ጥላቻን እግዚአብሔር ይጸየፋል ጥላቻን እግዚአብሔር ይጸየፋል  

ጥላቻን እግዚአብሔር ይጸየፋል

እግዚአብሔር ራሱ ፍቅር ስለሆነ እኛን ሰዎችን ሲፈጥር ርስ በርሳቸን እየተጋገዝን እየተረዳዳን በፍቅር እንድንኖርና ምድራዊ ሕይወታችንን በሰላም እንድናሳልፍ አድርጐ ፈጠረን፡፡ ነገር ግን ይህ የተቀደሰው ውሳኔው የአዳም ኃጢአት ከመጣ በኋላ ብትንትኑ ወጥቶ በስምምነትና በፍቅር ፈንታ ጥላቻ ተተከለ የአዳም ኃጢአት እርስ በርሳችን እንድንጣላና እንድንዋጋ አደረገን፡፡ ጥላቻ መጀመሪያ የአዳም ልጆች ኃጢአት ነው፡፡ ቃኤል አቤልን ወንድሙን በመልካም ሥራው ቀንቶ በጥላቻ መንፈስ እስከ መግደል ደረሰ (ዘፍ.4፣8) ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ጥላቻ በሰው ልጆች መካከል ጠንካራ ስር እየበዛና እየባሰ መጣ፡፡

አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ኤሳው ከአባቱ ይጠብቀው የነበረውን ቡራኪ ወንድሙ ያዕቆብ ስለ ወሰደበት ተቀይሞት ሊገድለው አሰበ (ዘፍ.27፣41)፡፡ ዮሴፍ ሕልሙን ለወንድሞቹ በገለጠላቸው ጊዜ በሕልሙ ደንግጠው በምቀኝነት ተነሳስተው ጥላቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ብለው ሸጡት (ዘፍ.37፣9)፡፡ አይሁዳውያንም በጥላቻ ታሪክ ማለቂያና መጨረሻ የለውም፡፡ ጥላቻ መንፈስተነሣሥተው ኢየሱስን በመስቀል ላይ ቸንክረው ገደሉት፡፡ የጥላቻ ታሪክ ማለቂያና መጨረሻ የለውም። ጥላቻ በባዕዳንና በጐረቤት መካከል ብቻ ሳይሆን በቤተሰቦች፣ በወንድማማቾችና በወዳጆቹ መካከልም ብዙ ጊዜ ተስተውላል፡፡ በሚረባና በማይረባ ምክንያት እርስ በርሳችን እንጣላለን፡፡  ጥላቻ በበደል በቅናትና በትዕቢት በመሳሰሉት ነገሮች ምክንያት ይነሳል፡፡ ይህንን ነገር ተመልክቶ ቅዱስ አውጉስጢኖስ እኛ ሰዎች ትንሽ ፍጥረቶች ነን ይላል፡፡

“እገሌ ሰድቦኛል፣ ንቆኛል፣ መትቶኛል፣ ጠላቱ ነው፣ ፊቱን ለማየት  አልፈልግም ፣አይወደኝም ፣ አያከብረኝም፣ በእኔ ላይ ክፋ ያስባል፤ ያማኛል ክፉ ዕድል እንዲገጥመኝ ይመኛል፣አንስማማም፣ከእርሱ ጋር እንዴት ብዬእኖራለሁ; እርሱ ሰው የሚያስጠጋ አይደለም፡፡ከእርሱ ሴይጣን ይሻለኛልእያልን መርዝኛ ጥላቻ እንተፋበታለን፡፡በጠላትነት ዓይንም እናየዋለን፡፡ ከሁሉም የሚከፋውና የሚገርመው ግን ጥላቻ ከትዕቢት ወይም ከቅናት የሚመነጭ መሆኑን ነው፡፡ አንድ ሰው ጥሩ ዕድል ቢያጋጥመው በሥነ-ምግባሩ ወይም ደግሞ በሞያው ቢወደድና  ቢመሰገን ቀንተን እንጠላዋለን፡፡ ስሙንም ለማጥፋት ያሳስለሰ ጥረት እናደርጋለን፡፡

