የዐብይ ጾም ወቅት ሕይወታችንን  የምፈታተኑዋትን ነገሮች ለይተን የምናውቅበት ወቅት ነው! የዐብይ ጾም ወቅት ሕይወታችንን የምፈታተኑዋትን ነገሮች ለይተን የምናውቅበት ወቅት ነው! 

የዐብይ ጾም ወቅት ሕይወታችንን የምፈታተኑዋትን ነገሮች ለይተን የምናውቅበት ወቅት ነው!

በእዚህ በመጀመሪያ የዐብይ ጾም ሳምንት የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ማርቆስ 1፡12-15) መፈተን፣ መለወጥ እና መልካም ዜና የሚሉትን ሦስት ዋና ዋና ጭብጦችን ያቀርብልናል። ወንጌላዊው ማርቆስ “ወዲያውም መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ወደ በረሓ መራው፤ በሰይጣንም እየተፈተነ አርባ ቀን በበረሓ ቈየ። ከአራዊትም ጋር ነበር፤ መላእክትም አገለገሉት (ማርቆስ 1፡12-13) በማለት በዛሬው ወንጌል ስገልጽ እናያለን። ኢየሱስ የእዚህ ዓለም ተልእኮውን በያፍ ለመጀመር ያስችለው ዘንድ ለመዘጋጀት ወደ በረሃ ሄደ። ኢየሱስ መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት  አያስፈልገውም ነበር፣ ነገር ግን የሰውነት ባሕርይው የራሱ እና የአባቱን ፈቃድ በመፈጸም ለመታዘዝ ለእኛ ሳይቀር ፈተናዎችን ማለፍ የሚያስችለንን ጸጋ ለመስጠት በማሰብ በእዚህ ፈትና ውስጥ አለፈ። ይህ ኢየሱስ ያደርገው ዝግጅት የተመሰረተው ከክፉው መንፈስ ጋር ማለትም ከዲያብሎስ ጋር በተደረገ ግብ ግብ ነው። ለእኛም ቢሆን ይህ የዐብይ ጾም ወቅት መፈሳዊ “ጭንቀት” በውስጣችን የሚያድርበት፣ መንፈሳዊ ግብግብ የምናደርግበት፣ ክፉ የሆኑ መንፈሶችን በጸሎት እና በእግዚኣብሔር እርዳታ በብቃት የምንመክትበት፣  በእለት ኑሮዋችን ክፉ መንፈስ የምናሸንፍበት ወቅት እንዲሆን ተጠርተናል። እንደምናውቀው ክፉ መንፈስ በእኛ ሕልውና እና በአቅራቢያችን እየሠራ ይገኛል፣ ይህም በሁከት፣ ሌላውን ሰው በማግለል፣ ራሳችንን ለሌሎች ዝግ በማድረግ፣ በጦርነቶች፣ በኢፍትሃዊ ድርጊቶች እየተገለጸ ይገኛል። እነዚህ ነገሮች ሁሉ የክፉ መንፈስ ተግባር ውጤቶች ናቸው፣ ክፉ የሆኑ ነገሮች ናቸው።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ኢየሱስ በምድረ በዳ ከተፈተነ በኋላ ወዲያውኑ ወንጌልን መስበክ ጀመረ፣ ይህም ማለት የምሥራቹን  ቃል መስበክ ጀምረ፣ ይህም በዛሬው ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው ሁለተኛው ቃል ነው። የመጀመሪያወ “መፈተን” የሚለው ቃል ሲሆን ሁለተኛው ቃል ደግሞ “የምስራች ቃል” የሚለው ነው። እናም ይህ መልካም ዜና ሰው መንፈሳዊ ለውጥ ካመጣ በኃላ የሚያገኘው እምነት ነው። ይህም በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ በሦስተኛነት የተጠቀሰ ቃል ነው። ኢየሱስ “ጊዜው ደርሶአል፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች” በማለት ይሰብክ ነበር። ከእዚያም በመቀጠል “ ንስሓ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ” እያለ ይገስጻቸው ነበር (ማርቆስ 1፡15)፣ የእግዚኣብሔር መንግሥት ስለቀረበች በእዚህ መልካም ዜና እምኑ ይለናል። በህይወታችን ውስጥ ሁል ጊዜም መለወጥ ያስፈልገናል - በየቀኑ፣ ቤተክርስቲያናችን ይህንን መንፈሳዊ ለውጥ እንድናመጣ ሁሌም ትጋብዘናለች።

