በጥር 30/2013 ዓ.ም በአሜሪካ ምስጢረ ተክሊል የፈጸሙ ሰዎች መታሰቢያ ሳምንት ይከበራል።
የአሜሪካ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ ይፋ በደረገው ዘገባው እንደ ገለጸው ከመጪው ጥር 30/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሰባት ቀናት “ማግኘት፣ ማኖር እና ማክበር” በሚል መሪ ቃል ምስጢረ ተክሊል የፈጸሙ ተጋቢዎች ከሠርጋቸው ቀን ጀምሮ ስላለው እድገታቸው እንዲያሰላስሉ እና በእዚህ ሁኔታ እንዴት መቀጠል እንደ ሚገባቸው ለመርዳት በሠርጋቸው ቀን የገቡትን ቃል ኪዳኖች፣ የነበራቸውን ተስፋዎች በማዳበር የትዳር ጓደኛቸውን በመውደድ እና በማክበር የበሰለ የሕይወት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ የሚረዳ ዝግጅት ከወዲሁ መዘጋጀቱ ተገልጿል።
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ብሄራዊ የሠርግ ሳምንት ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ለማንፀባረቅ እና ጥልቅ ለማድረግ ፣ በየቀኑ ፣ አንድ ላይ በሕብረት ለመጓዝ የሚረዳ ሳምንት እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን ይህ በአሜሪካ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት የተዘጋጀው የአንድ ሳምንት ዝግጅት ከመጪው ጥር 30/2013 ዓ.ም ጀመሮ ለሰባት ቀናት ያህል በተለያዩ ዝግጅቶችን በማቅረብ የሚከበር ሳምንት ነው። “ማግኘት፣ ማኖር እና ማክበር” በሚል መሪ ቃል ፣ የጋብቻ ቃል ኪዳን የሚታወስበት እንዲሁም በእቅዱ ውስጥ ያሉ ተሳታፊዎች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉትን ልዩ የሆነ በእንግሊዘኛው ቃል “meme” (ሚም በጅምላ ባህል ውስጥ ብዙውን ጊዜ በድንገት ታዋቂ እየሆነ የሚሄድ ሀሳብ ፣ ዘይቤ ወይም ድርጊት ነው። ቃሉ በሪቻርድ ዳውኪንስ እ.ኤ.አ. በ 1976 “የራስ ወዳድ ጂን” በተባለው መፅሃፉ ውስጥ የባህል መረጃ እንዴት እንደሚሰራጭ ለማስረዳት የሚጠቅም መተግበሪያ ነው) “ሜሞ” መጠቀምን የሚያጠቃልል ሲሆን በእዚህም መተግበሪያ ምስጢረ ተክሊል የፈጸሙ ጥንዶች ማኅበራዊ መገለጫዎቻቸውን የሚያመለክቱ መልእክቶችን የሚለዋወጡበት አውድ እንዲሆን ታቅዶ የተዘጋጀ እንደ ሆነ ተገልጿል። ባለትዳሮች በተወሰነ የጸሎት ዓላማ የታጀቡ ምስሎችን በመለዋወጥ ቤተሰባዊ ሕይወታቸውን እንዲያሳድጉ የሚረዳቸው ዝግጅቶች በእዚህ በአንድ ሳምንት ዝግጅት ውስጥ የተካተተ ሲሆን የካቲት 05/2013 ዓ.ም ለባለትዳሮች እና ቤተሰቦች በመገናኛ በዙሃን አውታሮች በቀጥታ የሚተላለፍ የመቁጠሪያ ጸሎት እንደ ሚደረግ ቀጠሮ እንደ ተያዘም ተገልጿል።
