“ወንድ እና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፡ በትምህርት ቤት ውስጥ ሥርዓተ-ፆታን በተመለከተ የሚነሱ ጽንሰ-ሐሳቦች ላይ ወደ ሚደረጉ ውይይቶች የሚወስድ መንገድ” “ወንድ እና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፡ በትምህርት ቤት ውስጥ ሥርዓተ-ፆታን በተመለከተ የሚነሱ ጽንሰ-ሐሳቦች ላይ ወደ ሚደረጉ ውይይቶች የሚወስድ መንገድ”  

“ፆታ በግለሰብ ደረጃ የሚወሰን ነገር ሳይሆን በተፍጥሮ የሚገኝ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው”

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤቶችን የሚመለከተው ጳጳሳዊ ተቋም “ወንድ እና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፡ በትምህርት ቤት ውስጥ ሥርዓተ-ፆታን በተመለከተ የሚነሱ ጽንሰ-ሐሳቦች ላይ ወደ ሚደረጉ ውይይቶች የሚወስድ መንገድ” በሚል አርእስት አንድ ሰነድ በቅርቡ ይፋ መሆኑ ይታወቃል።  ይህ አዲሱ ሰነድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ሰብዓዊ ጾታን በተመለከተ ቀጣይነት ባለው መልኩ በመነሳት ላይ ላለው ክርክር የራሷን አዎናትዊ አስተዋጾ ለማደረግ ታስቦ የፋ የሆነ ሰነድ ሲሆን  ከሥርዓተ-ፆታ ርዕዮተ-ዓለማዊ አስተሳሰቦች ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሳቸው የተነሳ እነዚህን ተጋዳሮቶች  አዎንታዊ በሆነ መልኩ ለመፍታት ይረዳ ዘንድ ለማገዝ ታስቦ ይፋ የሆነ ሰነድ ነው።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“ወንድ እና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፡ በትምህርት ቤት ውስጥ ሥርዓተ-ፆታን በተመለከተ የሚነሱ ጽንሰ-ሐሳቦች ላይ ወደ ሚደረጉ ውይይቶች የሚወስድ መንገድ” በሚል አርእስት ይፋ የሆነው ሰነድ ዋና ዓላማው ወጣቱን  ትውልድ በትምህርት ዘርፍ እያገዙ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተቋማት በአሁኑ ወቅት በዓለማችን በከፍተኛ ደረጃ ብዙ ክርክር እየተደረገበት የሚገኘውን ስነ-ፆታን የተመለከቱ ጉዳዮችን ፍቅርን በተመለከተ አድማሰ ስፊ የሁኑ ትምህርቶችን ስልታዊ በሆነ መልኩ ለመስጠት ታስቦ ይፋ የሆነ ሰነድ ነው።

በተለይም ለካቶሊክ ትምህርት ቤቶች እና በክርስቲያን ራዕይ ተነሳሽነት በሚሰሩ በሌሎች ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ላይ ይውል ዘንድ ታስቦ የተዘጋጀ ሰነድ ነው፣ ለወላጆች፣ ለተማሪዎች፣ እና ለሰራተኞች; እንዲሁም ለጳጳሳት፣ ለካህናት እና ገዳማዊያን/ገዳማዊያት በተጨማሪም ለቤተክርስትያኗ እንቅስቃሴዎች እና ለምዕመናን ማኅበራት አገልግሎት ይውል ዘንድ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ይህንን ሰነድ ያዘጋጀው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤቶችን የሚመለከተው ጳጳሳዊ ተቋም በአሁኑ ወቅት በዓለም ደረጃ ጽነ-ፆታን በተመለከተ በአሁኑ ወቅት ያለውን “የተዛባ አስተምህሮ” ለማስተካከል ታስቦ ያዘጋጀው ሰንድ ሲሆን በተለይም በወንድና በሴት መካከል ያለው ተፈጥሮአዊ ልዩነት “በታሪክ እና በባሕል አማካይነት ብቻ” የተፈጠረ ልዩነት እንደ ሆነ አድርጎ በማቀረብ በወንድ እና በሴት መካከል ያለው ልዩነት ተፍጥሮአዊ ይዘት ያለው ልዩነት ሳይሆን፣ ነገር ግን በታሪክ እና በባሕል ሂደት ውስጥ የተፈጠረ ልዩነት አድርጎ በማቀረብ የተዛባ አመለካከት እንዲፈጠር እየተደረገ በመሆኑ የተነሳ ይህንን አደገኛ አስተሳሰብ ለማጥራት ታስቦ የተዘጋጀ ሰነድ መሆኑም ተገልጹዋል።

