ፈልግ

የአውሮፓ ሕብረት ሰንደቅ ዓላማ የአውሮፓ ሕብረት ሰንደቅ ዓላማ 

የአውሮፓ ብጹዓን ጳጳሳት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ በስደት እና በሐይማኖት ነፃነት ላይ ውይይት አካሄዱ

የአውሮፓ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት በአውታረ መረብ አማካይነት ከመጋቢት 8 - 9/2013 ዓ. ም. ድረስ በሚያካሂዱት የሁለት ቀን ስብሰባ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን፣ ስደትን እና በአውሮፓ ውስጥ የሐይማኖት ነፃነት በሚሉ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ ወይይት የሚያደርጉ መሆኑ ታውቋል። በብጹዓን ጳጳሳቱ ስብሰባ ላይ የአውሮፓ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ማርጋሪቲስ ሺነስም ተገኝተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በዓለማችን ውስጥ የኮሮና ቫይረስ በታየ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ለ2.5 ሚሊዮን ሰዎች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሕይወታቸውን ማጣታቸው ታውቋል። ብጹዓን ጳጳሳቱ የወቅቱ አንገብጋቢ ርዕሠ ጉዳይ በሆነው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ ሰፊ ወይይት በማድረግ የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራቱ ወረርሽኙን ለመግታት መወሰድ ባለባቸው ወጤታማ መንገዶች ላይ የሚወያዩ መሆኑ ታውቋል። ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአውሮፓ ውስጥ በጤና፣ በማሕበራዊ ሕይወት እና በኤኮኖሚ ላይ እያስከተለ ያለውን ቀውስ ለመቀንስ የሚያስችሉ የአውሮፓ ሕብረት ፖለቲካዊ እሴቶች ላይ መሠረት በማድረግ የመፍትሄ ሃሳቦችን እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።             

የወ/ሮ ማርጋሪቲስ ሺነስም በስብሰባው ላይ መገኘት

የአውሮፓ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚደንት ማርጋሪቲስ ሺነስም ቨብጹዓን ጳጳሳቱ ስብሰባ ላይ መገኘታቸው ጳጳሳቱ ውይይታቸውን መደበኛ በሆነ መንገድ፣ ከሌሎች የቤተ ክርስቲያን ተቋማት ጋር ግልጽ ውይይቶችን በስፋት ለማካሄድ የሚያግዝ መሆኑ ታውቋል። ብጹዓን ጳጳስቱ የሚያካሂዱት ውይይት ከዚህ በፊት በአውሮፓ የሚገኙ የሕብረቱ አባል አገራት ለመመራት የተስማሙበት የአንቀጽ 17 ደንብን የሚያከብር መሆኑ ታውቋል። በዚህም መሠረት በተለይም ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን በማስመልከት ጠንካራ የመፍትሄ ሃሳብን እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል። የመፍትሄ ሃሳቡ የሚመነጨው ከአውሮፓ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ የተወጣጣው አንድ ቡድን እ. አ. አ 2020 ዓ. ም. ላይ የሰደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያዎችን ጉዳይ በማስመልከት ያዘጋጀውን መግለጫ መሠረት የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል። ብጹዓን ጳጳሳቱ በተጨማሪም በአውሮፓ ውስጥ የሃይማኖት ነፃነትን ስለማሳደግ እና ስለመጠበቅ፣ የተለያዩ አገራዊ ስጋቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደፊት የሚገጥሟቸውን ችግሮች እንዴት በብቃት መወጣት እንዳለባቸው የሚወያዩ መሆኑ ታውቋል።

18 March 2021, 16:39