ካሪታስ - የተቀናጀ ሥነ ምህዳር ለአየር ንብረት ቀውስ መፍትሄ ነው ማለቱ ተገለጸ። ካሪታስ - የተቀናጀ ሥነ ምህዳር ለአየር ንብረት ቀውስ መፍትሄ ነው ማለቱ ተገለጸ። 

ካሪታስ - የተቀናጀ ሥነ ምህዳር ለአየር ንብረት ቀውስ መፍትሄ ነው ማለቱ ተገለጸ።

የዓለም የሰብአዊነት ቀን እ.አ.አ በነሐሴ 19/2021 ዓ.ም ሐሙስ እለት ሲከበር ካሪታስ ኢንተርናሽናል በመባል የሚታወቀው በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጥላ ሥር የሚተዳደረው የግብረ ሰናይ ድርጅት ባስተላለፈው መልእክት የተቀናጀ የስነ ምዕዳር እና የሰውን ልጅ ማዕከል ያደረገ በሁሉም ውሳኔዎች እና ድርጊቶች መካከል የሰው ልጅ ሊጫወተው የሚችለውን ሚና በማጉላት መሥራት እንደ ሚገባ የገለጸ ሲሆን ይህንን በተቀናጀ መልኩ ተግባራዊ በምናደርግበት ወቅት በሰው ልጆች ላይ የሚታየውን የአየር ንብረት ቀውስ ለመፍታት ይረዳል በማለት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የዓለም የሰብአዊነት ቀን በየዓመቱ እ.አ.አ. ነሐሴ 19 ቀን ይከበራል። የሰብአዊነት ተግባራትን በማከናወን ላይ በነበሩበት ወቅት ሕይወታቸውን ያጡትን ሁሉንም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ለማክበር ታልሞ የተቋቋመ ቀን ነው።

በዚህ ዓመት ይህ ዓመታዊው ቀን የተከበረው በአየር ንብረት ቀውስ ጭብጥ ዙሪያ በማትኮር ሲሆን የፖለቲካ መሪዎች በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ትርጉም ያለው እርምጃ እንዲወስዱ እና በዓለም ላይ በጣም ተጋላጭ የሆኑትን ሰዎች እንዲጠብቁ በማድረግ የዚህ ቀውስ ከፍተኛ እና አስቸኳይ ተግዳሮቶችን እንዲያጎሉ በዓለም ዙሪያ አጋሮችን ይጋብዛል።

የአየር ንብረት ድንገተኛ አደጋ በዓለም ዙሪያ የሰብአዊ ማህበረሰብ እና ሰዎች በግንባር መስመሮቹ ላይ በቀላሉ ሊቆጣጠሩት በማይችሉት መጠን ላይ በሚገኙበት በአሁኑ ሰዓት እ.አ.አ በነሐሴ 19/2021 ዓ.ም የተከበረው የዓለም የሰብአዊነት ቀን ይህንን በሰው ልጅ ላይ የሚደርሰውን ትልቁን አደጋ ለመዋጋት የጋራ ፣ የተቀናጀ እርምጃ አስፈላጊነትን በማጉላት ተዘክሮ ማለፉ ተገልጿል።

ፈታኝ ሁኔታዎችን የሚጋፈጥ ዓለም

በዚህ ዓመት ጭብጥ መንፈስ ፣ ካሪታስ ኢንተርናሽናል ከአየር ንብረት ለውጥ ፣ ወረርሽኙ እና ከሚያስከትላቸው መዘዞች እና በአፍጋኒስታን እና በሊባኖስ የፖለቲካ ውዝግብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለመፍታት ደፋር እርምጃዎች እንዲወስዱ አሳስቧል። በአሁኑ ወቅት አገሪቱ በተከሰተው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ትርምስ ውስጥ በአሁኑ ወቅት በምትገኝበት ከዚህ በተጨማሪም በቅርቡ በሬክተር እስኬል መለኪያ በ 7.2 ያስመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከፍተኛ ችግር ውስጥ በምትገኘው በሄይቲ ውስጥ ይህ የቤተክርስቲያን የእርዳታ ድርጅት እንዲሁ የተቻለውን ሁሉ በማደረግ የአገሪቷን ሕዝቦች በማገዝ ላይ እንደ ሚገኝ የገለጸ ሲሆን ሌሎችም ግብረ ሰናይ ተቋማት ይህንን ችግር ከግምት ባስገባ መልኩ ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ድርጅቱ ጥሪ አቅርቧል።

