የክርስቶስ መስቀል የተስፋችን መብራት ነው! የክርስቶስ መስቀል የተስፋችን መብራት ነው! 

የክርስቶስ መስቀል የተስፋችን መብራት ነው!

አሁን የምንገኝበት ቅዱስ በሆነው በሕማማት ሳምንት ውስጥ ሲሆን በመንፈሳዊ ሁኔታ ውስጥ ገብተን እኛ በፋሲካ በዓል በሚከናወኑ 3 አበይት ተግባራት ማለትም የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማት፣ ሞት እና ትንሣኤ በምናክብርበት ዋዜማ ላይ እንገኛለን። ከነገ ጀምሮ እስከ እሁድ የጌታን የሕማማት ፣ የሞት እና የትንሳኤውን ምስጢር በማክበር የሚደረጉትን የስርዓተ አምልኮ ማዕከላዊ ቀናት እንናከብራለን። እናም መስዋዕተ ቅዳሴን በተሳተፍን ቁጥር ይህንን ምስጢር በድጋሚ በማሰብ እንኖራለን። ወደ መስዋዕተ ቅዳሴ ስንሄድ ለመጸለይ ብቻ አይደለም የምንሄደው፣በፍጹም እንዲህ አይደለም፣ የምንሄደው ወደ ምስጢር ማለትም ወደ ፋሲካ ምስጢር እንደገና ለማግባት እና ለማደስ ነው። ይህንን መገንዘብ በጣም አስፈላጊ ነው። ወደ ቀራንዮ መሄድ ያለብን ያህል ተሰምቶን በተመሳሳይ ጊዜም እምነታችንን ለማደስ የፋሲካን ምስጢር እንደ ገና ለማምጣት ነው መስዋዕተ ቅዳሴን የምንሳተፈው።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን  

በጸሎተ ሐሙስ ምሽት ላይ ወደ ፋሲካ የመጀመሪያው ምስጢር በመግባት ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻ ራት የበላበትን ምሽት በማስታወስ የሚከናወነውን መስዋዕተ ቅዳሴ እንካፈላለን። ይህ አጋጣሚ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ በቅዱስ ቁርባን ውስጥ የፍቅሩን ቃል ኪዳን በመግለጽ፣ ይህንን ማከናወን የሚገባቸው ለማስታወሻ ቢቻ ሳይሆን ነገር ግን ለመታሰቢያ እንደ ዘላለማዊ ህልውናው አድርገው እንዲያከብሩት ቃል የገባበት ምሽት ነው። መጀመሪያ ላይ እንዳልኩት መስዋዕተ ቅዳሴን በምንካፈልበት ወቅት ሁሉ የመበዤታችንን ምስጢር እንደ ገና እናድሳለን። በዚህ ቅዱስ ቁርባን ውስጥ ኢየሱስ የመሥዋዕቱ ሰለባ የነበረውን በግ በራሱ ይተካዋል። ሥጋው እና ደሙ ከኃጢአትና ከሞት ባርነት እንድንድን ያደርገናል። ከእያንዳንዱ የባርነት ዓይነት መዳን የሚያስችለን ጸጋ በዚያ ይገኛል። የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ እንዳደረገው እርስ በርሳችን አንዳችን ለአንዳችን አገልጋይ በመሆን እርስ በርሳችን እንድንዋደድ የጠየቀበት ምሽት ነው፣ በመስቀል ላይ የሚፈሰውን ደም አስቀድሞ የሚገልጽ ምልክት ነው። በእውነት ጌታ እና አምላክ የሆነው እርሱ በሚቀጥለው ቀን እግሮቻቸውን ሳይሆን ፣ የደቀ መዛሙርቱን ልብ እና መላ ህይወት ለማፅዳት ይሞትላቸዋል። በዚያ የመሥዋዕትነት አገልግሎት ሁላችንን አድኖናልና ለሁላችንም የአገልግሎት መባ ሆኖልን ነበር። 

