ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ታዋድሮስ ዳግማዊ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ታዋድሮስ ዳግማዊ  

ፓትሪያርክ ታዋድሮስ ዳግማዊ፣ “ጸሎት ግጭቶችን የምንመክትበት የተሻለ መሣሪያ ነው”

ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በመሆን፣ የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ታዋድሮስ ዳግማዊ እና የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ፓትሪያርኮች በጋራ ሆነው፣ ጸሎት ግጭቶችን ለመመከት የሚያስችለን ዋነኛ መሣሪያ ነው፣ የሚል መልዕክት ለመላው ዓለም ሕዝብና ለዓለሙ ማሕበረ ሰብ ለማስተላለፍ መዘጋጀታችው ታውቋል።

ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ታዋድሮስ ዳግማዊ፣ “ጸሎት ግጭቶችን የምንመክትበት የተሻለ መሣሪያ ነው”

ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በመሆን፣ የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ታዋድሮስ ዳግማዊ እና የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ፓትሪያርኮች በጋራ ሆነው፣ ጸሎት ግጭቶችን ለመመከት የሚያስችለን ዋነኛ መሣሪያ ነው፣ የሚል መልዕክት ለመላው ዓለም ሕዝብና ለዓለሙ ማሕበረ ሰብ ለማስተላለፍ መዘጋጀታችው ታውቋል። ነገ ቅዳሜ ይህን መልዕክት ለመላክ የተዘጋጁት፣ ለአብያተ ክርስቲያናት አንድነት በሕብረት ሆነው ጸሎታችውን ወደ ፈጣሪ ዘንድ ለማቅረብ ከሚሰበሰቡበት ከደቡብ ኢጣሊያ፣ የፑሊያ ሀገረ ስብከት እንደሆነ ከሀገረ ስብከቱ የክርስቲያኖች ውሕደት አስተባባሪ ጽሕፈት የወጣ መግለጫ ገልጿል።

የዚህ ዜና አቀናባሪ ዮሐንስ መኰንን

ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ታዋድሮስ ዳግማዊ በንግግራቸው፣ ጸሎት፣ በዓለማችን ሰላምንና የእርቅን ለማውረድ በምናደርገው ጥረት፣ ግጭቶችን ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ሁሉ ብርሃን በመሆነን፣ ወደር የሌለውን ሃይል እንደሚሰጠን እናምናለን ብለዋል። ይህን ጽኑ እምነት በመያዝ፣ በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ጥሪ መሠረት ነገ ቅዳሜ ሰኔ ሰላሳ ቀን 2010 ዓ. ም. በደቡብ ኢጣሊያ ክፍለ ሀገር፣ በፑሊያ ሀገረ ስብከት፣ ለመካከለኛው የምስራቅ አገሮች ሰላም በሚደረገው የጸሎትና የአስተንትኖ ጉባኤ እንደሚገኙ ገልጸዋል።   የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ፣ ብጹዕ ወቅዱስ ታዋድሮስ ዳግማዊ፣ ሲር ለተሰኘ ክርስቲያናዊ የዜና ተቋም እንደገለጹት፣ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ተገናኝተው፣ በጦርነት ለተጎዱት የመካከለኛው የምስራቅ አገሮች መጸለይ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል። ብጹዕ ፓትሪያርክ ታዋድሮስ ዳግማዊ በማከልም፣ የአብያተ ክርስቲያናት በፍቅር እርስ በርስ መተባበር ለግንኙነታችንም አስፈላጊ ነው ብለዋል። በደቡብ ኢጣሊያ፣ ባሪ ከተማ ተገናኝተን የምናደርገው የጋራ ጸሎት፣ በእርግጥ በጦርነት ለሚሰቃዩ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ሕዝቦች መጽናናትን እንደሚያመጣላቸው ያላቸውን እርግጠኝነት ገልጸዋል። ፓትሪያርኩ በማከልም፣ መላው ዓለምም፣ የክርስትና እምነት በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ዘንድ ሥር የሰደደ መሆኑን እንዲገነዘብ እንፈልጋለን ብለዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ፣ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የክርስትና ባሕልንና ወግን ሌላው ዓለም በሚገባ ቢያውቀው መልካም ይሆናል ብለዋል። ችግሮቻችንን በፍቅርና መግባባት በተመላበት ሰላማዊ ውይይት ልንፈታቸው እንችላለን ብለዋል። 

