በአውሮፓ አህጉር የሚገኙ ብጹዕን ጳጳሳት የአውሮፓ ፓርላማ ለሕይወት ጥበቃ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ! በአውሮፓ አህጉር የሚገኙ ብጹዕን ጳጳሳት የአውሮፓ ፓርላማ ለሕይወት ጥበቃ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ! 

በአውሮፓ አህጉር የሚገኙ ብጹዕን ጳጳሳት የአውሮፓ ፓርላማ ለሕይወት ጥበቃ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ!

በቅርቡ የፖላንድ መንግሥት ፅንስ ማስወረድን በተመለከተ የወጣውን ውሳኔ ተከትሎ በአውሮፓ አህጉር የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ለአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት በፃፉት ደብዳቤ የሁሉንም ሕይወት መጠበቅ የሚያስችል የሕይወት እንክብካቤ እና ጥበቃ አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተው መናገራቸው ይታወሳል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በአውሮፓ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት  ጉባሄ ህብረት እ.ኤ.አ በታህሳስ 2020 ዓ.ም በፖላንድ ውስጥ ፅንስ ማስወረድ “መብት” እየተባለ በሚጠራው ጉዳይ ላይ የአውሮፓ ፓርላማ ያፀደቀውን የውሳኔ ሀሳብ አንዳንድ ነጥቦችን ላይ የጳጳሳቱ ጉባሄ በመልእክታቸው ጥያቄ አንስተዋል።

በአውሮፓ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት  ጉባሄ ህብረት ሰኞ የካቲት 15/2013 ዓ.ም ለአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ለዴቪድ ማሪያ ሳሶሊ የተላከው ደብዳቤ ከአስቸጋሪ ወይም አላስፈላጊ እርግዝና ጋር ተያይዘው በሚከሰቱ የሕይወት ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙትን ሴቶችን ለመደገፍ የምትሞክረው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለሁሉም ሕይወት “ጥበቃና እንክብካቤ እንዲደረግ፣ በማህጸን ውስጥ የሚገኙ ያልተወለዱ ጨቅላ ሕጻናት ሕይወት ሳይቀር ጥበቃ እንዲደረግላቸው” ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጿል።

“እያንዳንዱ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር የተፈጠረ እንደ መሆኑ መጠን በተለይም ተጋላጭ የሆኑ የሰው ልጆች ሕይወት ጥበቃ ሊደረግላቸው ያስፈልጋል” ያሉት በአውሮፓ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ ህብረት አክለውም “ከመወለዱ በፊትም ሆነ በኋላ ለልጆች ልዩ ጥበቃ እና እንክብካቤ እንዲደረግ እንዲሁ በአለም አቀፍ የህግ ደረጃዎች የተባበሩት መንግስታት የሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን ጨምሮ ያወጡት ሕግ ተግባራዊ እንዲሆን የጳጳሳቱ ጉባሄ አጽኖት ሰጥቶ ገልጿል።

በፖላንድ ፅንስ ማስወረድ ላይ የተጣለው እገዳ

እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2020 ዓ.ም በፖላንድ ህገ-መንግስታዊ ፍ / ቤት የተሰጠው ውሳኔ በሀገሪቱ ውስጥ በአጠቃላይ ፅንስ ማስወረድ የተከለከለ ሲሆን ይህም አስገድዶ በመድፈር ወይም በዘመድ አዝማድ ወይም በእርግዝና ወቅት የእናትን ሕይወት አደጋ ላይ በሚጥልበት ጊዜ ብቻ እንደ ሁኔታው ታይቶ ጽንስ የማስወረድ ወይም የማቋረጥ መብት የሚሰጥ ሕግ መውጣቱ ይታወሳል።

እገዳው እ.አ.አ ከጥር ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው በፖላንድ ዋና ከተማ በዋርሶ እርምጃውን በሚደግፉ እና በተቃዋሚዎች መካከል በተከፋፈሉ ቡድኖች መካከል ተቃውሞ አስነስቷል።

እ.አ.አ በጥቅምት ወር የፍርድ ቤት ውሳኔ እ.አ.አ በ 1993 ዓ.ም ከባድ እና የማይቀለበስ የፅንስ መዛባት በሚከሰትበት ጊዜ ፅንስ ማስወረድ የሚፈቅድ ሕግ ህገ-መንግስቱን የሚፃረር መሆኑን አረጋግጧል። ያልተወለዱ ሕፃናት ሰዎች ናቸው ስለሆነም በሕይወት የመኖር መብትን በሚያረጋግጥ የፖላንድ ሕገ መንግሥት መሠረት ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል በሚል ሕሳቤ ነበር ፍርድቤቱ የጽንስ ማስወረድ እገዳን ያጸደቀው።

እ.ኤ.አ. ሕዳር 2020 ዓ.ም የአውሮፓ ፓርላማ ውሳኔ የአውሮፓ ህብረት ተቋማት በመላው አባል አገራት ፅንስ ማስወረድን ጨምሮ “የወሲብ እና የስነ ተዋልዶ ጤና መብቶችን” ለመደገፍ እና የህግ የበላይነትን የሚያጎለብቱ መሰረታዊ እና ሲቪል ማህበራት እንዲደግፉ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

የሕግ የበላይነት በተመለከተ የሚደረጉ ክርክሮች

በአውሮፓ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት  ጉባሄ ህብረት በደብዳቤያቸው ላይ እንዳሰፈሩት የአውሮፓ ህብረት ህግም ሆነ የአውሮፓ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ ፅንስ የማስወረድ መብትን አይሰጥም ፣ ስለሆነም ጉዳዩን ለአባል አገራት የሕግ ሥርዓቶች ሊተው እንደ ሚገባ አክለው ገልጸዋል።