ስቅለተ አርብ የንስሐ ፣ የጾም ፣ የጸሎት ቀን ነው። በቅዱሳት መጻሕፍት ንባባት እና በስርዓተ አምልኮ በሚደረጉ ጸሎቶች ፣ ቤዛ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን  ሥቃይ እና ሞት ለማስታወስ እኛም ብንሆን በቀራንዮ እንደሆንን አድርገን እንሰበስባለን። በአምልኮ ሥርዓቱ ከፍተኛነት ፣ በስርዓተ አምልኮ አከባበር በኩል ፣ በመስቀሉ እንድናመልከው ቀርቦልናል። ክቡር የሆነውን መስቀሉን በምናከብርበት ወቅት ለድነታችን የተሰዋውን ንጹዕ የሆነውን በግ ጉዞ በሕይወት እንኖራለን ፡፡ እኛ የታመሙትን ፣ ድሆችን ፣ በእዚህ ዓለም ውስጥ የተጣሉትን ስቃየተኞች በአእምሯችን እና በልባችን ውስጥ እንሸከማለን ፣ “የተሠውትን በጎች” ፣ በጦርነት ፣ በአምባገነናዊ አገዛዞች ፣ በዕለት ተዕለት ዓመፅ ፣ ፅንስ በማስወረድ ሰላባ የሆኑ ንፁሃን ሰዎችን እናስባለን።  በተሰቀለው የእግዚአብሔር አምሳል ፊት እኛ በኛ ውስጥ የተሰቀሉትን ብዙዎችን በጸሎት እናስታውሳቸውለን፣ በመከራቸው ውስጥ መጽናናትን እና ትርጉምን የሚቀበሉት በእርሱ ብቻ ነው፣ እናም በአሁኑ ጊዜ በዘመናችን እነዚህን የመሰሉ ብዙዎች አሉ ፣ በዘመናችን እየተሰቀሉ የሚገኙ ሰዎችን መርሳት አይገባንም፣ እነሱም የተሰቀለው የኢየሱስ አምሳል ናቸው፣ እናም ኢየሱስ በውስጣቸው እንዳለ ልናምን ይገባል። 

ኢየሱስ የሰው ልጆችን ቁስል እና ሞት የራሱ ቁስል እና ሞት አድርጎ ወደ ራሱ ከወሰደበት ጊዜ አንስቶ የእግዚአብሔር ፍቅር እነዚህን የመሳሰሉ ምድረ በዳችንን በማረስረስ ጨለማችንን አብርቶልናል። ምክንያቱም ዓለም በጨለማ ውስጥ ናትና። እስቲ በዚህ ቅጽበት እየተካሄዱ ያሉትን ጦርነቶች ሁሉ በዝርዝር እንመልከት፣ በረሃብ የሚሞቱትን ልጆች ሁሉ እንመልከት፣ የትምህርት አገልግሎት የሌላቸውን ልጆች እናስብ፣  በጦርነቶች ፣ በሽብርተኝነት የጠፋው አጠቃላይ ህዝብ እናስብ። ከብዙዎች በትንሹ የተሻሉ ሰዎች ደግሞ ትንሽ የተሻለ ስሜት እንዲሰማቸው ብቻ ለማድረግ አደንዛዥ ዕፅ የሚያስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ፣ ይህንን የመሰለ ገዳይ የሆነ ጉዳይ ኢንዱስትሪ የሚያቀላጥፉ ሰዎችም አሉ። ሁሉንም ዶግ አመድ የሚያደርግ ጥፋት ነው! የተሻሉ የመሆን ምኞትን በልባቸው ውስጥ ያነገቡ የክርስቲያን እና እንዲሁም የሌሎች እምነት ተከታዮች የሆኑ የእግዚአብሔር ሰዎች የሆኑ ነገር ግን እንደ ትናንሽ “ደሴቶች” የሆኑ ሰዎች አሉ። ነገር ግን እውነቱን እንናገር፣ በዚህ የሞት ቀውስ ውስጥ በደቀ መዛሙርቱ ውስጥ የሚሠቃየው ኢየሱስ ራሱ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ በአገልግሎቱ ሕይወትን፣ ፈወስን ፣ ይቅርታን እነዚህን የመሳሰሉ ነገሮችን ያከናወነ ሲሆን አሁን በመስቀል ላይ በከፈለው ከፍተኛ መስዋእትነት በአባቱ የተሰጠውን አደራ ወደ ፍጻሜው ያመጣዋል፣ በእዚህ አለም የሚገኙ መከራዎችን እና ስቃይ ለመለወጥ ወደ እዚህ ዓለም ፈተናዎች ውስጥ ይገባል፣ ወደ መከራ ገደል ውስጥ ይገባል። እንዲሁም እያንዳንዳችንን በኩራት መንፈስ ከገባንበት ጨለማ፣ ኩራት እኛን ከከተተበት ጨለማ እኛን በማውጣት እግዚአብሄር ወደ ሚወደው ብርሃን ያሻግረናል። ይህንን እንድናደረግ የሚገፋፋን ደግሞ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው። “በእሱ ቁስል እኛ ተፈወስን” (1 ጴጥሮስ 2: 24 ን ተመልከቱ) ፣ ሐዋርያው ጴጥሮስ እንደሚናገረው ፣ በሞቱ ሁላችንም እንደ ገና ተወልደናል። እናም ለእርሱ ምስጋና ይግባውና ሁሉም ኃጢያታችን በእርሱ መስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗል፣  ማንም በሞት ጨለማ ውስጥ ዳግመኛ ብቻውን አይኖርም። በጭራሽ እርሱ ሁል ጊዜ ከእኛ ጋር ነው፣ ልባችንን ከፍተን እራሳችንን በእርሱ እንድንመለከት ብቻ ያስፈልገናል ፡፡

