2018.08.30 Anna Kolesarova 2018.08.30 Anna Kolesarova 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቺስኮስ “ወጣት ሐና ኮለሳሮቫ፣ ለበርካታ ክርስቲያን ወጣቶች መልካም ምሳሌ ሆናለች”

“ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ!

በምስራቅ አውሮጳ አገር በሆነችው በስሎቫኪያ፣ ሊፈጸምባት የተሞከረውን ወሲባዊ ጥቃት አሻፈረኝ በማለት ሰብዓዊ ክብሯንና ክብረ ንጽሕናዋን ጠብቃ ለሰማዕትነት የበቃች፣ የስሎቫኪያ ተወላጅ ሐና ኮለሳሮቫ፣ ብጽዕት እንደሆነች ያለፈው አርብ ዕለት ነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ. ም. በመላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ዘንድ መታወጁ ይታወሳል። ይህች ወጣት እንደ ኢጣሊያ አገር ተውላጅ ከሆነች ከማርያ ጎረቲ ጋር ልትመሳሰል ትችላለች። ደፋር ወጣት ሐና ኮለሳሮባ፣ ለበርካታ ክርስቲያን ወጣቶች፣ ምንም እንኳን የሕይወት መስዋዕትንትን የሚያስከፍል ቢሆንም፣ ለወንጌሉ ቃል ያላቸውን ታማኝነት ጠብቀው እንዲገኙ ታግዛቸዋለች።

በዚህ አደባባይ ላይ ለተገኛችሁ፣ በኢጣሊያ ውስጥ ከተለያዩ ክፍላተ ሃገር እንዲሁም መንፈሳዊ ንግደት ለማድረግ ከሌሎች አገሮች ለመጣችሁ በሙሉ ሰላምታዬን አቀርባለሁ።  በተለይም የካየራኖ ቅዱስ ማርቆስ የትምህርተ ክርስቶስ መምህራንን፣ ከሞንቲሮነ፣ ከሮቫቶ የመጣችሁትን ወጣቶች፣ ረጅም መንገድ በመጓዝ ከተለያዩ የስፔን ከተሞች የመጣችሁትን ምዕመናንና እንዲሁም ከሩቅ ለምትታዩኝ የቨስፓ ሞተር ብስክሌት ጉዞ ተካፋዮች በሙሉ ሰላምታዬን አቀርባለሁ።

ለሁላችሁም መልካም ሰንበትን እመኝላችኋለሁ። እባካችሁ በጸሎታችሁ ሳትዘነጉ አስታውሱኝ”። በማለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙት በሙሉ መልካም ጊዜን ተመኝተውላቸዋል።          

03 September 2018, 17:16