምሕረትን፣ ፍትህን እና ተስፋን በማሳደድ የሰው ልጆችን ለማገልገል የረዥም ጊዜ ታሪክ እንዳላቸው አጉልቶ አሳይተዋል። ከእንደዚህ አይነት ምላሾች አንዱ ታሊታ ኩም የተሰኘው ድርጅት እንደ ሆነ የገለጹ ሲሆን የሕግወጥ የሰዎች ዝውውር ተጎጂዎችን፣ ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች እና ሌሎች በችግር ላይ ያሉ ሰዎችን ለመደገፍ በተልዕኮው ላይ እንደ ሆነ ገልጸዋል።

ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን አክለው እንደ ገለጹት ከሆነ ታሊታ ኩምን የእምነትን ምሥራች ወደ ዓለም የማድረስ ተልእኮወደ "የድርጊት መርሃ ግብር" እድቀይር እና እንዲነሳሳ አሳስበዋል። "ኢየሱስ የባርነትን እስራት ሰብሮአል፣ ሰውን ከኃጢአትና ከሞት በእውነት አድኗል” ያሉት ካርዲናሉ የእኛ የሁላችን ጥሪ " የመቤዠት፣ የመታደስ፣ የፍትህ፣ የምሕረት እና ተስፋ የማድረግ ልምድ ለሁሉም" የተሰጠ ተልዕኮ ነው ብለዋል።

ዮሴፍ እና መግደላዊት ማርያም

ካርዲናሉ የምሕረትን አስፈላጊነት እና ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘትን ለማስረዳት ከመጽሐፍ ቅዱስ ሁለት ታሪኮችን አስታውሰዋል።

በቅድሚያ የዮሴፍን ታሪክ ያስታወሱ ሲሆን የአባቱ ተመራጭ ልጅ ስለበረ በወንድሞቹ ላይ ቅናት እንዳደረባቸው እና በዚህ ምክንያት ተነሳስተው በወንድሞቹ ለባርነት ተሽጦ በኋላም እደታሰረ የገለጹት ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ሆኖም “ዮሴፍ በጌታ ላይ ያለው ተስፋ ወይም እምነት አልጠፋም” ነበር ብለዋል። እርሱ ከብዙ ስቃይ በኋላ ከፍተኛ ባለስልጣን ሆኖ የነበረ ቢሆንም ቅሉ ወንድሞቹ በሞት እንዲቀጡ የማደረግ ስልጣን ቢኖረውም ‘በራሱ ሕይወት የአምላክን ምሕረት በማየቱ’ የተነሳ ተመስጦ ምሕረትን አሳይቷል ብለዋል።

“የሚበድሉንን እና ፍትህን የምያጓድሉ ሰዎችን በሰውኛ አመለካከት ከማየት ይልቅ እነርሱን በእምነት እና በምሕረት አይን መመልከት በራሱ የቤተ ክርስቲያን ትንቢታዊ ድምጽ ነው ያሉ ሲሆን ይህ የማይቻል የሚመስል ነገር እውን ሊሆን የሚችለው ከእግዚአብሔር ጋር በመገናኘታችን የተነሳ ነው” ብሏል።

ከዚያም ካርዲናል ፓሮሊን በኢየሱስ ውስጥ “የፍቅር አባትና ወንድም ዓይኖች” ውስጥ የገባችውን የመቅደላዊት  ማርያምን ምሳሌ ያስታወሱ ሲሆን ይህቺ በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ የተገለጸችው ሴት ዝሙት አዳሪ መሆኗ እርግጠኛ ብንሆንም የመጽሐፍ ቅዱስ ወግ እንደሚነግረን ኢየሱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ባያት ጊዜ “እንደራሱ ልጅ እና እህት አድርጎ በመቁጠር ክብሯን ጠብቋል” በማለት ተናግሯል።

"በዚያን ቀን በማርያም ላይ የነበረው እይታ ልቧን ከመቀየር ባሻገር እና ክብሯን ሁሉ ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን የመጀመሪያውን ድንጋይ የሚወረውሩትን ወንዶች ልብም ለውጦታል" ያሉት ካርዲናል ፓሮሊን እሷም “የሐዋርያት ሐዋርያ” ሆና ቀጠለች - በመጀመሪያ “የክርስቶስን ትንሣኤ ምሥራች ሰበከችላቸው፤ ምክንያቱም እርስዋ ትንሣኤን አይታለችና በእርሱም ወደ አዲስ ሕይወት ስለተመለሰች እርሱን መመስከር ቀጥላ ነበር” ብለዋል።

