የቅድስት ቅድስት ክያራ ዘአሲዚ አመታዊ በዓል በመከበር ላይ ይገኛል የቅድስት ቅድስት ክያራ ዘአሲዚ አመታዊ በዓል በመከበር ላይ ይገኛል 

ቅድስት ክያራ ዘአሲዚ

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በነሐሴ 11/2021 ዓ.ም  የቅድስት ኪያራ አመታዊ በዓለ እየተከበረ ይገኛል። ቅድስት ክያራ እ.አ.አ በ1194 ዓ.ም ከመለድዋ በፊት ገና በእናትዋ ማኅፀን ውስጥ እያለች እናትዋ በቅዱስ ሩፊኖ ካተድራል ጸሎት ሲያሳርጉ “አንቺ ሴት ሆይ አትፍሪ! ለዓለም የምታበራ ንፅሕት ብርሃን ትወልጅያለሽ” የሚል ድምጽ ሰሙ። ልጅትዋ በተወለደች ግዜ እናቷ በሰማችው ድምጽ መሠረት ክያራ (ንፅሕት) ብላ ሰየመቻት፣ ልታስጠምቃትም ከዚህ ቀደም ልጇ ከመገላገሏ በፊት በምትጸልይበት ወቅት ድምጽ ወደ ሰማችበት ካተድራል ወሰደቻት፣ ሕፃን ክያራ በጥሩ አስተዳደግ ካደገችና ከተማረች በኋላ በቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘአሲዚ ስብከት የነበራትን ሁሉ እርግፍ አርጋ በመተው እንደ ጌታ ቃል ለመኖርና ቃሉን በፍጹም ለማስተንተን ከቤተሰቦችዋ በቅዱስ ዳምየን ቤተክርስትያን ተደብቃ ብዙ ጊዜ ካሳለፈች በኋላ ሁሉ አልፎ ገዳም መሠረተች፣ በዚሁ መጠግያዋ በነበረው የቅዱስ ዳምያን ቤተ ክርስትያን “የድሆች አገልጋይ ደናግላን ማሕበር” በሚል መጠሪያ የደናግላን ማሕበር መሠረተች፣ ገዳሙ ከዛ በኋላ ለተቆረቆሩ ገዳሞችዋ መሪ ሆነ፣ ቅድስት ክያራ ከሞተች በኋላ የገዳሙና የደንግሎቹ ማኅበር ስም “ክላሪሰ” የሚል ሆነ፣ ቅድስት ክያራ በዚሁ ገዳም ለ42 ዓመታት ኖረች፣ ብዙ ጤናም አልነበራትም፣ እ.አ.አ በ1215 ዓም ላይ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ የግዳሙ እመምኔት እንድትሆን ቅድስት ክያራን በመሾም የመጀመርያ የሆነውን የገዳም ደምብም ሰጣቸው፣ እ.አ.አ በ1253 ዓም ማኅበሩ በቤተ ክርስትያን ተቀባይነት አግኝቶ ር.ሊ.ጳ ኢንቸንሶ 4ኛ በአዋጅ አጸደቁት፣ ቅድስት ክያራም ከ2 ቀናት በኋላ እ.አ.አ በነሐሴ 11/1253 ዓም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች፣ ከሁለት ዓመታት ብኋላ እ.አ.አ በ1255 ዓም የቅድስና ማዕረግ በማግኘት ቅድስት ተባለች።

11 August 2021, 11:26