እንደ እውነቱ ከሆነ ሙሉ በሙሉ ወደ እግዚኣብሔር አምርተን አናውቅም፣ ስለእዚህም  አዕምሮአችንን እና ልቦናችንን ቀጣይነት ባለው መልኩ ወደ እርሱ እንዲያመራ ማድረግ ይኖርብናል። ይህንን ለማድረግ ወደ ተሳሳተ መንገድ ልመሩ የሚችሉ ነገሮችን ሁሉ፣ ለምሳሌም  ራስ ወዳድነትን ስውር በሆነ መንገድ በመቀስቀስ እኛን የሚያታልሉንን የተሳሳቱ እሴቶችን ለመተው ድፍረት ሊኖረን ይገባል። ይልቁንም በጌታ፣ በእርሱ መልካምነት እና እርሱ ለእያንዳንዳችን ባለው የፍቅር እቅድ ማመን አለብን። የዐብይ ጾም ወቅት የመጸጸቻ ወቅት ነው እንጂ የምናዝንበት ወቅት ግን አይደለም። የእኛን የራስ ወዳድነት መንፈስ፣ አሮጌውን ማንነታችንን፣ በጥምቀታችን ወቅት ባገኘነው ጸጋ ላይ ተመስርተን ቆራጥ የሆነ እርምጃ የምንወስድበት ወቅት ነው።

እውነተኛ  ደስት ሊሰጠን የሚችለው እግዚኣብሔር ብቻ በመሆኑ የተነሳ እውነተኛ ደስታን በሀብት፣ በጊዜያዊ ደስታ፣በስልጣን . . .ወዘተ ውስጥ እውነተኛ ደስታን በመፈለግ  ጊዜያችንን ማባከን ምንም ፋይዳ የለውም።

የእኛ ምኞቶች ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ የሚሆኑት በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ነው። ምክንያቱም ያ ወቅት የሰው ደኽንነት የሚረጋገጥበት እና የእግዚአብሔር ክብር የሚገለጥበት ወቅት ስለሆነ ነው። በእዚህ በመጀመሪያው የዐብይ ጾም ሳምንት ሰንበት ቀን ላይ በጥሞና እንድናዳምጥ እና ኢየሱስ ያስተላለፈው፣ ያቀረብልንን ጥሪ ተቀብለን መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት እና በወንጌል እንድናምን ይጋብዘናል። በእዚህ የመጀመሪያው የዐብይ ጾም ሳምንት ሰንበት እለት በዓለማችን ውስጥ ሰላም፣ ወንድማማችነት እና ፍትህ እንዲሰፍን ዓለምን በመለወጥ የእግዚኣብሔር ጸጋ በይበልጥ በመቀበል ወደ ትንሳኤው በዓል ጉዞ እንድናደርግ ጥሪ ያቀርብልናል።

እናታችን የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በእዚህ የዐብይ ጾም ወቅት የእግዚኣብሔርን ቃል በታማኝነት መፈጸም እንድንችል እና ኢየሱስ በምድረበዳ እንዳደረገው ያለማቋረጥ እንድንጸልይ ትርዳን። ይህ የማይቻል አይደለም። የእግዚኣብሔርን ፍቅር ለመቀበል እና ሕይወታችንን እና መላውን ዓለም ለመለወጥ የሚያስችለንን ሕይወት እንድንኖር በጸጋዋ ትርዳን።

ይህንን ዝግጅት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!
09 March 2020, 13:58