በመጨረሻም እሁድ የካቲት 07/2013 ዓ.ም በመላው አገሪቱ የሚገኙ ምዕመናን ሁሉ በጣም በተገቢው መንገድ “የምስጢረ ተክሊል ሰንበት” የሚል አርዕስት የተሰጠውን እለተ ሰንበት ምዕመኑ ለየት ባለ ሁኔታ ምስጢረ ተክሊል የፈጸሙ ሰዎችን በማሰብ እንዲከበሩ ተጋብዘዋል ፣ ለዚህም ልዩ የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ ስርዓት እንደ ሚደረግ ተገጿል። በውስጡም “ጋብቻ እና ቤተሰብ ሁሉንም ይመለከታሉ ፣ ምክንያቱም እያንዳንዳችን ከቤተሰብ የተገኘን ስለሆነ፣ እያንዳንዳችን የእግዚአብሔር ልጆች ነን” የሚል አጽንዖት ተሰጥቶታል። ስለዚህ “ቤተክርስቲያኗ በጋብቻ እና በቤተሰብ ላይ የምታስተምረው ትምህርት ለሁሉም ሰው አስፈላጊ ነው”።
በተጨማሪም የአሜሪካ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ ምዕመናን “የጌታ ምህረት ታላቅ” መሆኑን አውቀው “የጋብቻን እና ከተጋቡ በኋላ ጋብቻቸውን ወደ ፊት ማስቀጠል ያልቻሉ ቤተሰቦች ልምድን እና ህመምን እንዲገነዘቡ” በትህታና አሳስበዋል። በተጨማሪም “የግለሰባችን ሁኔታ ምንም ይሁን ምን ሁላችንም በቤተሰብ ራእይ ላይ እግዚአብሔር ድርሻውን እንዲወጣ ማደረግ አለብን” የሚለውን እውነታ ከግምት ውስጥ ለማስገባት ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ የሰጡ ሲሆን ምክንያቱም “በንስጢረ ጥምቀት ሁላችንም የአንዱ ፍፁም ቤተሰብ አካል ነን- የእግዚአብሔር ቤተሰብ ፣ እንደ ተወዳጅ የአብ ልጆች ነን” የሚለውን የቤተክርስቲያን አስተምህሮ በፍጹም መዘንጋት አይኖርብንም ብለዋል።
ጸሎት ፣ እረፍት እና መቀራረብ
ይህ የአሜሪካ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ ይፋ ያደርገው ብሔራዊ ምስጢረ ተክሊል የፈጸሙ ሰዎች ሳምንት ላይ “ተጋቢዎች ከሠርጋቸው ቀን ጀምሮ ስላላቸው እድገታቸው እና የትዳር ጓደኛቸውን በመውደድ እና በማክበር ብስለታቸውን ለመቀጠል እድል የሚሰጣቸው” ሳምንት እንደ ሚሆን ከወዲሁ ይጠበቃል። ስለሆነም ከፀሎት ጀምሮ ሶስት ተግባራዊ የሚሆን ዝግጅቶች የሚከናወኑ ሲሆን እነዚህም “ከሥራ አጥነት ጋር ለሚታገሉ ወይም ከትዳር ጓደኞቻቸው ጋር በመለያየታቸው ምክንያት በተለይም በችግር ላይ ላሉ ቤተሰቦች እና ለመላው ልጆቻቸው ጸሎት እንዳድርግ” በማለት ጳጳሳቱ ጥሪ በማቅረባቸው መሰረት በእዚህ መንፈስ ጸሎት ይከናወናል። በሁለተኛ ደረጃ እሁድ “የጌታ ቀን ፣ ለሚዋደዱ ባለትዳሮች ተወስኖ ለእረፍትና በቅዳሴ አከባበር ወይም በእረፍት ጊዜያት አብረዋቸው እንዲኖሩ የእረፍት ቀን” ተብሎ ተጠርቷል። በመጨረሻም ፣ እንደ ሦስተኛ ነጥብ ምስጢረ ተክሊል የፈጸሙ ተጋቢዎች “ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር እና የቤተሰብም ናት” በማለት ጸሎት ይደግማሉ። ምእመናን ይህንን ከግምት በማስገባት በችግር ውስጥ ካሉ ቤተሰቦች ጋር እንዲቀራረቡ ተጋብዘዋል ፣ በተለይም በ “ኮቪድ -19” ወረርሽኝ በጣም የተሰቃዩ ቤሰቦችን እንዲሁም ለአረጋውያን እና ችግረኛ ለሆኑ ሰዎች ጸሎት የሚደረግበት ሳምንት እንዲሆን መወሰኑም ተገልጿል።