የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ 

ከሁሉም የእውቀት ምንጮች ጋር ገንቢ ውይይቶችን ማድረግ

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ ተፈጥሮአዊ ባሕሪይ

ክፍል 20

የካቶሊክ ቤተክርስቲያም ማሕበራዊ አስተምህሮ አዎንታዊ እና ገንቢ የእውቀት ገበታ ከሆኑ የተለያዩ ምንጮች ባበረከቱት አስተዋጾ ላይ መሰረቱን ያደረገ ሲሆን “በማህበራዊ ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ ሁኔታዎች ውስጥ እና በሰዎች በየጊዜው እና በተለዋዋጭ ሁኔታዎች ውስጥ ስለ ሰው የሚናገረውን እውነት ለመቅረጽ በተሻለ ሁኔታ ለማስተማር ይህ የሰው ልጅ ከሚመለከታቸው የተለያዩ አዎንታዊ እና ገንቢ ለሆኑ የእውቀት ምንጮች ጋር ውይይት ታደርጋለች ተባብራ ጸራላች”። ሥነ-ሥርዓቶች ጋር ውይይት ይጀምራል ፡፡ እነዚህ ተግሣጽዎች ምን ማበርከት እንዳለባቸው ይተነትናል ” (John Paul II, Encyclical Letter Centesimus Annus, 59: AAS 83 (1991), 864)። የቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ ጠቃሚ የሆኑ የፍልስፍና አስተምህሮችን እንዲሁም የማሕበራዊ ሳይንስ አስተምህሮችን የሚያበረክቱትን አስተዋጾችን ትጠቀማለች።

ከሁሉም በላይ የፍልስፍና ትምህርት አስተዋፅ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ አስተዋፅ የፍልስፍና ትምህርት የሚያበረክተው አስተዋጾ ለሰው ልጅ ተፈጥሮ ቅርብ እንድንሆን እና በእውቀት ብርሃን እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ የሰው ልጅ የእምነት መንገዱን እንዲረዳ እንደ ሚያደርግ ቀድሞውኑ ታይቷል። በምክንያታዊነት የቤተክርስቲያኗ ማህበራዊ አስተምህሮ በፍልስፍና ውስጣዊ አመክኒዮ ውስጥ እንዲያልፍ በማድረግ በሌላ አገላለጽ  አግባብ ባለው ክርክር በማድረግ አስተምህሮውን ይደግፋል።

የቤተክርስቲያኗ ማህበራዊ አስተምህሮ የፍልስፍና ሳይሆን የነገረ መለኮት አስተምህሮ አንድ አካል መሆኑን ማረጋገጥ የፍልስፍናውን ሚና ወይም አስተዋፆ ውድቅ ያደርገዋል ማለት አይደለም። እንደ እውነቱ ከሆነ ፍልስፍና የቤተክርስቲያኗን ማህበራዊ አስተምህሮ መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳቦች ዋና አካል የሆኑትን የሰው ልጅ፣ ማሕበረሰው፣ ነፃነት ፣ ህሊና ፣ ሥነ ምግባር ፣ ሕግ ፣ ፍትህ ፣ የጋራ ተጠቃሚነት፣ መተባበር ፣ ድጎማ፣ የመሳሰሉትን የቤተክርስቲያኗ ማሕበራዊ አስተምህሮ ዋና ዓላማ ግብ ይመታ ዘንድ አስፈላጊ እና ምቹ የሆነ መሣሪያ ነው። ይህ ግንዛቤ ሕብረተሰቡ እርስ በርሱ እንዲስማማ እና በማሕበረሰቡ ውስጥ መነቃቃት እንዲኖር የሚያደርግ ነው። በህብረተሰቡ ላይ የወንጌልን ብርሃን የማብራት ምክንያታዊ እና ተቀባይነት ያለው መሆኑን በድጋሚ የሚያረጋግጥ የፍልስፍና አስተምህሮ ነው፣ ይህም የእያንዳንዱ ሰው አዕምሮ እና ህሊና ክፍት እና የእውነት ቃልን ለመቀበል የተዘጋጀ እንዲሆን ያደርጋል ማለት ነው።

