የሰብዓዊ ወንድማማችነት አለማቀፍ ቀን በኢትዮጲያ ተከበረበት ወቅት የሰብዓዊ ወንድማማችነት አለማቀፍ ቀን በኢትዮጲያ ተከበረበት ወቅት 

የሰብዓዊ ወንድማማችነት አለማቀፍ ቀን በኢትዮጲያ ተክብሮ ማለፉ ተገለጸ።

የሰው ልጆች ወንድማማችነት/ እህትማማችነት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመጀምሪያ ጊዜ እ.አ.አ. የካቲት 4 ቀን 2021 ዓ.ም. ተከበሯል። ብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በበይነ መረብ በሚደረገው ውይይት የሚሳተፉ መሆኑ ታውቋል። በኢትዮጵያም በአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ ጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ፣ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን፣ ብፁዕ ሊቀጳጳሳት አንቷን ካሚሌሪ በኢትዮጵያ የቅድስት መንበር አምባሳደር፣ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ ሙፍቲህ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት፣ ሌሎች የሃይማኖት አባቶች፣ እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ እና ሀገራዊ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት ተከብሮ ውሏል።

በኢትዮጵያ የተካሄደውን ኮንፈረንስ አሜን ኢትዮጵያ ለሰላም እና በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኤሜረቶች ኤምባሲ በመተባበር ያዘጋጁት መሆኑ ተገልጿል።

ዓለም አቀፍ የሰው ልጆች ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ቀን የሚከበረው ብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የአል-አዝሃር ኢማም አህመድ አል ጠይብ እ.አ.አ. የካቲት 4 ቀን 2019 ዓ.ም. የተፈራረሙትን የዓለም ዓቀፍ ወንድማማችነት ሰነድ መሰረት በማድረግ ይህንኑ ታላቅ ተግባር ለመዘከር ነው።

ምንጭ፡ የኢትዮጲያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዋና ጽህፈት ቤት

Photogallery

የሰብዓዊ ወንድማማችነት አለማቀፍ ቀን በኢትዮጲያ ተከበረበት ወቅት
04 February 2021, 14:13