በተጨማሪም ከፍተኛ በሆነ የሙቀት ሞገዶችን ፣ አውዳሚ አውሎ ነፋሶችን ፣ ጎርፍን ፣ የአየር ሁኔታ መለወጥ እና እ.አ.አ. በ 2021 ዓ.ም ውስጥ በተለያዩ አከባቢዎች የተከሰቱትን የሰደድ እሳት ያስከተላቸውን የደን ቃጠሎዎችን ዓለም እየተጋፈጠ እንደ ሆነ ካሪታስ ኢንተርናሽናል የተባለው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የእርዳታ መስጫ ድርጅት በመልእክቱ የገለጸ ሲሆን እነዚህ ሁሉ ለአከባቢው እንክብካቤ በአግባቡ ባለመደረጉ የተነሳ የተፈጠሩ ናቸው ፣ ይህም ለአየር ንብረት ለውጥ እና ሥነ ምህዳራዊ ቀውስ ያስከትላል፣ እያስከተለም ይገኝል ብሏል።

የበጎ አድራጎት ድርጅቱ በድርጅቱ ድረ ገጽ ላይ ባወጣው መግለጫ “እጅግ በጣም ድሃ በሆኑ አገራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የተፈጥሮ አደጋዎች እንዲሁ የሰዎችን ሕይወት ለመጠበቅ ፣ ለመከላከል እና ለማዳን ቆራጥ እና የተቀናጀ የፖለቲካ እርምጃ እንዲደረጉ ጥሪ እናቀርባለን” ሲል አመልክቷል። የሰው ልጅ በከፊሉ ሲሰቃይ  መላው የሰው ቤተሰብም እንዲሁ ይሰቃያል ” በማለት አክሎ ገልጿል።

ተጨባጭ እርምጃ

ካሪታስ ኢንተርናሽናል የተሰኘው የካቶሊክ እርዳታ መስጫ ድርጅት አክሎ እንደ ገለጸው ከሆነ ተግባራዊ እርምጃዎችን ሲያቀርብ ፣ የፖለቲካ መሪዎችን የአፍጋኒስታንን ህዝብ ደህንነት እና ለሊባኖስ ህዝብ መሰረታዊ ፍላጎቶችን እንዲያቀርቡ ጥሪ ያቀርባል። በዚህ ረገድ መንግስታት የኑሮአቸውን እና የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ በግብርናም ሆነ ግብርና ባልሆነ መልኩ በሚተዳደሩ ማህበረሰቦች ላይ የተመሰረቱ የልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ እንዲሳተፉ በቂ ገንዘብ በመመደብ የአከባቢውን ማህበረሰቦች እንዲደግፉ አሳስቧል።

በተጨማሪም የበጎ አድራጎት ድርጅቱ የአካባቢ ማህበረሰቦችን በሰብአዊ ርምጃ ውስጥ ተሳትፎን ያበረታታል እና ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ ማህበረሰቦች ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉትን አደጋዎች በቅድሚያ ለመከላከል ይችላ ዘንድ በአደጋ ቅነሳ ተግባራት ላይ በመሳተፍ እና በቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶች በኩል ደህንነትን ማረጋገጥ ይፈልጋል በማለት በመግለጫው አክሎ ገልጿል። ይህንን ለማረጋገጥ የአከባቢ መስተዳድሮች የምላሽ ስልቶቻቸውን ለማጠናከር ከአከባቢው ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና በእምነት ላይ ከተመሠረቱ ቡድኖች ጋር እንዲተባበሩ ተጋብዘዋል።

ካሪታስ ለበሽታዎች ክትባትን ጨምሮ በጣም ተጋላጭ ለሆኑት መሠረታዊ የተቀናጀ የጤና እንክብካቤ ተደራሽነትን የማረጋገጥ አስፈላጊነትን ያጎላል። እናም የአለም ሙቀት መጨመር ተፅእኖን እና የስነ -ምህዳር መበላሸትን ለመቀነስ ለኢኮኖሚ እና ለኢንዱስትሪ ዓለም አቀፍ ፖሊሲዎች ቁርጠኛ እንዲሆኑ ያሳስባል።

የተቀናጀ ሥነ ምህዳር መፍትሔ ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ካላቸው አቋም ጋር በመስማማት ፣ ካሪታስ ኢንተርናሽናል ለአየር ንብረት ቀውስ ብቸኛው ተገቢ ምላሽ ሥነ ምህዳር መፍትሔ ማምጣት ነው ያለ ሲሆን እንዲሁም “የሰው ልጅ ፍላጎትና ክብር በሁሉም እንቅስቃሴዎች እና ውሳኔዎች ማዕከል” ላይ መሆኑን እንዳለበት አስታውሷል። በ 200 ሀገሮች እና ግዛቶች ውስጥ ከመሠረታዊ ማህበረሰቦች ጋር አብረው የሚሰሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች አባላት አውታረ መረብ “በእነዚህ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ቀውሶች ምክንያት የተከሰቱ እስከ ዛሬ ድረስ የማይታወቁ ስቃዮችን” ለዓለም ይፋ ለማደረግ አብክረው እይሰሩ መሆኑን ካሪታስ ኢንተርናሽናል አክሎ ዘግቧል።

20 August 2021, 14:03