የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ 

ቤተክርስቲያን በማሕበራዊ አስተምህሯ አማካይነት ቅዱስ ወንጌልን ታውጃለች

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ

ክፍል አስራ ሰባት

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በማኅበራዊ አስተምህሮዋ አማካይነት ጌታ ለቤተክርስቲያን በአደራ የሰጣትን ቅዱስ ወንጌል የማወጅ ተግባሯን ታከናውናለች። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የሚገኘውን ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የሚያወጀውን ቅዱስ ወንጌል እና በክርስቶስ የተከናወነውን የነፃነትና የመቤዤት ወይም የደህንነት መልእክት ለአለም የማዳረስ ተልዕኮ ተሰቷታል። ቅዱስ ወንጌልን በማወጅ ቤተክርስቲያን “ለሰው ልጅ በክርስቶስ ስም ለክብሩ እና ለጥሪው እንዲተጋ እንዲሁም የሰው ልጆች አንድ እንዲሆኑ አንድነትን የሚያጠናክር የምስራች ቃል ታውጃለች ትመሰክራለች። ከመለኮታዊ ጥበብ ጋር የሚስማሙ የፍትህ እና የሰላም ጥያቄዎችን ታስተምራለች ”(የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ቁጥር 2419 ይመልከቱ)።

ቅዱስ ወንጌል በቤተክርስቲያኗ አማካይነት እየተሰበከ ይህ ማህበራዊ አስተምህሮ በወንዶች እና በሴቶች መካከል ነፃነትን የሚያመጣ ቃል ነው (John Paul II, Homily at Pentecost for the First Centenary of Rerum Novarum (19 May 1991): AAS 84 (1992), 282)። ይህ ማለት  የፍቅር ፣ የፍትህ ፣ የነፃነት እና የሰላም ሀሳቦች እና እቅዶችን ይተነብያል ፣ ከእግዚአብሔር መንፈስ የሚመጣ የእውነት ጸጋ ውጤታማነትን ያስተምራል ማለት ነው። ለማህበራዊው ዘርፍ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ ማለት በቅዱስ ወንጌሉ ውስጥ የሚገኘውን እጅግ በጣም አስፈላጊ የሚባሉ የቅዱስ ወንጌል እሴቶችን እና በቅዱስ ወንጌል አማካይነት የሚገኘውን የነፃነት ኃይል በሰዎች ልብ ውስጥ ማስረጽን እና መስጠትን ያካትታል፣ ምክንያቱም ክርስቶስ የሚፈልገውን ዓይነት ሕብረት በመፍጠር በማሕበርሰቡ ውስጥ የሕብረት መንፈስ እንዲስፋፋ ለማስቻል ይሰራል። ከእግዚአብሔር መንግሥት ጋር የበለጠ የሚስማማ ማሕበርሰብ ለመፍጠር የሚያስችል ዓይነተኛ መንገድ ነው። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በማኅበራዊ ትምህርቷ አማካይነት ቤተክርስቲያኗ ተልዕኮዋን የምትወጣበት መንገድ ብቻ ሳይሆን ይህ ሕልሟ እውን ይሆን ዘንድ በትጋት እና በታማኘት ትሰራለች ማለት ነው። በክርስቶስ የተከናወነው ቤዛነት እና የደህንነት ምስጢር ለቤተክርስቲያኗ መዳን ተልዕኮ በአደራ የተሰጠው በእውነቱ ከተፈጥሮ በላይ ባለው ኃይል አማካይነት ነው። ይህ ልኬት የደኅንነት መገለጫ ብቻ አይደለም ፣ ነገር ግን የእሱ አስፈላጊ መግለጫ ነው (Paul VI, Apostolic Exhortation Evangelii Nuntiandi 9, 30: AAS 68 (1976), 10-11; John Paul II, Address to the Third General Conference of Latin American Bishops, Puebla, Mexico (28 January 1979), III/4-7: AAS 71 (1979), 