በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር እያደገ መምጣቱ ተገለጸ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር እያደገ መምጣቱ ተገለጸ 

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር እያደገ መምጣቱ ተገለጸ

ዜኒት በመባል የሚታወቀው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የዜና መስጫ ማዕከል በመረጃ መረቡ ላይ ካሰፈረው ዘገባ ለመረዳት እንደ ተቻለው በአሁን ወቅት በዓለማችን ላይ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የሀገረ ስብከት ካህናት ቁጥር  415,792 መድረሱን በመረጃ መረቡ ላይ ያስፈረ ሲሆን፣ 54,599 የተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት እና ገዳማት ካህናት፣ 44, 566 ቋሚ ዲያቆናት፣ 682,729 ደናግላን፣ 3,264,768 ካታኪስቶች፣ 116,939 የዐብይ ዘረዓ ክህነት ተማሪዎች፣ 102,942 የንዑስ ዘረዓ ክህነት ተማሪዎች በዓለም ዙሪያ እንደ ሚገኙ ዜኒት ከተባለው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የዜና መስጫ ማዕከል ካወጣው መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን፣ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መንፍሳዊ አገልግሎትን በዓለም ዙሪያ በመሰጠት ላይ እንደ ሚገኙ ለመረዳት ተችሉዋል።

በቅድስት መንበር ስር የሚተዳደረው እና የካቶሊክ ቤተክርቲያን ምዕመናን ብዛት ቆጠራ ማዕከላዊ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በ2018 ዓ.ም ይፋ ካደረገው አመታዊ መረጃ ለመረዳት እንደ ተቻለው እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ2015-2016 ዓ.ም ባሉት ሁለት አመታት ውስጥ በተደረገው ጥናት በዓለማቀፍ ደረጃ እ.አ.አ 2015 ዓ.ም  1ቢሊዮን 258 ሚሊዮን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በዓለም ዙሪያ እንደ ሚገኙ የገለጸ ሲሆን ይህ አሀዝ በ1.1% በመጨመር  አሁንም እ.አ.አ በ2016 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር 1 ቢልዬን 299 ሚልዮን መድረሱን ለመረዳት ተችሉዋል።

በተያያዘ መልኩም በአሁኑ ወቅት በዓለማችን የሚገኘው የሕዝብ ብዛት በቁጥር እያደገ እንደ ሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ይህ በፍጥነት እያደገ የሚገኘው የዓለማችን የሕዝብ ቁጥር ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር ከመጨመር ጋር በንጽጽር ሲታይ የካቶሊክ ምዕመናን ሕዝብ ቁጥር መጨመር ልቆ እንደ ሚታይ ከወጣው መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህም አሀዛዊ በሆነ እና ለመረዳት በሚያስችል መልኩ ሲገለጽ እ.አ.አ በ2016 ዓ.ም የዓለም የሕዝብ ቁጥር በ17.67% መጨመሩ እና በተመሳሳይ አመት በዓለማቀፍ ደረጃ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር በ17.73 % ማደጉን እና ከአጠቃላይ ዓለም ሕዝብ ብዛት መጨመር ጋር በንጽጽር ሲታይ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር በ0.6% ብልጫ መደጉን ከወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

በቅድስት መንበር ስር የሚተዳደረው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ብዛት ቆጠራ ማዕከላዊ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በ2018 ዓ.ም ይፋ ካደረገው አመታዊ መረጃ ለመረዳት እንደ ተቻለው እ.አ.አ 2017 ዓ.ም በአፍሪካ አህጉር የሚገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ቀጣይነት ባለው መልኩ በቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በተቃራኒው ግን በአውሮፓ አህጉር የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በቁጥር እያነሱ መምጣታቸውን መረጃው በስፊው ያትታል።

በእዚህም መሰረት በአፍሪካ አህጉር የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ከአጠቃላይ በዓለም ዙሪያ ከምትገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር አኳያ ሲታይ 17.6 % የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በአፍሪካ አህጉር እንደ ሚገኙ በቅድስት መንበር ስር የሚተዳደረው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የምዕመናን ብዛት ቆጠራ ማዕከላዊ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በ2018 ዓ.ም ይፋ ካደረገው አመታዊ መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

