የማላዊ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት እና የምርጫ ዝግጅት የማላዊ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት እና የምርጫ ዝግጅት 

የማላዊ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፣ በሃገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ወገናዊ እንደማትሆን አስታወቀች

የማላዊ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ለማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ተወዳዳሪ ግለ ሰብ ሳንወግን፣ ነገር ግን የሃገሪቱ ካቶሊካዊ ምዕመናን በሙሉ፣ ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ. ም. በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ላይ በንቃት እንዲሳተፍ እናደርጋለን ብለዋል።

የማላዊ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፣ በሃገሪቱ ሊካሄድ በታቀደው ብሔራዊ ምርጫ ወገናዊ እንደማትሆን አስታወቀች።

ቤተ ክርስቲያኒቱ ይህን መልዕክት ይፋ ያደረገችዉ፣ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ በቅርቡ ካካሄዱት ጠቅላላ የምክር ቤት ስብሰባ  ማግስት እንደሆነ ታውቋል።

የማላዊ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ለማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ተወዳዳሪ ሳንወግን፣ ነገር ግን የሃገሪቱ ካቶሊካዊ ምዕመናን በሙሉ፣ ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ. ም. በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ላይ በንቃት እንዲሳተፍ እናደርጋለን ብለዋል። የጳጳሳቱ ጉባኤ ይህን የጸና አቋሙን የገለጸው አመታዊ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ካካሄደባት ከዋና ከተማ ሊሎንጉዌ እንደሆነ ታውቋል።

የዚህ ዜና አዘጋጅ ዮሐንስ መኰንን

ብጹዓን ጳጳሳት ባወጡት የአቋም መግለጫቸው፣ በሃገሪቱ የካቶሊካዊት ቤት ክርስቲያን ካህናት፣ ገዳማዊያንና ገዳማዊያት፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ማሕበራዊ እና መንፈሳዊ ተቋማት ውስጥ በሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሰዎች በሙሉ ከማንኛውም ዓይነት የወገንተኝነት ተግባር እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። ቤተ ክርስቲያኒቱ በወገናዊነት መፈረጅ የለባትም ብለዋል። ጳጳሳቱ በማከልም የሃገሪቱ ዜጎች በሙሉ ቁጣን እና አመጽን የሚቀሰቅሱ ቃላትንና ተግባራትን በማስወገድ ምርጫው ሰላማዊ ምርጫ እንዲሆን እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ ያስፈልጋል ብለዋል። የብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ፣ ማላዊ ነጻነቷን ከተቀዳጀች ጊዜ ወዲህ የሰላምን ጸጋ የተቸረች አገር እንደሆነች አስታውሰው ይህን ጸጋ ዘላቂ ለማድረግ፣ የማላዊ ሕዝብ ተከባብሮ እና ተፋቅሮ በሰላም አብሮ በመኖር ሲሆን ይህም ከእግዚአብሔር እና ከሃገር የተላከ ግዴታ እንደሆነ አስረድተዋል። በተለይም ይህ ሰላም ሃገሪቱ በምታክሂደው ብሔራዊ ምርጫ ወቅት የተጠበቀ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።

ጳጳሳቱ በማከልም በሃገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ላይ መሳተፍ መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታም እንደሆነ አበክረው አሳስበዋል። ይህን በመገንዘብ የምርጫ አስተባባሪ አካላትም ትክክለ እና ፍትሐዊ የሆነ ምርጫ መካሄዱን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ማላዊ ከብሪታኒያ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን ከተቀዳጀችበት ከ1956 ዓ. ም. ወዲህ የመጀመሪያ የሆነውን ነጻ ምርጫን ያካሄደችው፣ በካሙዙ ባንዳ ዘመነ መንግሥት፣ በ1986 ዓ. ም. እንደሆነ ታውቋል። ማላዊ ከሌሎች አጎራባች አገሮች በተቃራኒ፣ አምባ ገነናዊ ሥርዓትን ያለፈች፣ አሁን ደግሞ በሙስና፣ በድርቅ፣ በረሃብ እና እያደገ በመጣው የኤይድስ በሽታ የምትሰቃይ ደሃ አገር መሆኗ ታውቋል።                 

09 July 2018, 13:22