ከሊቢያ ወደ ጣሊያን በጀልባ ለመግባት እየሞከሩ የሚገኙ ስደተኞች ከሊቢያ ወደ ጣሊያን በጀልባ ለመግባት እየሞከሩ የሚገኙ ስደተኞች  

የወጣቶች ስደት እና የቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ እንክብካቤ

ክፍል ሰባት

1.   የቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ  እንክብካቤ  መመዘኛዎች፥

እንደ ጎርጎርሳዊያን አቆጣጠር 2012 ዓ.ም ላይ ር.ሊ.ጳ  ቤኔዲክቶስ 16ኛ በወቅቱ ያስተላለፉትን መልእክት እንዲህ በማለት ነበረ የጀመሩት “ዛሬ በታላቅ ጥንካሬ በልዩ ረጅም የሕይወት ተሞክሮ መሠረት የሆናቹ ውድ ወጣቶቼ (ልጆቼ)፣ ክርስቶስን አትፍሩ (አትሽሹ) እላለሁ። ምንም ነገር አይወስድም ፣ እናም ሁሉንም ነገር ይሰጣችዋል” በማለት መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን ሲቀጥሉም “ለወጣቶች የሚሰጠው ሐዋርያዊ እንክብካቤ ወጣት ስደተኞች አስፈላጊውን የህይወት ሁኔታዎችን እና በባህላዊ እሴት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ነው። የሐዋርያዊ እንክብካቤ ዓላማ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ልዩ የሆነ፣ የወጣት ስደተኞች ችግር በመተንተን ፣ የወጣትን አስተሳሰብ  ለማሳደግና ለማሻሻል ጥረት ያደርጋል ፡፡ እንደ ቤተክርስቲያኗ መብትና ግዴታ ሁሉ ይህንን ተስፋም ለዓለም ለማወጅ ግዴታ እንዳለበት ማወቅ ነው። ለዚህ የቤተክርስቲያኗዋ ተሞክሮ በዚህ ውስጥ ጥበብን የታከለ መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ ነው ቤተክርስቲያን ራሷን በተለያየ መንገድ  ለመገግለጽ የምትጥረው” በማለት መናገራቸው ይታወሳል።

ቤተክርስቲያኗ ብቸኛዋ  የስደተኞች እናት ናት

ለሰው ልጅ ከሚትሰጠው ቦታ አንጻር ስንመለከት  የቤተክርስቲያኗ ሚና እንደ ቅድስት እናት ሆና ታገለግላለች፡፡ ለሰው ነፍሷ ባላት ከፍተኛ ፍቅር ተገፋፍታ የሰው ልጆችን ሁሉ ለመዳን፣ የመዳን ኃላፊነት የተሰጣቸውን ተልእኮዎች ለመወጣት ጥረት ታደርጋለች፣ በክርስቶስ የተሰጠውን ተልእኮ፡ ግደታ የቤተክርስቲያኗን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የሚያተኩር ሲሆን ይህም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዓለም አቀፋዊ አንድነት አቀራረብን የሚያመላክት ነው፡፡ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሐዋርያዊ አገልግሎት እንክብካቤዋን የሁሉንም የሰው ልጆች ፍላጎት ለማሟላት እና በተቻላት አቅም እና መጠን ሁሉን ለማገልገል ቅድሚያ በመስጠት በተለይም ለወጣት ስደተኞች የለውጥ መንገድ በማበጀት አፅኖት ሰጥታ ትሰራለች። ሆኖም የቤተክርስቲያን ዓላማና አስተምሮ አንድ ቢሆንም የአገልግሎት አሰጣጡ እንደየ አገሩ አቅምና ሁነታ ይመዘናል።

የሐዋርያዊ አገልግሎት እንክብካቤ ላይ የምናደርጋቸው ጥረቶች በወጣቶች ስደት ላይ ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴን ማዳበር እንዲችሉ በተስፋ መስራት እንዳለብን የእናታዊ ፍቅር ትለግሳለች፡፡ እኛ እንደምናውቀው፣ አሁን ባለው ማህበራዊ አኗኗር  በህብረተሰብ ውስጥ፣ በኢኮኖሚ ፣ በፖለቲካ ፣ በባህላዊ እና የሃይማኖት ልምድ ስንመለከቱ ለተለያዩ ጉዳዮች በመጨነቅ፣ የቤተክርስቲያን ትምህርት በእርግጥ አዳዲስ እድሎችን ይሰጣል፣ ነገር ግን በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ አንዳንድ ያልተለመዱ ፈታኝ ሁኔታዎችን ያጋጥማል፡፡ “ተርቤ አብልታችሁኛል፣ ተጠምቼ አጠጥታችሁል፣ እንግዳ ሆኜ ተቀበላችሁኝ ነበር” (ማቴ 25፥ 35) በማለት በመጨረሻው ቀን ላይ ጌታ የሚያቀርብልን ጥያቄ በመሆኑ የተነሳ በዚህ መሰረት ለእነዚህ ጥያቄዎች ተገቢው መልስ ለመስጠት ያስችለን ዘንድ እናት የሆነችው ቤተክርስቲያን ታስተምረናለች፡፡ የቤተክርስቲያኗን እናትነት እናደንቃለን፣ ስለዚህ ባለው ተስፋ መሰረት የዘመናችን ወጣቶች በልጅነት መንፈስ እንድኖር ቤተክርስቲያን የአቅሙዋን ሐዋርያዊ እንክብካቤ ታደርጋለች።

አዘጋጅ እና አቅራቢ አባ ኤርሚያስ ኩታፎ -ሮም

 

17 July 2020, 10:53