የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ልዑካን ኢትዮጲያን ለመጎብኘት አዲስ አበባ ገቡ የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ልዑካን ኢትዮጲያን ለመጎብኘት አዲስ አበባ ገቡ 

የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ልዑካን አዲስ አበባ ገቡ

በብፁዕ አቡነ መንግሥተ አብ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ዘኤርትራ የተመራ ልዑካን የካቲት 5/2011 ዓ. ም. በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት በመገኘት ከብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ዘኢትዮጵያ ጋር ተገናኙ፡፡

የዚህ ዜና አቅራቢ ማክዳ ዮሐንስ-አዲስ አበባ

በሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ አቡነ ሙሴ የእምንድብር ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ አንጀሎ የሐረር ሀገረ ስበከት ጳጳስ ተገኝተዋል፡፡ ብፁዕነታቸውን እንኳን ደህና መጡ በማለት የክብር አቀባበል ያደጉላቸው ሲሆን ከብፁዕነታቸው ጋር የመጡትን ከፍተኛ የቤተክርስቲያን ልዑካን ተዋውቀዋል፡፡ በዚህም ጊዜ ክቡር አባ ሐጐስ ሐይሽ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ጠቅላይ ጸሐፊ ስለ ኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አጠቃላይ ሁኔታ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን የልዑካኑ ቡድን ከ21 ዓመታት በኋላ ለመጀሪያ ጊዜ ጽ/ቤታችን በመገኘታችሁ የተሰማኝ ደስታ አገልጻለሁ በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

በመቀጠልም ብፁዕ ካርዲናል ብፁዕነታቸውንና ልዑካኑን በማመስገን በኤርትራ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ታላቅ ናት ብለዋል፡፡ የሁለቱ ሀገር የጳጳሳት ጉባኤ ለሁለቱ አገራት መልካም ግንኙነት ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ መሆኑን ገልጸው “በእግዚአብሔር ፈቃድ ለዚህ ዕለት መብቃታችን ቀላል አይደለም ብፁዕነትዎ እኛን ለመጐብኘት በመምጣታት የተሰማን ደስታ ታላቅ ነው” በማለት ደስታቸውን በኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ስም ገልጸዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ መንግሥተአብም ከሁሉ በላይ እግዚአብሔርን አመስግነው የልዑካኑ ቡድን በኢትዮጽያ ከምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጋር ያለውን የተሳሰረ አንድነት የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

በኤርትራ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሐዋርያዊ ሥራ ሆነ በማህበራዊ ልማት አገለግሎት በምትችለው ሁሉ ከሕብረተሰቡ ጐን በመቆም ታላቅ ሥራ  እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከሁሉ በላይ ይህ በሁለቱ አገራት የተጀመረው የሰላም ግንኙት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሁንም ጸሎታችንን አናቋርጥ በማለት በድጋሚ ስለተደገላቸው አቀባበል ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

Photogallery

የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ልዑካን ኢትዮጲያን ለመጎብኘት አዲስ አበባ ገቡ
14 February 2019, 15:35