199-204; Congregation for the Doctrine of the Faith, Instruction Libertatis Conscientia, 63-64, 80: AAS 79 (1987), 581-582, 590-591)። ከሰው በላይ የሆነ ኃይል ተፈጥሮ የሚያበቃበት እና አንድ አካል ወይም አንድ ስፍራ የሚጀምርበት ነገር ተድርጎ መቆጠር የሌለበት ሲሆን ነገር ግን ፍጡርን ከፈጣሪ ጋር ለማገናኘት እና ደረጃውን ከፍ ለማደረግ ታስቦ በእግዚአብሔር የደህንነት እቅድ ውስጥ የተቀመጠ ነገር ነው።  በዚህ መንገድ ፍጥረት ወይም ሰብአዊነት ከሰው በላይ ከሆነ ኃይል ወይም ከሥነ-መለኮታዊ ቅደም ተከተል  ከሚያስገኘው ፀጋ እና እምነት ውጭ የሆነ ወይም የተገለለ አይሆንም፣ ይልቁንም በውስጡ ይገኛል በእርሱ አማካይነት ከፍ ከፍ ብሏል። “እግዚአብሔር በሚታየው ቃሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሰው ልጆችን ተበዤ”። ይህ ቃል ኃጢአት በገባ ጊዜ “ፍጥረታት ሁሉ የእግዚአብሔር መገለጥ በናፍቆት ይጠባበቃል። ፍጥረት ሁሉ ለከንቱነት ተዳርጎአል፤ ይኸውም በራሱ ምርጫ ሳይሆን፣ በተስፋ እንዲጓዝ ካደረገው ከፈቃዱ የተነሣ ነው። ይህም ፍጥረት ራሱ ከመበስበስ ባርነት ነጻ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሆነው ወደ ከበረው ነጻነት እንዲደርስ ነው። እስከ አሁን ድረስ ፍጥረት ሁሉ በምጥ ጊዜ እንዳለው ሥቃይ በመቃተት ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን (ሮሜ 8 19- 22) በዚህ ሁኔታ  መለኮታዊ የጥበብ እና የፍቅር ምንጭ መለኮታዊ ምንጭን እንደገና እንዲያገኝ አደረገ። በእውነት “እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሐ 3 16)። ከእግዚአብሔር ጋር የተገናኘንበት መስመር በአዳም አማካይነት በመስበሩ የተነሳ ሞት በአዳም፣ ሕይወት በክርስቶስ ተሰጠን “ስለዚህ ኀጢአት በአንድ ሰው በኩል ወደ ዓለም እንደ ገባ ሁሉ፣ ሞትም በኀጢአት በኩል ገብቶአል፤ በዚሁ መንገድ ሞት ወደ ሰዎች ሁሉ መጣ፤ ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፣ በአንድ ሰው መተላለፍ ምክንያት ሞት በዚህ ሰው በኩል የነገሠ ከሆነ፣ የእግዚአብሔርን የተትረፈረፈ ጸጋና የጽድቅ ስጦታ የተቀበሉት፣ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንዴት አብልጠው በሕይወት አይነግሡ!” (ሮሜ 5 12-21)። በክርስቶስ አማካይነት የሰው ልጆች ያጡትን መንፈሳዊ ክብር እንደ ገና ለመጎናጸፍ ችለዋል።

ሰው በዚህ ፍቅር ሙሉነት እና በዚህ ፍቅር ይካተታል፣ እሱ ሥጋዊ እና መንፈሳዊ ፣ ከሌሎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት ያለው ነው። ቤተክርስቲያን የተሰጣት ተልዕኮ ይህንን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያመጣውን የደህንነት ምስጢር ተጠብቆ እንድቆይ የማደረግ ኃላፊነት የተጠለባት ሲሆን የሰው ልጅ አጥቶት የነበረውን መንፈሳዊ ክብር በክርስቶስ አማካይነት መልሶ እንዲጎናጸፍ በማደረግ መንፈሳዊ እና ማሕበራዊ ክቡር ተጠብቆ ይኖር ዘንድ በማሕበራዊ አስተምህሮዋ አማካይነት ግንዛቤ እንዲያገኙ የበኩሏን ጥረት ታደርጋለች።

አዘጋጅ እና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

14 July 2020, 10:09