በዚህ ረገድ የአውሮፓ ህብረት መሰረታዊ መርህ የአውሮፓ ህብረት የተጠቀሱትን ስምምነቶች ዓላማ ለማሳካት በተስማሙባቸው ስምምነቶች ውስጥ አባል አገራት በሚሰጧቸው የብቃት ወሰን ላይ በመመርኮዝ ብቻ የሚሰራበት የግንኙነት መርህ ነው።

ስለዚህ ይህንን መርሕ ማክበር በአውሮፓ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ ህብረት እንደ ገለጹት “የሕግ የበላይነት መስፈርት” ነው ፣ ምክንያቱም የአውሮፓ ፓርላማ ውሳኔ “ለህግ የበላይነት መከበር ለህብረቱ ሥራ አስፈላጊ ነው” የሚል በመሆኑ የተነሳ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ይኸው የሕግ የበላይነት “በአባል አገራት የግል ብቃቶች እንዲሁም የአባል አገራት በብቃት የመረጧቸውን ምርጫዎች ማክበርን ይጠይቃል” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

የህሊና ተቃውሞ

በአውሮፓ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት  ጉባሄ ህብረት ሌላ አሳሳቢ ጉዳይ የፓርላማው ውሳኔ በሕሊና የመቃወም መሠረታዊ መብትን የሚጥስ ይመስላል ፣ ይህም በአውሮፓ ህብረት መሠረታዊ መብቶች ቻርተር ውስጥ የተጠቀሰው የሕሊና ነፃነት ነው” በመሆኑም ሕብረቱ ይህንን መሰረታዊ መብት ሊያከብር እንደ ሚገባ በአውሮፓ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት  ጉባሄ ህብረት በመልእክታቸው አክለው ገለጸዋል።

ይህ በአውሮፓ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ ህብረት አፅንዖት የሰጡበት ሁኔታ በተለይም አሳሳቢ እና መሻሻል የሚገባው ጉዳይ ሲሆን ምክንያቱም በብዙ ጉዳዮች ላይ የህሊና የመቃወም መብት በተለይም በጤና አጠባበቅ ዘርፍ አድልዎ ስለሚፈፀምባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ለሁሉም እኩል የሆነ ጥበቃ ማደረግ እና አድሎን ማስወገድ በተመለከተ

በተመሳሳይ መልኩም በአውሮፓ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት  ጉባሄ ህብረት የፓርላማውን አጣቃሽ የሆኑ የሕግ ድንጋጌዎች ሙሉ በሙሉ በተመለከተ በመፍትሔው በርካታ አንቀጾች ውስጥ እኩል የሆነ የሰው ልጆች መብት ጥበቃ እና አያያዝ እና ያለ መድልዎ መብት ማክበር የመሳሰሉ ሕጎች የተጠቀሱ ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን አንዳንድ ሕጎች አድሎ በመፍጠር የአውሮፓ ህብረት ብቃቶችን ድንበር ለማደብዘዝ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው አክለው ገልጸዋል። ይህ የአውሮፓ ህብረት ቻርተር አንቀጽ 51.2 ን የሚፃረር መሆኑን ያስጠነቀቁት በአውሮፓ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት  ጉባሄ ህብረት ቻርተሩ “ከህብረቱ ስልጣን በላይ የህብረት ህግን የመተግበር መስክን አያራዝምም ወይም ለህብረቱ አዲስ ሀይል ወይም ተግባር አያቋቁምም” በማለት አስጠንቅቀዋል።

በአውሮፓ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት  ጉባሄ ህብረት ቀጥሎም “እንደ ዓለም አቀፋዊነት ፣ የማይዳሰስ ፣ የማይቀለበስ ፣ የማይነጣጠሉ እና እርስ በእርሱ የሚደጋገፉ ነገሮች” በሚል አስተሳሰብ ፣ እንደ አስተሳሰብ ፣ እንደ ሕሊና እና እንደ ሃይማኖት ነፃነት ያሉ መሠረታዊ መብቶችን ከግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ በተለይ የአውሮፓ ህብረት ቻርተር ብሔራዊ ህገመንግስታዊ ባህሎችን የማክበር እና ብሔራዊ የሆኑ የአባል አገራትን ህጎች መጠበቅ እንደ ሚገባ አክለው ገልጸዋል።

በአውሮፓ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት  ጉባሄ ህብረት በፖላንድ በሕግ ላይ በተነሱት ተቃውሞዎች መሠረት በአብያተ ክርስቲያናት እና በአምልኮ ቦታዎች ተቀባይነት የሌለው ጥቃት  በተፈፀመበት ወቅት ውግዘት ወይም የአብሮነት መግለጫዎች በመንግስት በኩል ባለመውጣቱ እንዳሳዘናቸው አክለው በመልእክታቸው ገልጸዋል።

በአውሮፓ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት  ጉባሄ ህብረት ፕሬዝዳንት የሆኑት ካርዲናል ዣን ክላውድ ሆለሪች እና በአውሮፓ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት  ጉባሄ ህብረት ምክትል ፕሬዚዳንቶች የተፈረመውን ደብዳቤ ሲያጠናቅቁ የአውሮፓ ሕብረት በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ያለውን አቋም እንዲያብራራ በአክብሮ ከጠየቁ በኋላ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

26 February 2021, 11:29