SYRIA-CONFLICT-DISPLACED SYRIA-CONFLICT-DISPLACED 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “በኢዲሊብ በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ሊከተል ይችላል”።

በሶርያ፣ ኢዲሊብ ክፍለ ሃገር በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ሊከተል ይችላል። በመሆኑም ሰላማዊ መፍትሄን ለማምጣ ጥረት በማድረግ ላይ ለሚገኙት ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰቦች በሙሉ ልባዊ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

“ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ!

ሌላው በዛሬው ዕለት በሐዘን ልብ የምናስታውሰው በሶርያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት፣ በኢዲሊብ ክፍለ ሃገር ነዋሪዎች ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ነው። በድጋሚ ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ፣ ለዲፕሎማቲክ አካላት፣ ለአስታራቂ ወገኖችና ሰላማዊ መፍትሄን ለማምጣ ጥረት በማድረግ ላይ ለሚገኙት ለዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የነፍስ አድን ድርጅቶች በሙሉ ልባዊ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

በዚህ አደባባይ ላይ ለተገኛችሁ፣ በኢጣሊያ ውስጥ ከተለያዩ ክፍላተ ሃገር እንዲሁም መንፈሳዊ ንግደት ለማድረግ ከሌሎች አገሮች ለመጣችሁ በሙሉ ሰላምታዬን አቀርባለሁ።  በተለይም የካየራኖ ቅዱስ ማርቆስ የትምህርተ ክርስቶስ መምህራንን፣ ከሞንቲሮነ፣ ከሮቫቶ የመጣችሁትን ወጣቶች፣ ረጅም መንገድ በመጓዝ ከተለያዩ የስፔን ከተሞች የመጣችሁትን ምዕመናንና እንዲሁም ከሩቅ ለምትታዩኝ የቨስፓ ሞተር ብስክሌት ጉዞ ተካፋዮች በሙሉ ሰላምታዬን አቀርባለሁ።

ለሁላችሁም መልካም ሰንበትን እመኝላችኋለሁ። እባካችሁ በጸሎታችሁ ሳትዘነጉ አስታውሱኝ”። በማለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙት በሙሉ መልካም ጊዜን ተመኝተውላቸዋል።       

03 September 2018, 17:35