ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ቤርቶሎሜዎስ ቀዳማዊ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ቤርቶሎሜዎስ ቀዳማዊ  

ፓትሪያርክ ቤርቶሎሜዎስ፣ ለአደጋ የተጋጠ አካባቢያችንን ከጉዳት መጠበቅ ያስጋፈልጋል አሉ

የቆንስጣንጢንያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ቤርቶሎሜዎስ ቀዳማዊ ለጣሊያን መንግሥት ፕሬዚደንት ለክቡር አቶ ሴርጆ ማታሬላ በላኩት መልዕክት “የዛሬዎቹ ሰዎች የፕላኔቷ ገዥዎች ሊሆኑ አይችሉም በማለት የጋራ መልእክታችንን እናስተላልፋለን” ብለዋል። የጣሊያን ደሴት በሆነችው ሳርደኛ የተቀጣጠለው የሰደድ እሳት በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ያስከተለውን ጥፋት አስታውሰው በአደጋው ለተጎዱት በሙሉ ብርታትን ተመኝተውላቸዋል። የሰደድ እሳቱ በሌላኛዋ የጣሊያን ደሴት ሲሲሊያም መቀጣጠሉ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በሳርደኛ ደሴት ላይ እሳቱ ባስከተለው ጥፋት ሐዘናቸውን የገለጹት ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ቤርቶሎሜዎስ ቀዳማዊ፣ የግል ጥቅማቸውን ብቻ የሚፈልጉ ግድ የለሽ ሰዎች በአካባቢ ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት መከላከል ያስፈልጋል ብለዋል። ለጣሊያን ፕሬዚደንት ለክቡር አቶ ሴርጆ ማታሬላ በላኩት መልዕክት በሳርደኛ የተነሳው ኃይለኛ የሰደድ እሳት በንግድ ተቋማት፣ በእንስሳት እና በአካባቢው ለ70 ዓመታት ያህል ጥበቃ ሲደረግለት በቆየው አካባቢያዊ ንብረት ላይ ያደረሰው ጥፋት ያሳዘናቸው መሆኑን ገልጸዋል።    

በሰው ሕይወት እና በፍጥረት እንክብካቤ መካከል ያለው ግንኙነት

በጣሊያን መንግሥት ከፍተኛ እውቅና ያላአውን ሽልማት ከፕሬዚደንት ሴርጆ ማታሬላ የተሸለሙት የቆንስጣንጢንያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ቤርቶሎሜዎስ ቀዳማዊ በቤተክርስቲያናቸው ድረ-ገጽ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት የእሳት አደጋው ቶሎ እንዲቆም፣ በአካባቢ ጥበቃ ላይ ለተሰማሩት በሙሉ ፈጣሪ ብርታትን እንዲሰጣቸው በማለት በጸሎታቸው አስታውሰዋል።     

ቅዱስነታቸው አክለውም አካባቢው ለጥፋት የተጋለጠበት ምክንያት በሰዎች የተሳሳተ አስተዳደራዊ ውሳኔ እና ስግብግብነት በመሆኑ እናወግዘዋለን ብለው፣ ዛሬም ቢሆን በሰው እና በጋራ መኖሪያ ቤታችን ጥበቃ መካከል ያለውን ግንኙነት በደንብ ለመረዳት እየተሞከረ እንደሚገኝ፣ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምሁራን ሥነ-ምህዳራዊ ለውጥን ለማምጣት ብለው የአከባቢ ጥበቃን የሚመለከቱ ጥናቶችን ከሠላሳ ዓመታት በላይ ሲያካሂዱ መቆየታቸውን አስታው፣ ለዚህ ዕላማ ሲባል በየዓመቱ ስብሰባዎች እና ዝግጅቶች መደረጋቸውን ገልጸዋል።

ፓትሪያርኩ እ. አ. አ ከ1980 ዎቹ ጀምሮ የአካባቢ ጥበቃን ሲደግፉ ኖረዋል

ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ቤርቶሎሜዎስ ቀዳማዊ “ወንድሜ!” ብለው የሚጠሯቸው ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ አስፈላጊነትን በማስመልከት “ውዳሴ ላንተ ይሁን” የሚል ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን እ. አ. አ በ2015 ዓ. ም. ይፋ ማድረጋቸው እና በየዓመቱ ተፈጥሮን ለማስታወስ በወሰኑበት መስከረም 1 የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምዕመናንም በተመሳሳይ ዕለት በጸሎት ሲተባበሩ መሆኑ ታውቋል።

“እኛ የፕላኔቷ ፍጹም ገዥዎች አይደለንም”

ብጹዕ ወቅዱስ ቤርቶሎሜዎስ ቀዳማዊ ለጣሊያን መንግሥት ፕሬዚደንት ለክቡር አቶ ሴርጆ ማታሬላ በላኩት መልዕክት፣ በተፈጥሮ አከባቢ እና በሰው ልጅ መካከል ያለው መደጋገፍ ለመጪው ትውልድ በሚተላለፈው ዓለም ላይ ያለውን ተጠያቂነት የሚገልጽ ነው ብለዋል። በዚህ ግንዛቤ መሠረት ፣ የዘመናችን ሕዝቦች በሙሉ “የዛሬ ሰዎች የፕላኔታችን ፍፁም ገዥዎች አይደሉም” የሚለውን መልእክት ማስተላለፍ ካልቻልን በዓለማችን ላይ ለሚደርስ መከራ ለመቅመስ እንገደዳለን” በማለት አስጠነቅቀዋል።

04 August 2021, 18:27