በባንኮክ የድሆች መንደር፣ በባንኮክ የድሆች መንደር፣ 

በባንኮክ ከተማ ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ብዙ ሕይወት ሊጠፋ ይችላል ተባለ።

በታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ፣ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ድሃ ነዋሪዎች በሚገኙበት ኮልግ ቶይ ሠፈር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የበርካቶችን ሕይወት ሊያጠፋ እንደሚችን በከተማው የሚኖሩ ሚሲዮናዊ አባ አሌሳንድሮ ባሪ አስታወቁ። ሠፈሩ ቁጥጥር የማይደረግለት፣ ሕጻናት ያለ ቤተሰብ ቁጥጥር በየጎዳናው በብዛት የሚታዩበት መሆኑን የገለጡት አባ አሌሳንድሮ ለጊዜ ወረርሽኙ ያልተስፋፋ ባሆንም ከሚታየው ዝቅተኛ የጤና አጠባበቅ እና የማህበራዊ ርቀት አለመከበር የተነሳ ወረርሽኙ በአጭር ጊዜ ውስጥ በስፋት ሊዛመት የሚችል መሆኑን አስረድተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን 

ያልተሟሉ የሕክምና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት፣

ቤቶች እና መንገዶች በወረርሽኝ መከላከያ መድኃኒት የተረጩባቸው ቢሆንም በቂ እንዳልሆነ የገለጹት አባ አሌሳንድሮ በሚፈለገው መጠን የተሟሉ ባይሆንም በአቅራቢያው ሆስፒታሎች መኖራቸውን ገልጸው በመንደሩ ከሚኖረው የሕዝብ ቁጥር አንጻር ውረርሽኙ እንዳይሰራጭ ማድረግ የማይታሰብ መሆኑን አስረድተዋል።

ቤተክርስቲያን የምታሳየው ገደብ የሌለው ፍቅር፣

በድህነት ሕይወት ለሚሰቃይ የታይላንድ ሕዝብ ቤተክርስቲያን ዕርዳታ በማቅረብ ላይ መሆኗን የገለጹት አባ አሌአስንድሮ በአገሩ የሚገኙ ካቶሊካዊ ሀገረ ስብከቶች በመተባበር የትምህርት አገልግሎትን፣ የገንዘብ እና የሞራል ድጋፍን በማድረግ ላይ መሆኗን አስረድተዋል። ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አስቀድሞም ቢሆን ብዙ ቁጥር ያለው መሕመም የሚሰቃይ የአልጋ ቁራኛ እንዳለ የገለጹት አባ አሌሳንድሮ ከኮሮና ቫይረስ ወዲህ ከሥራ ገበታ የተሰናበቱት ሲታከልበት ችግሩ መባባሱን ገልጸው ቤተክርስቲያን ለእነዚህ በሙሉ የምታቀርበውን የምግብ ማዳረስ አገልግሎትን ማሳደጓን ገልጸዋል። ከምግብ ማዳረስ አገልግሎት በተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀንስ የሚያግዙ ቁሳ ቁሶችንም በበጎ ፈቃደኞች አማካይነት ለሕዝብ በማደል ላይ የሚገኙ መሆኑን አባ አሌሳንድሮ ገልጸዋል።

የብርሃነ ትንሳኤው በዓል አካባበር፣

ከታይላንድ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ትዕዛዝ መሠረት ምዕመናን የብርሃነ ትንሳኤውን መስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ከቤታቸው እንዲሳተፉ መደረጉን የገለጹት አባ አሌሳንድሮ ለማኅበራዊ ሚዲያ ምስጋና ይግባው ብለው፣ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ የኮልግ ቶይ ሠፈር ምዕመናን ሥነ ሥርዓቱን በተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛዎች አማካይነት የተከታተሉ መሆኑን ተናግረዋል።

16 April 2020, 18:22