ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልኮች የሕይወታችን አንዱ ክፍል በመሆን ላይ የገኛሉ። ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልኮች የሕይወታችን አንዱ ክፍል በመሆን ላይ የገኛሉ። 

በዐብይ ጾም ወቅት በቀን ለ1 ሰዓት ያህል ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮቻችንን ከመጠቀም መጾም ይገባል!

አሁን የምንገኝበት ወቅት የዐብይ ጾም ወቅት እንደ ሆነ ይታወቃል። በዚህ የዐብይ ጾም ወቅት “በእውነተኛ ልብ እግዚኣብሔርን እንዳናመልክ ለማድረግ፣ ልባችንን በመጥፎ ነገሮች በመሙላት፣ ከእግዚኣብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት የሚያበላሹብንን ጣዖታት፣ ገንዘብ እና ምድራዊ የሆኑ የማያቋርጡ ፍላጎቶቻችንን በማስወገድ በዚህ የዐብይ ጾም ወቅት ልባችንን ከክፉ ነገሮች የምናጸዳበት የጸጋ ወቅት ሊሆን ይገባል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በዚህ የዐብይ ጾም ወቅት ጉዞ ላይ  በጣም አስፈላጊ ወደ ሆኑ ነገሮች መመለስ እንችል ዘንድ፣ ከግብዝነት እና ትክክለኛ ካልሆኑ ተግባራት እንቆጠብ ዘንድ የሚረዱንን ሦስት እርምጃዎችን እንወስድ ዘንድ ቅዱስ ወንጌል ሐሳብ ያቀርብልናል፡- እነዚህም ምጽዋዕት፣ ጸሎት እና ጾም ናቸው። ታዲያ እነዚህ ነገሮች ምንድናቸው? ምጽዋዕት፣ መጸለይ እና መጾም፦ እነዚህ ሦስቱ መንፈሳዊ ተግባራት በነው ሊጠፉ ወደ ማይችሉ ወደ ሦስት እውነቶች ይመልሱናል። ጸሎት ከእግዚኣብሔር ጋር፣ ምጽዋዕት ከባልንጀራዎቻችን ጋር እና ጾም ደግሞ ከራሳችን ጋር ተመልሰን  በአዲስ መልክ ሕብረት እንድንፈጥር ይረዱናል። እግዚኣብሔር፣ ባልንጀራ እና እኔው ራሴ፡ እነዚህ እንዲያው በከንቱ በነው የማይጠፉ እውነታዎች በመሆናቸው የተነሳ በእነዚህ ነገሮች ላይ አጥብቀን መሥራት ይኖርብናል።

ይህንን የዐብይ ጾም ወቅት ክርስቲያናዊ በሆነ መልኩ በማክበር መንፈሳዊ ትሩፋት ማግኘት እንችል ዘንድ የሚረዳ መልእክት የፓኪስታን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት መልእክት አስተለፈዋል። በፓኪስታን የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት በመልእክታቸው እንደ ገለጹት በዚህ በዐብይ ጾም ወቅት ከተለያዩ ምግቦች እና መጠጦች ከመታቀብ ባሻገር በእየለቱ በእጆቻችን ላይ ይዘን የምንጓዛቸውን እስማርት ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ባለመጠቀም ጾማችንን ማጠናከር እንደ ሚገባ መልእክት አስተላልፈዋል።

በፓኪስታን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የላሆር አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ሳባስቲያን ሻው አሁን የያዝነውን የዐብይ ጾም ወቅት አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት በዚህ በዐብይ ጾም ወቅት ከምግብ እና ከመጠጥ ባሻገር እኛን በተለያየ መልኩ ሊረብሹን የሚችሉ እና ሱሰኛ ሊያደርጉን የሚችሉትን ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በዚህ በዐብይ ጾም ወቅት መጾም እንደ ሚገባን ጥሪ አቅርበዋል።

“አሁን ባለንበት የቴክኖሎጂ ዘመን ከሰዎች ጋር ለመገናኘት ካለን ጉጉት የተነሳ እስማርት ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ሕዝቡ ከመጠን በላይ በመጠቅም ላይ እንደ ሚገኝ ኖሃው እናዳልቸው” የገለጹት በፓኪስታን የላሆር አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳሳ  የሆኑት ሳባስቲያን ሻው “ይህ ቴክኖሎጂ ብዙ እጅግ በጣም ብዙ የሚባሉ ጥቅሞች ያሉት ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን ከመጠን በላይ በሆነ መልኩ የምንጠቀም ከሆንን እለታዊ ሕይወታችንን በተለያየ መልኩ ሊረብሽ እና ሱሰኛ እንድንሆን የሚያደርገን ቴክኖሎጂ በመሆኑ የተነሳ” ምዕመናኖቻቸው በዚህ በያዝነው የዐብይ ጾም ወቅት ቢያንስ ቢያንስ በቀን ለአንድ ሰዓት ያህል እስማርት ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮቻቸውን ከመጠቀም እንዲጾሙ አሳስበዋል።

