ለዓለም አቀፍ የወጣቶች በዓል የተዘጋጀ አርማ ለዓለም አቀፍ የወጣቶች በዓል የተዘጋጀ አርማ 

ለዓለም አቀፍ የወጣቶች በዓል የተዘጋጀው አርማ ትርጉም ይፋ ሆነ።

ለዓለም አቀፍ የወጣቶች በዓል በተዘጋጀው አርማ ውስጥ ቀይና ሰማያዊ ቀለማት አማካይነት የኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይና ፍቅር የተገለጠበት፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አልባሳት የሚታይበት፣ በዓሉ የሚከበርበትን አገር ባንዲራና አዋሳኝ የፓስፊክ ውቅያኖስን የሚያመላክት መሆኑ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ዘንድሮ ከጥር 14 እስከ ጥር 19 2011 ዓ. ም. ድረስ፣ በመካከለኛዋ የላቲን አሜርካ አገር በሆነችው ፓናማ፣ ለ34ኛ ጊዜ ለሚከበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች በዓል እንዲሆን ተብሎ የተዘጋጀው አርማ ትርጉሙ ይፋ መሆኑ ታውቋል። ለበዓሉ እንዲሆን ተብሎ የተዘጋጀው አርማ በውስጡ ሦስት ቀለማትን ያካተተ፣ የበዓሉን መንፈስ የሚገልጹ ስድስት ምልክቶችን የያዘ መሆኑ ታውቋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለዚህ ወር

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ለተጀመረው የጥር ወር ምዕመናን በያሉበት ሆነው በጸሎት እንዲተባበሩ በማለት ለወሩን የሚሆን የጸሎት ሃሳብ በቪዲዮ ምስል አማካይነት ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ይህም “ወጣቶች እና የማርያም አብነት” የሚል መሆኑን ይታወቃል። ከዚህም በተጨማሪ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድሮ ለ34ኛ ጊዜ በመካከለኛዋ የላቲን አሜርካ አገር በፓናማ ከጥር 14 እስከ ጥር 19 2011 ዓ. ም. ድረስ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የወጣቶች በዓል ምክንያት በማድረግ ባቀረቡት የጸሎት ሃሳብ ላይ፣ የበዓሉ መሪ ቃልም “እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” በማለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለእግዚአብሔር የገለጸችለትን መልስ፣ ከሉቃ 1፡38 የተጻፈውን ጠቅሰው ባስተላለፉት መልዕክታቸው ወጣቶች ይህን ዓለም አቀፍ በዓል በሚያከብሩበት ወቅት ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ሆነው የኢየሱስ ክርስቶስን ዕቅድ ማሰላሰል እንደሚገባ፣ እንዲሁም በዓለማችን ሰላም ይሰፍን ዘንድ እያንዳንዱ ምዕመን በጸሎት በመተባበር ለሰላም ግንባታ ጠንክረን መስራት እንደሚገባ ማሳሰባቸው ይታወሳል።       

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ሃሳብ መሠረት በማድረግ በፓናማ የስነ ሕንጻ ትምህርቷን በመከታተል ላይ የምትገኝ ወጣት ኣምባር ካልቮ ለዓለም አቀፍ ወጣቶች በዓል ባዘጋጀችው አርማ ውስጥ ቀይና ሰማያዊ ቀለማት አማካይነት የኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይና ፍቅር የተገለጠበት፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አልባሳት የሚታይበትና፣ በዓሉ የሚከበርበትን አገር ፓናማን የሚያዋስን የፓስፊክ ውቅያኖስን የሚያመላክት መሆኑ ታውቋል። የእነዚህ ቀለማት ውህደትና ቅርጽ ጠቅለል ተደርጎ ሲታይ ደግሞ የልብ ምስልም መጠቃለሉ ታውቋል።        

16 January 2019, 15:42