ኢየሱስ በቃና ዘገሊላ ሰርግ ላይ የመጀመርያውን ተአምር አደረገ ኢየሱስ በቃና ዘገሊላ ሰርግ ላይ የመጀመርያውን ተአምር አደረገ 

ቃና ዘገሊላ

ቃና ዘገሊላ በምትባል ሀገር ሠርግ ተደረገ። እመቤታችን ድንግል ማርያም ለሠርግ ተጠርጣ ሄደች፡፡ ኢየሱስ በሠርጉ ቦታ ተጠርቶ ነበር፡፡ በምሳ ጊዜ ወይን ስላለቀ እመቤታችን ድንግል ማርያም የአምላክ ርኀርኀት እናት ለሙሽሮቹ አዘነችላቸውና ለኢየሱስ “ወይን እኮ የላቸውም” አለችው፡፡ እርሱም አንቺ ሴት ምን ትያለሽ ጊዜዬ ገና አልደረሰም” አያለ መለሰላት፡፡ እርስዋም በአነጋገሩ ተስፋ አልቆረጠችም እምቢ እንደማይላት በማመን በዳሱ የሚያገለግሉ ሰዎችን “የሚላችሁን አድርጉ” አለቻቸው።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

አይሁዳውያን ለመታጠቢያ የሚጠቀሙባቸው ስድስት ጋኖች ነበሩ፡፡ አንዳንዱ ሰላሳ ሊትር አንዳንዱ አርባ ሊትር ይይዙ ነበር፡፡ ኢየሱስ ሳይዘገይ ለአገልጋዮቹ እንሥራዋቹን በውኃ እንዲሞሉዋቸው አዘዘ፡፡ ወዲያው ውኃውን በተአምር ወደ ወይን ጠጅ ለወጠው፡፡ ይህንን አስደናቂ ሥራ ከሠራ በኋላ “ቅዱት$ አላቸው፡፡ እነርሱም ቀድተው ለአስተናጋጁ ሰጡት፡፡ ከውኃ የተቀየረውን ወይን ጠጅ ሲቀምስ ተገረመ የሚለውን አጣ፡፡ ከየት አንደመጣ አያውቅም ነበርና አገልጋዮቹ ግን ውኃው ወደ ወይን አንደተለወጠ ያውቁ ነበር፡፡ አስተናጋጁ በጣም ተደንቆ ሙሽራውን አስጠራና “ሰው ሁሉ በመጀመሪያ ጥሩውን ያቀርባል ሰዎቹ ከሰከሩ በኋላ መናኛውን ያቀርባል አንተ ግን መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተህ አመጣህ” ((ዮሐ. 2፣1-11)) እያለ ተናገረው፡፡ ይህ ኢየሱስ በቃና ዘገሊላ ያደረገው የመጀመሪያ ተአምር ነው፡፡ በዚህም ክብሩን ገለጠ ደቀ መዛሙርቱ በእርሱ አመኑ፤ ይህ ተአምር ሁለት ነገሮች ያስገነዝበናል።

1ኛ/ እመቤታችን ማርያም ለሰው ያላት ርኀራኄ

ሠርገኞቹ ያለስጋት በደስታ ሲያስተናግዱ ድንገት ወይን ጠጅ አለቀባቸው፡፡ ሙሽሮቸ ይህን አሳዛኝ ሁኔታ ሲመለከቱ በጣም ደነገጡ፣ የሚገቡበት ጠፋቸው፡፡ እመቤታችን ድንግል ማርያም እፍረታቸውንና ውርደታቸውን ተመልክታ ራራችላቸው ሁሉን ነገር ወደሚችል ልጅዋ ሄደችና ጭንቃቸውን አይቶ እንዲረዳቸው ለመነችው፡፡ እንደሚሰማትም አምና “ወይን እኮ አልቆባቸዋል" አለችው፡፡

2ኛ/ የእመቤታችን ድንግል ማርያም በአምላከ ፊት ያላት ተሰሚነት

ምንም እንኳ ኢየሱስ መልስ ሊሰጣት የማይፈልግ ቢመስልም ጥቂት ቆየት ብሎ ግን ትፈልገው የበረውን ተአምራት እንደ ልመናዋ አደረገላት፤ ሙሽሮቹን አስደስቶ አገዛት፡፡ ኢየሱስ ለዚያን በስንት ፍቅርና እንክብካቤ ያሳደገችውና ስለ እርሱ ብዙ ስቃናይና መከራ ላሳለፈችው ደግ እናቱ የለመነችውን ሊከለክላት አልፈለገም፡፡ ልመናዋን ተቀብሎ ሳያስደስታት ዝም ለማለት አልቻለም፡፡ በፍቅርዋ ተሸንፎ ምኞትዋን ለመፈጸመ ተገደደ፤ ፍቅርዋ ጊዜው ሳይደርስ ተአምር አሠራው። በዚህም የመጀመሪያ ተአምራት እርስዋን ደስ ለማሰኘት ሲል አደረገ።

እግዚአብሔር እኛን ለመጥቀም ብሎ ለሚወዳት እናቱ ለማርያም ትልቅ የርኀራኄ ሥልጣን ሰጣት፡፡ እርስዋ ደግሞ ይህን ርኀራኄና ተሰሚነት ዘወትር በጥቅማችን ላይ ታውለዋለች፡፡ በታላቅ ሰማያዊ ተደማጭነትዋ ከልዑል አምላክ ጸጋና ምሕረት ታማልደናለች፣ ቡራኬውን ታወርድልናለች፡፡ እንደዚህ ያለች ርኀርኀት መንፈሳዊት እናት በማግኘታችን ታድለናል፡፡ እንግዲህ በመልካም ዕድላችን ተደስተንና ተበረታትተን በተስፋ እርስዋን እንመልከተ። ዘወትር በተለይ በመከራችንና በፈተና ወቅት እርስዋን በመተማመን ጥበቃዋንና ዕዳታዋን እንለምን።

20 January 2021, 11:36