manifesto Rimini Meeting 2018 manifesto Rimini Meeting 2018 

ኢየሱስ ክርስቶስ የዘለዓለም አምላክ ነው!

ብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ የሕይወት ታሪካቸውን የሚገልጽ መጽሐፍ ለንባብ አድርሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ ይህን የገለጹት በሰሜን ምስራቅ ኢጣሊያ ከተማ በሆነችው በሪሚኒ ሲካሄድ የቆየው ዓመታዊ ስብሰባ በተገባደደበት በትናንትናው ዕለት መሆኑ ታውቋል። ብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ በዕለቱ የግል ሕይወት ታሪካቸውን የሚገልጽ መጽሐፍ ለንባብ ማድረሳቸው የታወቀ ሲሆን ከቫቲካን የዜና አገልግሎት፣ የጣሊያንኛ ቋንቋ ዝግጅት ክፍል ጋርም ቆይታ አድርገዋል።

ካርዲናል አንጀሎ፣ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በኢጣሊያ የነጻነትና የአንድነት እንቅስቃሴ መስራች ከሆኑት ከአባ ሉዊጂ ጁሳኒ ጋር የነበራቸውን የሥራ ጊዜን በማስታወስ ባሰሙት ንግግር ከአባ ሉዊጂ ጋር ከልጅነት ዕድሜ ጀምሮ ለአንድ ዓላማ ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰው፣ በእነዚህ ዓመታት ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወታቸው መሪ እንደነበር ተናግረው ዛሬም ቢሆን ነገ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወታቸው መሪ መሆኑን አያቋርጥም ብለው፣ ይህን በግልጽ በማስረዳት ክቡር አባ ጁሳኒ በቂ ጥበብና ችሎታ አላቸው ብለዋል።

ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊና ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ጋር የነበረው ግንኙነት፣

የስነ መለኮት ትምህርት አዋቂ የሆኑት ክቡር አባ ሉዊጂ ጁሳኒ በቅድስት መንበር የሕዝቦች እምነት ጉዳይ ጳጳሳዊ ምክር ቤት አማካሪ በመሆን ባገለገሉባቸው ዓመታት ውስጥ ማለትም ከ1963 ዓ. ም. ጀምሮ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊና ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ጋር የነበራቸው ግንኙነት፣ ዓለም አቀፋዊ ሕብረት የተሰኘ መጽሔት ማሳተም እንዲጀምሩ መልካም አጋጣሚ እንደሆናቸው ብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ ገልጸዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቤተክርስቲያን ተስፋ ናቸው፣

ብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ በንግግራቸው እንደገለጹት ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር ያላቸው ግንኙነት፣ የቅዱስ ዮሐንስ ዘ ላተራን ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ አስተዳዳሪ ሆነው ካገለገሉበት ዓመት ጀምሮ የዘለቀ እንደሆነ አስታውሰው፣ በተለይም በቅድስት መንበር ጳጳሳዊ ምክርቤቶች የአገልግሎት ዓመታትና በጳጳሳት ሲኖዶስ ወቅትም የነበራቸው ግንኙነቶች ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን የበለጠ እንዳውቃቸው አግዞኛል ብለዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅት በነበራቸው የሐዋርያዊ አገልግሎት ዓመታት ቤተክርስቲያንን የሚያሳድጉ ሃሳቦችን በማፍለቅ የሚታወቁ ገልጸው እነዚህ የቅዱስነታቸው ሃሳቦች መላዋ ቤተክርስቲያናችንን በማገዝ ወደ ተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚያደርሳትና በዘመናችን ካጋጠማት ችግሮች እንድትወጣ የሚያግዛት እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ወሲባዊ ጥቃቶችን በተመለከተ፣

ብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ ከቫቲካን ዜና አገልግሎት፣ የጣሊያንኛ ቋንቋ ዝግጅት ክፍል ጋር ባደረጉት ረጅም ቃለ ምልልስ ወቅት እንደገለጹት፣ ቤተክርስቲያንን እያስጨነቃት ያለውና በአንዳንድ የቤተክርስቲያን አባቶች ወሲባዊ ጥቃቶች ለመሸፈን ያደረጉት ጥረት በእርግጥም ስህተት እንደነበር ገልጸው፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅርቡ “የእግዚአብሔር ሕዝብ” በማለት መልዕክት ማስተላለፋቸውን ብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ ገልጸዋል። ይህንና ቤተክርስቲያን ከወደቀችበት ከዚህ ችግር ለመውጣት በምታደርገው ጥረት በርካታ እርምጃዎችን መውሰድዋንና በመውሰድም ላይ እንነምትገኝ ጠቁመው ጊዜ ይውሰድ እንጂ በጋራ በመሥራት ወደ መልካም ጎዳና የሚመልስ ተስፋ አለ ብለው የቤተክርስቲያን ቅድስና በልጆችዋ ስህተት የተነሳ ሊጠፋ ወይም ሊፋቅ አይችልም ብለዋል።

በሪሚኒ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ስብሰባ መንደርደሪያ ርዕስ “ታሪክ ቀጣይነት እንዲኖረው እና የሰው ልጅም እውነተኛ ደስታን እንዲያገኝ የሚያደርግ አንድ ሃይል እግዚአብሔር ብቻ ነው።” የሚል ሲሆን ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን፣ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ለስብሰባው በላኩት መልዕክታቸው እንዳስገነዘቡት፣ በርካታ ምዕመናን የተሻለ ዓለምን እውን ለማድረግ ከእምነታቸው በሚያገኙት ጸጋ እንደሚተማመኑ ገልጸው በሌላ ወገን ደግሞ ዓለም ለሰው ልጅ የተሻለ የመኖሪያ ስፍራ ለማድረግ የነበረው ምኞት ዓለም የሰውን ልጅ በሙሉ የሚያገናኝ ድልድይን ከመገንባት ይልቅ የሚከፋፍል ግድግዳን መገንባት ስለመረጠ የሚመኘውን ሕይወት እውን ማድረግ አልቻለም ብለዋል።  

23 August 2018, 17:17