እ.አ.አ በ2010 ዓ.ም በአፍሪካ አህጉር የነበረው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ሕዝብ ቁጥር 185 ሚልዮን እንደ ነበረ እና ይህ አሀዝ በስድስት አመት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ እ.አ.አ በ2016 ዓ.ም 228 ሚልዮን እንደ ደረሰ በቅድስት መንበር ስር የሚተዳደረው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የምዕመናን ብዛት ቆጠራ ማዕከላዊ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በ2018 ዓ.ም ይፋ ባደረገው አመታዊ መረጃ የገለጸ ሲሆን በእነዚህ አመታት ውስጥ ከፍተኛ የካቶሊክ ምዕመና ቁጥር መጨመር የታየባቸው የአፍሪካ አገራት በቅደም ተከተል ሲቀመጥ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፖብልክ፣ በናይጄሪያ፣ በሁጋንዳ እና በንጎላ የተመዘገበው የካቶሊክ ምዕመን ቁጥር ከፍተኛ እንደ ሆነ ከወጣው መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በተቃራኒው “አዛውንቱ አህጉር” በመባል በሚታወቀው የአውሮፓ አህጉር ግን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመና ቁጥር በ0.2% ቅናሽ ማሳየቱ የተገለጸ ሲሆን ይህም በዓለማቀፍ ደረጃ ካለው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን አጠቃላይ ቁጥር አንጻር ሲታይ በአውሮፓ አህጉር የሚኖሩ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን 22% እንደ ሆኑ ለመረዳት ተችሉዋል።

በእዚህም መሰረት በዓለማቀፍ ደረጃ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ብዛት በመቶኛ ሲቀመት ከፍተኛ የካቶሊክ ምዕመናን 48.6 % የሚገኙት በላቲን እና መካከለኛውን አሜርካ ጨምሮ በአሜርካ አህጉር ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ 22% በአውሮፓ፣ 17.6% በፍሪካ፣ 11% በኢስያ እና 0.8% በሆሺኒያ አህጉር እንደ ሚገኙ  በቅድስት መንበር ስር የሚተዳደረው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ብዛት ቆጠራ ማዕከላዊ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በ2018 ዓ.ም ይፋ ካደረገው አመታዊ መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ2010 -2016 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የነበረውን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ቁጥር በንጽጽር የተመለከተው በቅድስት መንበር ስር የሚተዳደረው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ብዛት ቆጠራ ማዕከላዊ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በ2018 ዓ.ም ይፋ ያደረገው አመታዊ መረጃ እንደ ሚያስረዳው የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት ቁጥር በ5% ማደጉን የገለጸ ሲሆን በእዚህም መሰረት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ቁጥር 5,353 መደርሱን መረጃው ያስረዳል።

በተጨማሪም ዜኒት የተባለው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የዜና መስጫ ማዕከል ድረ ገጽ ላይ ከወጣው መረጃ በአሁኑ ወቅት በዓለማቀፍ ደረጃ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚተዳደሩ 73,580 መዋለ ሕጻናት ውስጥ የሚማሩ 7,043,634 ሕጻናት እንደ ሚገኙ፣ 96,283 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ 33,516,860 ተማሪዎች እንደ ሚገኙ፣ በዓለም ደረጃ በሚገኙ 46,339 ሁለተኛ ደረጃ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቤቶች ውስጥ ደግሞ 19,760,924 ተማሪዎች የትምህርት እድል አግኝተው በመማር ላይ እንደ ሆኑ ዜኒት ካወጣው መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በተጨማሪም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በዓለም ደረጃ ለ2,477,636 የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እና 2,719,643 የዩኒቬርሲቲ ተማሪዎች የተለያየ ዓይነት ድጋፍ እያደርገች እንደ ምትገኝ ይታወቃል።

የሕክምና መስጫ ተቋማትን በተመለከተ ደግሞ በሁኑ ወቅት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ 5,158 ታላላቅ የሕክምና መስጫ ሆስፒታሎች እና 16,523 የጤና ክብካቤ መስጫ ጣቢያዎች  እንደ ሚገኙ እና የተለያየ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 1,221 ሆስፒታሎች እና 5,230 የጤና ክብካቤ መስጫ ጣቢያዎች  በአፍሪካ እንደ ሚገኙ ከዜኒት ድረ ገጽ ካገኘበው መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል። 

07 June 2019, 14:33