የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ 

ትንቢታዊ አስተሳሰቦች (እ.አ.አ ከ1978-2005)

ክፍል ዐስር 

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች፣ ከእዚህ ቀደም በነበሩን ዝግጅቶቻችን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ አራት ዋና ዋና የታሪክ ሂደቶችን አልፎ ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ላይ መድረሱን መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን ከእነዚህ ደረጃዎች መካከል የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕዮተ ዓለም (እ.አ.አ 1891-1931) እና አዲስ የክርስቲያን አስተሳሰብ (እ.አ.አ. 1931-1958) እና አዎንታዊ አስተሳሰቦችን ከሚያራምዱ ማኅበራዊ አካላት ጋር ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል የሚሉትን ሦስቱን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ ያለፈባቸውን የታሪክ ሂደቶች በቅደም ተከተል በአጭሩ ከእዚህ ቀደም ማቅረባችን ይታወሳል። በዛሬው እለት የክፍል ዐስር ዝግጅታችን ደግሞ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ ያለፈበትን አራተኛውን የታሪክ ሂደት እንደ ሚከተለው በአጭሩ እናስቃኛችኋለን፣ እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

ትንቢታዊ አስተሳሰቦች (እ.አ.አ ከ1978-2005)

በእነዚህ አመታት ውስጥ ዓለማችን ከፍተኛ የሚባል የቴክኖሎጂ ምጥቀት ያሳየበት ወቅት እንደ ሆነ የሚታወስ ሲሆን ከዚህ የቴክኖሎጂ አብዮት ጋር ተያይዞ የመጣው የመድበለ ዘር ምንድስና ቴክኖሎጂ የሰው ልጅ ተፍጥሮኣዊ ባሕሪን በሚቃረን መልኩ የሚያደርገውን ጥናት እና ምርምር በስነ-ምግባር ሕጎች የተመራ እንዲሆን ለማሳሰብ የተለያዩ ሐዋሪያዊ መልእክቶች የተጻፉበት ወቅት ነው።

በዚህ አግባባ ከፍተኛ የሆነ አዎንታዊ አስተዋጾ ካበረከቱት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሱት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ እንደ ነበሩ የሚታወቅ ሲሆን በጵጵስናቸው ዘመን በላቲን ቋንቋ Laboremexercens፣Sollicitudine re socialis፣ Centesimusannus በመባል የሚታወቁትን ሐዋርያዊ መልእክቶችን በማስተላለፍ በመድብለ ዘር ምድስና ቴክኖሎጂ ምክንያት በሰው ልጆች ተፈጥሮኣዊ ማንነት ላይ ተቃቶ የነበረውን ከፍተኛ አደጋ በከፊልም ቢሆን ለመከላለከል ያደርጉት ጥረት በከፍተኛ ደረጃ የምያስመሰግናቸው እንደ ሆነ ይገለጻል። ከዚያም በመቀጠል ከዚህ ቀደም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስታ የነበሩት እና ከ7 አመታት በፊት በገዛ ፈቃዳቸው በእርጅና ምክንያት መንበራቸውን የለቀቁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በኔዴክቶስ 16ኛ በላቲን ቋንቋ Caritas in veritate በእውነት ላይ የተመሰረት ፍቅርን በተመለከተ ለንባብ ባበቁት ሐዋርያዊ መልእክት የመድበለ ዘር ምድስና ቴክኖሎጂ ከአሁኑ ጥንቃቄ ካልተደረገበት በሰው ልጆች ሰብኣዊ እልውና ላይ ለወደፊቱ ከፍተኛ ጫና የሚያስከትል በመሆኑ ከወዲሁ ሊታሰበብት የሚገባው ጉዳይ ሊሆን እንደ ሚገባው የሚገልጽ ሐዋርያዊ መልእክት ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል።

05 May 2020, 17:36