በኢየሱስ አሳፋሪ ሞት የደነገጡ ሰዎች በቅዳም ሱር ወይም ከስቅለተ ዐርብ ቀጥሎ ባለው ቅዳሜ ቀን የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት በሐዘን እና ግራ መጋባት ውስጥ መኖራቸውን ለማሳየት በማሰብ በዝምታ ያሳለፉት ቀን የሚታሰብበት እለት ነው። ዓለም ዝም ሲል፣ ሕይወት በመቃብር ውስጥ ሆኗ ጸጥ ሲል፣ በእርሱ ተስፋ ያደረጉ ሰዎች ለከባድ ፈተና ሲዳረጉ፣ ወላጅ አልባ ልጆች እንደሆኑ ሆኖ ሲሰማቸው፣ ምናልባትም እግዚአብሔር መከታ ያልሆናቸው ልጆች ሆነው ሲሰማቸው .. . እነዚህን የመሳሰሉ ነገሮችን የምናሰላስልበት ወቅት ነው። ይህ በዝምታ የምናሳልፈው እለተ ቅዳሜ የማርያም ቀን ጭምር ነው፣ እሷም በእንባ ኖራለች ልቧ ግን በእምነት ፣ በተስፋ ፣ በፍቅር ተሞልቷል። የኢየሱስ እናት የልጇን የሐዘን ጎዳና ተከትላ በመስቀሉ ስር ነፍሷ በሐዘን ስይፍ ተወግቶ በእዚያው ነበረች። ነገር ግን ሁሉም ነገር ያበቃለት በሚመስልበት ጊዜ እንኳን ሙታንን በሚያስነሳው በእግዚአብሔር እመንት ላይ ተስፋዋን በማድረግ ነቅታ ትጠባበቅ ነበር። ስለዚህ ዓለም በሚጨልምበት ሰዓት ውስጥ ፣ የአማኞች እናት ፣ የቤተክርስቲያን እናት እና የተስፋ ምልክት ሆና ብቅ አለች። እያንዳንዳችን የምንሸከመው መስቀል እጅግ በጣም ከባድ ሆኖ በሚሰማን ወቅት ሁሉ የእርሷን የእመንት ምስክርነት እና አማላጅነት መማጸን ይኖርብናል። 