አንድ ሰው በትጋቱ ያገኘውን ሽልማት ስንመለከት በቅናት አንቃጠላለን፡፡ አንድ ሰው ስላላከበረንና ስላላመሰገነን ተናደን እንጠላዋለን፡፡ ጥላቻ ቂምንና በቀልን፣ ጥልን፣ አምባጓሮን በማስከተል አንደተቀበረ ፈንጂ ይፈነዳል፡፡ ደም መፍሰስና አካል መጉደል፣ከዚህ የባሰን እስከመጋደልም ያደርሳል፡፡ጥላቻ ልባችንና አዕምሮአችን ከተቆጣጠረ እንደ እንሰሳም ያደርገናል፣ወደ አውሬነት ይለውጠናል፡፡ውስጣዊ ሰላምና የልብ እረፍት ያሳጣናል፡፡ጥሩና በጐውንም በማሰብ ፋንታ መጥፎና እርኩሱን ምግባር እንድንአስብ ያደርገናል፡፡

ጥላቻ በባልንጀራችንና በእኛ ላይ የሚያመጣው መዘዝ ብዙ ነው፡፡ በጥላቻ በምንመረዝበ ጊዜ የተበደልን እንጂ የበደልን አይመስለንም እኔ ሰላም ፈላጊ ነኝእንላለን፡፡የተጣለውን ሰው በምናገኘው ጊዜ ሰላም ልንለው አንፈልግም &በተቻለን መጠን ከእርሱ ልንርቅ እንፈልጋለን፡፡

እንደዚህ በጥላቻ ተመርዘን ንጹሐንና በመልካም መንፈስ ያለን ይመስለናል፡፡ ከባልንጀራችንን ጋር ተጣልተን ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በሰላምና በፍቅር ያለን በማስመሰል እግዚአብሔርን «ማረን ልንለው እንደፍራለን፡፡ጸሎት እያደረግን ምስጢራትንም ለመሳተፍ እንፈልጋለን፡፡ የባልንጀራችን ጥላቻ በልባችን ውስጥ እያለ እንዴት «ንጹሐን ነን ለማለት እንደፍራለን; እንዴት ንጹሕ ልብ ያለን መስሎ ይታየናል;እንዴትስ ንጽህ ልብ  ሳይኖረን «ማረኝ ልንለው እንደፍራለን; ጸሎታችን በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ተቀባይነት ሊኖረው ይችላል?

እንግዲህ ከባልንጀራችን ጋር ከተጣላን ከእግዚአብሔር ጋርም ተጣልተናል ማለት ነው፡፡ እኛ ባልጀራችንን ይቅር ካላልን ወይም ምሕረት ካላደረግንለት እግዚአብሔርም ደግሞ ምሕረት እያደርግልንም፤ይቅርታ እንደማናገኝና በኃጢአት ላይ ያለን መሆናችን ጥርጣሬ የሌለው ሐቅ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በመልእክቱ «ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍስ ገዳይ ነው” (1ኛ ዮሐ.3፣15) ይላል፡፡ ፍቅር የእግዚአብሔር ነው፣ ጥላቻ ግን የዲያብሎስ ነው ጥላቻን የሚከተል ሁሉ ዲብሎስን ይከተላል። ደያብሎስን የሚከተል ይጠፋል&ፍቅርን የሚከተል እግዚአብሔርን ይከተላል ከእርሱ ጋርም በሰማይ ይነግሣል።

እኛ የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ጥላቻን ትተን ፍቅርን እንልበስ፡፡ ለጥላቻ አንሸነፍ ጥላቻን በፍቅር እናሸንፈው፡፡ ለሚበድሉን መልካም እናድርግላቸው እንጂ በጥላቻ ተመርዘን እንበቀላቸው።(ሮሜ 1ዐ፣21) በሙሴ ሕግ «ባልንጀራን ውደድ ጠላትህን ጥላ እንደተባለ ሰምታችኋል፤ እኔ ግን እላችኋለሁ … ጠላቶቻችሁን ውደዱ የሚረግሙአችሁንም መርቁ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለማያሳድዱአችሁም ጸልዩ…”ማቴ.5፣43-45” እያለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል።

15 June 2020, 13:35