በፓኪስታን የላሆር ሊቀ ጳጳሳ የሆኑት ሳባስቲያን ሻው ባለፈው እሁድ በመጋቢት 01/2011 ዓ.ም የኢየሱስ ቅዱስ ልብ በመባል በሚታወቀው በፓኪስታን በሚገኘው ካቴዳራል ባሳረጉት መሳዋዕተ ቃዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “በዚህ የዐብይ ጾም ወቅት መንፈሳችንን ሊረብሹ የሚችሉትን ነገሮች በተለይም ደግሞ እስማርት የሆኑ የእጅ ስልኮችን መጠቀም በመቀነስ በተቃራኒው ደግሞ የመስቀል መንገድ ጽሎት እና መስዋዕተ ቅዳሴን ቢያንስ በሰንበት ቀን በመከታተል በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት የእጅ ስልኮቻችንን እንዳይረብሹን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል” ብለዋል።

የዐብይ ጾም ወቅት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት አገልግሎቱን በይፋ ከመጀመሩ በፊት ለአርባ ቀናት ያህል በበረሃ ውስጥ ጾሞ እንደ ነበረ ሁሉ፣ እኛም ክርስቲያኖች ይህንን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አብነት በመከተል በዚህ በያዝነው የዐብይ ጾም ወቅት በጸሎት፣ ንስሐ በመገባት፣ በጾም እና ምጽዋዕት በመስጠት መንፈሳዊ ለውጥ በማምጣት የጌታችን የኢየሱ ክርስቶስን ትንሳኤ በመንፈሳዊነት ለማክበር የምንዘጋጅበት የጸጋ ወቅት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

እንደ ማነኛውም የዓለማችን ክፍል በፓኪስታን የእስማርት ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮች አጠቃቀም ከቀን ወደ ቀን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሄዱ የሚታወቅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአገሪቷ 155.4 ሚሊዮን በላይ ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮች አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደ ሚገኙ ከስፍራው ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በአገሪቷ የሚገኘው አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር ደግሞ 197 ሚሊዮን ነው፣ ይህም በመቶኛ ሲሰላ 78% የፓኪስታን ሕዝቦች የተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮች ተጠቃሚዎች ናቸው ማለት ነው።

በፓኪስታን የላሆር ሊቀ ጳጳሳ የሆኑት ሳባስቲያን ሻው የዐብይ ጾም ወቅትን በማስመልከት ለምዕመኖቻቸው ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት እስማርት ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮች እንደ ማነኛውም ዓይነት አደንዣዥ ዕጽ ሰዎችን የመሳብ አቅም እንዳላቸው ገልጸው በተለይ ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው በመጸለይ ላይ እያሉ እንኳን ሳይቀር በእጅ ስልኮቻቸው አመካይነት መልእክት ሲልኩ እና መልእክት ሲቀበሉ በሰፊው እንደ ሚሰተዋል ገለጸው ይህም ይህ ቴክኖሎጂ ወጣቶችን ምነኛ ሱሰኛ እንዳደረጋቸው የሚያሳይ መረጃ ነው ብለዋል።

ወጣቶች በዚህ በያዝነው የዐብይ ጾም ወቅት እስማርት ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮችን በአግባቡ እና በመጠኑ በመጠቀም አብዛኛውን ጊዜያቸውን ጠቃሚ በሆን የሕይወት ጉዳዮች ላይ በማዋል፣ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ለመመርመር በቂ ጊዜ በመስጠት ይህንን የዐብይ ጾም ወቅት ትክክለኛ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በመንፈሳዊነት በማክበር መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት በሚያስችላቸው መንገድ ይህንን የጸጋ ወቅት መጠቀም እንደ ሚገባቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በፓኪስታን ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመጠቀም፣ በተለይ ምዕመናን በሚበዙባቸው የፋሲካ እና የገና ዓመታዊ በዓላት ወቅት ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮችን በመጠቀም ፎቶ ማንሳት ይሁን የተለያየ ተግባራትን መፈጸም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መከልከላቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህም ክልከላ በሥራ ላይ እንዲውል የተደረገው በአገሪቷ የተለያዩ የእስማርት ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮችን በመጠቀም በክርስቲያኖች ላይ በተለያዩ አጋጣሚዎች በጸሎት ስፍራዎች ላይ በርካታ የሆነ የሽብር ጥቃት በመፈጸሙ የተነሳ ሲሆን ይህ ክልከላ ተግባራዊ የሆነው ደግሞ ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ መልኩ እንደ ሆነ ጨምሮ ተገልጹዋል።

እስማርት ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮችን በጣቶቻችን በመነካካት ቢቻ በመጠቀም በርካታ መረጃዎችን በአፋጣኝ እና በተቀላጠፈ መልኩ መለዋወጥ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖሌቲካዊ . . .ወዘተ ጥቅም የሚያስገኝ መሆኑን በሚገባ እንደ ሚገነዘቡ የገለጹት በፓኪስታን የላሆር ሊቀ ጳጳሳ የሆኑት ሳባስቲያን ሻው ነገር ግን ከገደብ ያለፈ አጠቃቀም በተቃራኒው በተለይም ደግሞ በማኅበራዊ ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር በመሆኑ የተነሳ፣ ይህም ወጣት የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍልን በቀጥታ የሚነካ በመሆኑ የተነሳ፣ በተጨማሪም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ላይ ከዋለ ደግሞ ቤተሰብን እስከ ማፍረስ የሚድረስ ነገር በመሆኑ የተነሳ ገደብ ሊበጅለት እንደ ሚገባ ገልጸዋል።

15 March 2019, 15:04