ለካቶሊክ ቤተክርስቲያም ማሕበራዊ አስተምህሮ ትልቅ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ የእውቀት ምንጮች መካከል የሰው ልጅን ሰብዓዊ ተፈጥሮ የሚያጠና ሳይንስ አንዱ የእውቀት ምንጭ ሲሆን የሰውን ልጅ ፍልስፍና ፣ ስነ-ህይወት ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ገጽታዎች የሚያጠና የእውቀት ዘርፍ ነው፣ በተጨማሪም የሰውን ልጅ ሰብዓዊ ተፈጥሮ የሚያጠና ሳይንስ በሰፊው ስለ ሰው ልጆች ያለን ልዩ ልዩ ግንዛቤ እንዲጨምር በማድረግ ስለ ዓለም ያለንን ግንዛቤ እንድናሰፋ ይረዳናል።

በተጨማሪም ማህበራዊ ሳይንስ በበኩሉ በማህበረሰቦች እና በእነዚያ ማህበረሰቦች ውስጥ ባሉ ግለሰቦች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠና የሳይንስ ትምህርት ቅርንጫፍ በመሆኑ የቤተክርስቲያኗ ማሕበራዊ አስተምህሮ ስያንሳዊ በሆነ መልኩ እንዲተገበር እና ውጤታማ እንዲሆን በከፍተኛ ደረጃ ሊያግዝ እና አስተዋጾ ሊያደርግ ይችላል።

ገንቢ እና አዋጭ የሆኑ የእውቀት ዘርፎች ሁሉ የሰውን ልጅ በተመለከተ ስለሰው ልጅ መላክምነት እና እውነት የሚያስተምህሩ የእውቀት ዘርፎች አስከሆኑ ድረስ ከቤተክርስቲያኗ ማሕበራዊ አስተምህሮ የተገለሉ ሊሆኑ በፍጹም አይገባቸውም። የሰው ልጅ ማህበራዊ ግንኙነቶቹን በይበልጥ እንድንረዳ እና ውስብስብ የሰው ልጅ ግንኙነቶችን  ሰፋ ባለ መልኩ እንድንረዳ አስተዋጾ የሚያደርጉ ማነኛውም ገንቢ እና እውነተኛ የሆነ አስተዋጾ ማበርከት ለሚችሉ የእውቀት ዘርፎች እውቅና ትሰጣለች። የሰውን ልጅ በጥልቀት ለመረዳት የሚረዳ እውቀት ከሥነ-መለኮት አስተምህሮ ብቻ የመነጫ አንዳልሆነ የምትገነዘብ ሲሆን የሥነ-መለኮት ትምህርት  በራሱ  በብዙ የእውቀት ምንጭ የሆኑ ቅርንጫፎች አስተዋጾ የተመሰረተ የውቀት ዘርፍ ቢሆንም የቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ ከዚህም በላቀ ሁኔታ ስለ ሰው ልጆች ውስብስብ ግንኙነቶች ይበልጥ ማብራራት ከሚችሉ የእውቀት ዘርፎች በእውነት ላይ የተመሰረቱ እስከ ሆነ ድረስ የሚያበረክቱትን አስተዋጾ ትቀበላለች።

ይህ የሌሎች የእውቀት ዘረፎችን በትኩረት እና ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚያበረክቱትን አስተዋጾ የምትቀበል ሲሆን በዚህ ረገድ የቤተክርስቲያኗ ማሕበራዊ አስተምህሮ አስተማማኝ ፣ ተጨባጭ እና ተዛማጅነት ያለው እንዲሆን ያደርገዋል ማለት ነው።  ለሳይንስ ሊቃውንት ምስጋና ይግባቸውና ቤተክርስቲያኗ በኅብረተሰቡ ውስጥ ስላለው ውስብስብ ማሕበራዊ ግንኙነት የበለጠ ትክክለኛ ግንዛቤ ማግኘት ትችላለች ፣ የዘመኑ ሰዎች ሊረዱት በሚችለው ዓይነት ቋንቋ ይበልጥ አሳማኝ በሆነ መንገድ አስተምህሮዋን ማስተላለፍ እንድትችል የሚረዳት ሲሆን እንዲሁም በዘመናችን በህሊና እና በማህበራዊ ሀላፊነት የመመስረት ስራዋን በብቃት እንድትወጣ ያደርጋታል፣ የእግዚአብሔር ቃል እና ማህበራዊ ትምህርቶች የሚመነጩበት ከእምነት እንደ ሆነ እንድንገነዘብ ይረዳናል (John Paul II, Encyclical Letter Centesimus Annus, 54: AAS 83 (1991), 860)።

02 August 2020, 16:36