በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ከሚገኙ መንፈሳዊ ሥፍራዎች አንዱ፤ በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ከሚገኙ መንፈሳዊ ሥፍራዎች አንዱ፤ 

በኢየሩሳሌም የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች መንፈሳዊ ቅርሶች እንዲጠበቁ ጥሪ አቀረቡ።

በኢየሩሳሌም የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች እና ፓትሪያኮች የእስራኤል መንግሥት በአገሩ በሚገኙ ጥንታዊ እና ቅዱስ ሥፍራዎች ለሚገኙ ክርስቲያናዊ ቅርሶሶች ጥበቃ እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ። የሐይማኖት መሪዎች በተጨማሪም በኢየሩሳሌም ውስጥ በሚገኙ ክርስቲያን መንደሮች የሚኖሩ ምዕመናን ሰብዓዊ ክብር እንዲጠበቅ በማለት ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የቫቲካን ዜና፤

የአብያተ ክርስቲያና መሪዎች በጋራ ሆነው ባወጡት መግለጫ፣ በቅርቡ የኢየሩሳሌም ከተማ ፍርድ ቤት ያጸደቀው ደንብ ያሳሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል። የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሆነው ንብረት በሕገ ወጥ መንገድ ለአይሁድ ብሔራዊ ማኅበር እንደተሸጥ ተደርጎ የቀረበውን አቤቱታ የኢየሩሳሌም ፍርድ ቤት ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል።

በኢየሩሳሌም ውስጥ “የጃፋ በር ጉዳይ የወቅቱን መንግሥት መመሪያዎች ስጋት ላይ የጣለ ነው በማለት በኢየሩሳሌም የሚገኙ አስራ ሦስት ፓትሪያርኮች እና የቤተክርስቲያናት መሪዎች፣ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ያቀረበውን አቤቱታ በመደገፍ ድምጻቸውን አሰምተው፣ በጃፋ በር አካባቢ የሚገኘውን የቤተክትርስቲያኒቱ ንብረት ለመቆጣጠር አክራሪ ቡድኖች የሚያደርጉት ቁርጠኝነት የቅስቲቱን ከተማ አቋም የሚያሳንስ፣ የነጋዲያንን መንገድ የሚያደናቅፍ እና በኢየሩሳሌም የክርስቲያኖችን መኖር ለማዳከም የተደረገ ሴራ ነው ብለዋል። በማከልም ይህ ሴራ በግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና በንብረቷ ላይ ብቻ የተጠነሰሰ ሳይሆን፣ የኢሩሳሌም ከተማ የምትታወቅበት በሰላም አብሮ የመኖር የረጅም ጊዜ ባሕልን የሚጎዳ ነው በማለት የተሰማቸውን ቅሬታ ገልጸዋል።         

09 July 2020, 19:29