“በሴት እና በወንድ መካከል ያለው ልዩነት ተፈጥሮአዊ ሳይሆን በታሪክ እና በባሕል ሂደት ውስጥ የተፈጠረ ልዩነት ነው” በማለት በአሁኑ ወቅት በሰፊው እየተነዛ የሚገኘው ጽንሰ-ሐሳብ፣ በዚህ የተነሳ ፆታ ተፍጥሮአዊ ይዘት ያለው ሳይሆን በታሪክ እና በባህል ሂደት ውስጥ እየዳበረ የመጣ ጽንሰ-ሐሳብ በመሆኑ የተነሳ ፆታ የግለሰብ ምርጫ ነው፣ ገለሰቡ በሂደት ሊቀይረው የሚችል ነገር ነው” በማለት የተዛባ እና የተሳሳተ ጽንሰ-ሐሳብ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ በመምጣቱ የተነሳ ይህንን ወቅታዊ ተግዳሮት ለመፍታት እና ፆታ ተፍጥሮአዊ የእግዚኣብሔር ስጦታ በመሆኑ የተነሳ ማንም ሰው በፈለገው ጊዜ እና ወቅት ሊቀይረው የሚችለው ጉዳይ አለመሆኑን በስፋት የሚገልጹ እና ማብራሪያ የታከለባቸው ሐሳቦች የተካተቱበት ሰነድ ነው።

ይህ “ወንድ እና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፡ በትምህርት ቤት ውስጥ ሥርዓተ-ፆታን በተመለከተ የሚነሱ ጽንሰ-ሐሳቦች ላይ ወደ ሚደረጉ ውይይቶች የሚወስድ መንገድ” በሚል አርእስት ይፋ የሆነው ሰነድ አሁን ባለው ዘመናችን ስነ-ሕይወትን በተመለከተ እየተንጸባረቀ ያለውን የተዛባ እና የተከፋፈለ አስተሳሰብ ቤተሰባዊ መዋቅሮችን እያናጋ መምጣቱን የሚገልጹ ሐሳቦች የተካተቱበት ሰንድ ሲሆን ሰነዱ በላቲን ቋንቋ አሞሪስ ላኤቲሲያ በአማሪኛው የፍቅር ሐሴት ከሚለው እና በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተጻፈው ቃለ ምዕዳን በመጥቀስ ሰነዱ እንደ ገለጸው ይህ ፅንሰ-ሃሳብ ( “ፆታ ተፍጥሮአዊ ይዘት ያለው ሳይሆን በታሪክ እና በባህል ሂደት ውስጥ እየዳበረ የመጣ ጽንሰ-ሐሳብ በመሆኑ የተነሳ ፆታ የግለሰብ ምርጫ ነው፣ ገለሰቡ በሂደት ሊቀይረው የሚችል ነገር ነው”)  የሚለው ጽንሰ-ሐሳን ፆታ "በወንድና ሴት መካከል ካለው ተፍጥሮአዊ የሆነ ልዩነት በተለየ መልኩ፣ ፆታ ግላዊ ማንነት የሚወሰን እና ለስሜት ቅርብ በሆነ መልኩ የሚገልጽ ተለዋዋጭ በሆነ ስሜታዊ የሆኑ ቅርጾችን የሚያራምድ ነው” የሚለውን የተዛባ ጽንሰ-ሐሳብ በትምህት ፕሮግራሞችን እንዲካተቱ እና በሕግ ድንጋጌዎች ውስጥም ሳይቀር እዲካተቱ እያደረጉ መሆኑ ደግሞ ከፍተኛ አደጋ እያስከተለ እንደ ሚገኝ የሚገልጹ ሐሳቦች ተካተውበታል። በእዚህ የተነሳ ይህ አሁን ይፋ የሆነው አዲስ ሰንድ ስነ-ፆታን በተመለከተ ይህንን ከላይ የተጠቀሰውን ሐሳብ በመቃወም “በማዳመጥ፣ ምክንያታዊ በመሆን እና ገንቢ ሐሳብ ማቅረብ” በተሰኙ ሦስት መርሆች ላይ መሰረቱን ያደረገ ውይይት ማደረግ ይገባል የሚል አቋም የያዘ ሰነድ ነው።

12 June 2019, 16:11