ኢየሱስ አርብ እለት ተሰቃይቶ፣ ሞቶ ከተቀበረ በኋላ ባለው የቅዳሜ እለት ጨላማ ውስጥ የገባን ሲሆን በፋሲካ በዓል ዋዜማ በሚደረጉ የአምልኮ ስነ ስርዓቶች ደግሞ በደስታ እና በብርሀን ተሞልተን በመጨረሻው ምሽት የሀሌሉያ ዝማሬን በመዘመር ከሙታን መነሳቱን እናበስራለን። ከተነሳው ክርስቶስ ጋር በእምነት የሚደረግ ገጠመኝ ይሆናል ፣ እናም መንፈስ ቅዱስ እስኪመጣ ድረስ የትንሳኤ ደስታ በሚቀጥሉት ሃምሳ ቀናት ውስጥ ይቀጥላል። የተሰቀለው ተነስቷል! ሁሉም ጥያቄዎች እና አለመተማመኖች ፣ ማመንታት እና ፍርሃቶች በዚህ ራዕይ ተወግደዋል። ከሙታን የተነሳው ጌታ መልካም ምሳሌ፣ መልካም ነገር በክፉ ነገር ላይ አሸናፊ ሆኖ እንደ ሚወጣ፣ ሕይወት ሁል ጊዜ ሞትን እንደሚያሸንፍ እርግጠኛ እንድንሆን ያደርገናል፣ እናም በትህትና ዝቅ ብለን ሐዘን መጨረሻችን እንዳልሆነ ተገንዝበን፣ ይልቁንም ወደ ላይ ከፍ የሚያደርገን የእግዚአብሔር ፍቅር እንደ ሆን እንድንረዳ የሚያደርገን ፍቅር መያዝ ይኖርብናል። ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ ሁሉም ነገር ትክክል መሆኑን የማረጋገጫ ምልክት ነው-ከሞት በኋላ ሕይወት እና ከኃጢአትም በላይ ይቅርታ ለእኛ እንደ ሚሰጥ አረጋገጠልን።፡ ደቀ መዛሙርቱ ተጠራጠሩ ፣ አላመኑም ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ያመነቺው እና ያየችው መግደላዊት ማርያም ነበረች፣ በስሟ የጠራትን ኢየሱስን እንዳየች ለማሳወቅ የሄደች የትንሳኤ ሀዋርያ ነበረች። እናም ከእዚያ በኋላ ነበር ደቀ መዛ ሙርቱ ሁሉ ይህንን ነገር ያዩት። ነገር ግን  እዚህ ላይ አንድ ጊዜ ቆም ለማለት እፈልጋለሁ .. . ደቀ መዛሙርቱ እንዳይመጡ እና ሬሳውን እንዳይወስዱ መቃብሩን ሲጠብቁ የነበሩ ጠባቂ  ወታደሮች ኢየሱስን አዩት፣ በሕይወት እንዳለ እና እርሱ ከሙታን እንደ ተነሳ ተመልክተው ነበር።  ጠላቶቹ አዩትና እንዳለዩ ሆነው አለፉት። ለምን? ምክንያቱም ተከፍለዋቸው ነበርና።  ኢየሱስ በአንድ ወቅት የተናገረው እውነተኛው ምስጢር እዚህ ላይ እናገኘዋለን “በዓለም ላይ ሁለት ጌቶች አሉ ፣ ሁለት ፣ ከዚያ በላይ የለም፤ እግዚአብሔር እና ገንዘብ። ገንዘብን የሚያገለግል ሰው የእግዚአብሔር ተቃዋሚ ነው”፡፡ እናም እውነታን የቀየረው ገንዘብ እዚህ አለ። እነሱ የትንሳኤን አስደናቂ ነገር አይተው ነበር ፣ ነገር ግን ዝም እንዲሉ ተከፍለዋቸው ነበር። ክርስቲያን የሆኑ ወንዶችና ሴቶች የክርስቶስን ትንሣኤ በተግባር እንዳይመሰክሩ የተከፈላቸው ብዙ ጊዜዎችን እናስብ፤ እንደ ክርስቲያን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድናድረግ የጠየቀን ነገር ይህ አይደለም። 

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ እንደገና በዚህ አመት የፋሲካ በዓላትን ከወረርሽኙ ሁኔታ አንፃር ነው የምናከብረው።  በብዙ የመከራ ሁኔታዎች ውስጥ ፣ በተለይም እነሱ ቀድሞውኑ በድህነት ፣ በአደጋዎች ወይም በግጭቶች በተሞከሩ ሰዎች ፣ ቤተሰቦች እና ሕዝቦች በሚሸከሟቸው ጊዜ የክርስቶስ መስቀል በአውራ ጎዳና ላይ አሁንም ለሚንሳፈፉ መርከቦችን ወደቡን የሚያመላክት መብራት ነው ። የክርስቶስ መስቀል ተስፋ የማይቆርጥ የተስፋ ምልክት ነው፣ እናም በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ የሌለ ሰው ስለሌለ አንዲት እንባ እንኳን በከንቱ እንደ ማትቀር፣ አንድም ትንፋሽ እንደ ማትጠፋ ይናገረናል። ጌታን እርሱን የማገልገል እና እርሱን የምናውቅበት ጸጋ እንዲሰጠን እና እሱን ለመርሳት እንዳይከፈለን ይረዳን ዘንድ ጸጋውን እንጠይቅ።

29 April 2021, 08:51