"ይህ በጣም ብዙ ሰለባዎች እና በታሊታ ኩም ጥብቅና እና እንክብካቤ የተረፉ ሰዎች ያጋጠማቸው ገጠመኝ እና  መልእክት ለአለም መታወቅ አለበት" በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ካርዲና ፒዬትሮ ፓሮሊን ይህ ደግሞ “የቤተክርስቲያኗ ትንቢታዊ ድምጽ ልብ ነው። እንዲሁም በጋራ የአገልግሎት ጥሪ ውስጥ አብረውት የሚሠሩት የሁሉም ትንቢታዊ ድምፅ ነው” በማለት በአጽኖት ገልጸዋል።

ትንቢታዊ ድምፅ

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን በታሊታ ኩም ሥራ ላይ በማሰላሰል “መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ጋር በሚደረገው ሚስጥራዊ ግንኙነት ውስጥ በመገኘቱ የተጨቆኑ ሰዎች በወንድማማችነት እና በወንድማማችነት ግንኙነቶች የተጨቆኑ ሰዎች ክብር ሊመለስ ይችላል” በሚለው እምነት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመቀጠልም ታሊታ ኩም “ሰዎች በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች መረብ እጅ ውስጥ የመውደቅ አደጋ ላይ የሚጥሉ ስልታዊ ምክንያቶችን ይመለከታል፣ ቤተሰቦችን እና የአካባቢ ማህበረሰቦችን በአገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ካሉ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገው ግንኙነት አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል” ብለዋል።

"ዓለም በትክክል ሊሰማው የሚገባው ትንቢታዊ ድምጽ ነው" በማለት የገለጹት ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን "ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለዘመናዊ ባርነት መቅሰፍት በአገር ውስጥም ጭምር ምላሽ በሚሰጥበት መንገድ ላይ አስፈላጊ ለውጦችን እንዲያመጣ” ተግቶ መሥራት ይገባል ብለዋል።

የድርጊት መርሃ ግብሩ ጥሪ ሁሉንም ያካትታል

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ንግግራቸውን ከማጠቃለላቸው በፊት እንደ ገለጹት ሁሉም ሰው ማንኛውንም ዓይነት ግብዝነት ትቶ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር መረብን ለመበጠስ የሚደረገውን ርብርቦሽ አጠናክረው መቀጠል እንደ ሚኖርባቸው የገለጹ ሲሆን ሁላችንም እውነታውን መጋፈጥ ይኖርብናል ብለዋል።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን ንግግር በማስታወስ በአንድ በኩል በወንጀል ድርጅቶች ውስጥ በቀጥታ የሚሳተፉ እና መቅሰፍቱን የሚያባብሱ አንዳንድ ሰዎች አሉ ምክንያቱም “በአዲሱ የባርነት መንገድ ከፍተኛ ትርፍ ያገኛሉና” ብለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የፍጆታ ሰንሰለቱ የሚያልቅበት ቦታ ላይ ስላሉ ማውራት የማይፈልጉም አሉ “በወንዶች፣ ሴቶችና ሕጻናት ዘመናዊ ባርነት የተለወጡ ሰዎች እንደ መሆናቸው መጠን ስለጉዳዩ በድፍረት መናገር የማይፈልጉ ሰዎች አሉ” በማለት አክለው ገለጸዋል።

“የድርጊት መርሃ ግብሩ” የኃጢአትን እስራትና ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ባርነት ለመስበር በሚደረገው ጥረት ሁሉም እንዲተባበሩ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን “በሕግወጥ የሰዎች ዝውውር ውስጥ የተሳተፉ ሰዎችን ሕሊና እንዲያናውጥና ከዚህ በተቃራኒ ይህንን ድርጊት ለማስወገድ ሌላ መንገድ የሚመለከቱትን ሰዎች ሁሉ እንዲያበረታታ” ጸሎቴ ከእነርሱ ጋር ነው ብለዋል።

26 November 2021, 15:42