DRCONGO-ECONOMY-DAILY LIFE DRCONGO-ECONOMY-DAILY LIFE 

የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ጳጳስ ለንጹሃን ዜጎቻቸው ከለላ እንዲደረግላቸው ጠየቁ።

“በቤኒ ክፍለ ሃገር ከ2006 ዓ. ም. ጀምሮ ከአንድ ሺህ አምስት መቶ ዜጎች በላይ ተገድለዋል እንዲሁም ከ800 በላይ ተማርከዋል። የዩጋንዳ ዴሞክራቲክ ሃይሎች ጥምረት ተጠያቂ ነው”።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ምስራቃዊው ግዛት የተዛመተው የኢቦላ ወረርሽኝ እንዲሁም ከሽምቅ ተዋጊዎች በኩል የሚሰነዘር ጥቃት የዜጎችን ሕይወት አደጋ ላይ መጣሉን የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ጳጳስ አስታወቁ። የቡቴምቦ ቤኒ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሲኩሊ ፓሉኩ በአገሪቱ የሰሜን ምስራቅ አካባቢ ጸጥታን በማስከበር ተግባር ተሰማርቶ ለሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ሃይል ባቀረቡት ስሞታ፣ ጸጥታ አስከባሪ ሃይሉ በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የሕይወት መጥፋትና የንብረት መውደም እንዲያስቆም ተማጽነዋል።

ጳጳሱ ይህን ተማጽኖ ያቀረቡት ባለፈው ሳምንት የዩጋንዳ ሽምቅ ተዋጊዎች ድንበር ዘልቀው በመግባት በዴሞክራቲክ ኮንጎ የሰሜን ምስራቅ ግዛት ነዋሪዎች ላይ ጥቃት በመክፈት ቢያንስ 14 ነዋሪዎችንና 4 የመንግሥት ወታደሮችን ገድለው በመቶዎች የሚቆጠሩትን ከመኖሪያቸው ካፈናቀሉ በኋላ እንደሆነ ታውቋል። የዩጋንዳ ዴሞክራቲክ ሃይሎች ጥምረት የድንበር ከተማ ወደ ሆነችው ወደ ቤኒ ዘልቀው የገቡት ያለፈው ቅዳሜ እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል።

የቡቴምቦ በሊ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሲኩሊ ፓሉኩ ፊደስ ለተሰኘ የዜና ማሰራጫ ማዕከል እንዳስታወቁት የመንግሥት ባለስልጣናት የተጣለባቸውን አደራ በትክክል በወጣት እንዳለባቸው አሳስበው በማከልም የሕዝቡን ጸጥታ እንዲያስከብሩ፣ ዳር ድንበርንና የሃገሪቱን ሉዓላዊንት እንዲያስከብሩ ጥሪ አቅርበዋል። ጳጳሱ በተጨማሪም የዩጋንዳ ዴሞክራቲክ ሃይሎች ጥምረት ከ2006 ዓ. ም. ጀምሮ ከአንድ ሺህ አምስት መቶ ዜጎች በላይ ሕይወት መጥፋት እንዲሁም ከ800 በላይ ምርኮኞች ተጠያቂ ነው ብለዋል። ጥቃትን ያነጣጠሩት በክርስቲያኑ ማሕበረሰብና ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን በማበርከት ላይ ባሉ ሚሲዮናዊያን ላይ እንደሆነ አቡነ ሲኩሊ ፓሉኩ አስረድተዋል። የበኒ ክፍለ ሃገር የኢቦላ ወረርሽኝ የተከሰተበትና ባሁኑ ወቅት የዓለም ጤና ድርጅት በሥፍራው ተሰማርቶ የሕክምና አገልግሎትን በመስጠት ላይ እንዳለ ገልጸው እንደ ጤና ባለሙያዎች መረጃ መሠረት በበሽታ የተለከፉት ሰዎች ቁጥር 120 እንደደረሰ፣ የሞቱት ሰዎች ቁጥርም 70 መድረሱ ብጹዕ አቡነ ሲኩሊ ፓሉኩ ገልጸዋል።    

28 September 2018, 16:56