ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የፋሲካን በዓል በደስታ ማክበር ይገባል

በመጋቢት 23/2010 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ለሮም እና ለመላው ዓለም ያስተላለፉት መልእክት።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ የመጋቢት 23/2010 ዓ.ም. ድምቀት ተከብሮ ማለፉ ይታወሳ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በእዛሬው እለት ረፋዱ ላይ Urbi et Oribi ለከተማው (ለሮም) እና ለዓለም በተሰኘው የፋሲካ ቀን መልእክት ማስተላለፋቸው ተገልጹዋል።

በታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት በተለይም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት የገና በዓል ቀን እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በተነሳበት የትንሳኤ ቀን ልማዳዊ በሆነ መልኩ አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በላቲን ቋንቋ Urbi et Orbi በአማሪኛው ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም የተሰኘ መልእክት በዓላቱን አስመልክተው እንደ ሚያስተላልፉ ይታወቃል። በእዚህም መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የመጋቢት 23/2010 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ Urbi et Orbi በአምሪኛው ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም የተሰኘው መልእክታቸው የሚከተለውን ብለዋል።

ኢየሱስ ከሙታን ተንስቷል።

ይህ እየሱስ ከሙታን የተነሳበት እለት በመላው ዓለም በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ “ሃሌሉያ ጌታችን ኢየሱስ ስክርስቶስ ከሙታን ተንስቷዋል፣ አባቱ የሆነ እግዚኣብሔር ከሙታን አስነስቶት ለዘለዓለም በእኛ መሀል ይኖራል” የሚለው መዝሙር በታላቅ መንፈሳዊነት እይተዘመረ እንደ ሆነ ገልጸዋል።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሞቱ እና ስለትንሳሄው አስቀድሞ ተናግሮ እንደ ነበረ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንንም “እውነት እላችኋለሁ፤ የስንዴ ቅንጣት መሬት ላይ ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች’ በማለት ስለሞቱ እና ስለትንሳኤው አስቀድሞ ተናግሮ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ይህም ኢየሱስ የተናገረው ቃል በተግባር መፈጸሙን ያመለከቱት ቅዱስነታቸው እንደ አንድ የስንዴ ፍሬ በመሬቱ ውስጥ ለሁለት ቀናት ያህል ተቀብሮ በሦስተኛው ቀን ደግሞ ሁል ጊዜም ቢሆን ከእርሱ ግራ የነበረው የእግዚኣብሔር ኃይል ከሙታን እንዲነሳ እንዳደርገው እና እነሆ ዛሬ የፋሲካን በዓል በደስታ እንድናከብር ምክንያት ሆኖናል  ብለዋል።

“እኛ ክርስቲያኖች ይህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መሞት እና ከሙታን መነሳት የእኛ እና የዓለማችን እጣ ፈንታ እንደ ሆነ እኛ ክርስቲያኖች በሚገባ እንረዳለን” ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም የክርስቲያን ተስፋ ምንጭ ነው ብለዋል። ይህም ተስፋ የመነጨው ልክ እንደ አንድ የስንዴ ፍሬ ራሱን ለእኛ ሲል በፍቅር ዝቅ ባደረገው እና እስከሞት ድረስ ራሱን ታዛዢ ካደረገው ከጌታችን ከኢየሱስ መታዘዝ የመነጨ እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም ዓለም በስሙ እንዲታደስ እንደ ሚረዳ ገለጸዋል። ይህ ኢየሱስን ከሙታን እንዲነሳ ያደረገው ታላቅ ኃይል ዛሬም ቢሆን በዓለማችን ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የሚንጸባረቁትን ኢፍትሐዊነት እና ግጭቶች መፍትሄ እንደ ሚያስገኝ እና ሁሉም የሰው ልጆች ፍሬያማ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ የገለጹት ቅዱስነታቸው መገለል እና ስቃይ በበዛበት የማኅበረሰብ ክፍሎች ውስጥ፣ በረሃብ እና በስራ አጥነት የሚጎሳቆሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ውስጥ፣ በስደት ላይ ባሉ ሰዎች ሕይወት ውስጥ፣ በአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎች ምክንያት መከራ በደረሰባቸው የማኅበርሰበ ክፍሎች ውስጥ በአሁን በእኛ ዘመን በሚታየው በዘመናዊ ባርነት በሚሰቃዩ ሰዎች ሕይወት ውስጥ ይህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መነሳት ተስፋቸው እንዲለመልም እና ሰብዕዊ መብታቸውን እንዲጎጸፉ ማድረግ የሚችል ኃይል አለው ብለዋል።

እኛም ብንሆን ዛሬ የሰላም ፍሬ ውጤት የሆኑ ነገሮችን እንዲሰጠን እርሱን በመማጸን በተለይም ደግሞ ማብቂያ በሌለው ጦርነት እየተጎሳቆለች በምትገኘው በሶሪያ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ከሙታን የተነሳውን ጌታ መማጸን እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዚህ የፋሲካ ስሞን የትንሳሄው ብርሃን በፖለቲካ ኃላፊነት ላይ የሚገኙትን ሰዎች፣ በእዚህ ጦርነት ላይ የተሳተፉ ሰዎችን ሕሊና ያበራ ዘንድ እና ሰብዕዊ እርዳታ ለተጎጂዎ ይደርስ ዘንድ ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹ ቅዱስነታቸው በአደራ ጭምር ተማጽነዋል።

የኢየሱስን በድን ሽቶ ለመቀባት ወደ መቃብሩ በማለዳ ሴቶች በሄዱበት ወቅት “ለምን ሕያውን ከሙታን መካከል ትፈልጉታላችሁ! እርሱ እዚህ የለም ከሙታን ተንስቱዋል” (ሉቃስ 24፡5-6) ብሎ መላእክቱ ለሴቶቹ እንደ ተናገረ ሁሉ እንዲሁም ለእኛ ክርስቲያኖች ሞት እና ፍርሃት የእኛ ክርስቲያኖች የመጨረሻ እጣ ፈንታችን እንዳልሆነ በእግዚኣብሔር ኃይል ብቻ ሊከናወን የሚችል ከሙታን የመነሳት ተስፋ እንዳለን ልንረዳ ይገባል እንጂ በፍርሃት ልንዋጥ አይገባም ብለዋል።

የእግዚኣብሔር መለኮታዊ ፍቅር  “ክፉን ነገር ማሸነፍ ይችላል፣ ኃጢኣታችንን ያጥባል፣ ለኃጢያተኛው ሰው ንጽዕናን ያጎናጽፋል፣ ለተስቃዩ ሰዎች ደስታን ይሰጣል፣ ጥላቻን ያስወግዳል፣ የኃያላንን ጉልበት እንዲገዛ ያደርጋል፣ መግባባትን እና ሰላምን እንድንጎናጸፍ ያደርጋል ብለዋል።

08 July 2018, 15:17