በደቡብ ኢጣሊያ፣ የባሪ ቢቶንቶ ሀገረ ስብከት፣ የክርስቲያኖች ውሕደት አስተባባሪ ጽሕፈት ተጠሪ የሆኑት ክቡር አባ አልፍሬዶ ጋብርኤሊ ለተደረገላቸው ቃለ መጠይቅ እንደተናገሩት፣ ለመካከለኛው የምስራቅ አገሮች ሕዝቦች ሰላም እንዲወርድ አብያተ ክርስቲያናት በሕብረት ሆነን ካልጸለይን በስተቀር ክርስትናችንን ለዓለም ሕዝብ መመስከር አይቻልም ብለዋል።  ክቡር አባ አልፍሬዶ በማከልም፣ በዓለም ዙሪያ የክርስቲያኖችን መገኘት ዋና ትርጉም ማወቅ ያስፈልጋል ብለዋል። አብያተ ክርስቲያናት በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት እና በዓለም ዙሪያ የክርስቲያኖች መገኘት ምን ትርጉም እንዳለው ዓለም በሚገባ እንዲያውቅ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አጥብቀው ያሳስባሉ። ስለዚህ በሕብረት ሆነን ለመካከለኛው የምስራቅ አገሮች ሕዝቦች ሰላም በምንጸልይበት ጊዜ፣ በክርስቲያኖች መካከል አንድነት ከጠፋ የሰላም መስካሪዎች መሆን አንችልም ብለዋል ክቡር አባ አልፍሬዶ ጋብርኤሊ። በሕብረት በመሆን ለመካከለኛው ምስራቅ ሕዝብ ሰላም ለመጸለይ ወደ ባሪ ያደረግነው መንፈሳዊ ጉዞ፣ በዚያች ከተማ የሰላምና የእርቅ እንዲሁም የክርስቲያኖች አንድነት ምሳሌ የሆነው የቅዱስ ኒኮላ ቅዱስ አጽም የተቀመጠባት በመሆኑ የእርሱን ምሳሌ እንድንከተል መልካም አጋጣሚ ይሆናል ብለዋል። በዚያ ስፍራ ካቶሊኮች፣ ኦርቶዶክሶችና የወንጌላዊያን ሕብረት አንድ ላይ ሆነን ለጸሎት መሰብሰባችን ዓላማችንን ለማሳካት የሚያስችለንን ሃይል ያስገኛል ብለዋል።

የባሪ ቢቶንቶ ሀገረ ስብከት፣ የክርስቲያኖች ውሕደት አስተባባሪ ጽሕፈት ተጠሪ በመሆን የሚያበረክቱትን አገልግሎት አስመልክተው ክቡር አባ አልፍሬዶ ጋብርኤሊ ሲገልጹ፣ ክርስቲያን በመሆናችን በሕብረት መጸለይ፣ በሕብረት መስራት፣ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፣ በሕብረት በመሆን የጋራ መንገድ ስንጓዝ፣ የጋራ ግብ ሲኖረን ለእርቅ፣ ለእውነተኛ ሰላምና ፍቅር እንበቃለን ብለዋል።  ክቡር አባ አልፍሬዶ ጋብርኤሊ በማከልም የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች በር በመባል የምትታወቀው የሀገረ ስብከት ምእመናን፣ ስለ አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ያላቸውን አመለካከት ሲገልጹ፣ በከተማው ከ 1958 ዓ. ም. ጀምሮ የቅዱስ ኒኮላ ባዚሊካ፣ ለኦርቶዶክስ ምዕመናን ተበርክቶላቸው በስርዕእተ አምልኮ አቸው መስዋዕተ ቅዳሴን እንደሚያሳርጉ መመልከት በከተማው ምዕመናን ዘንድ የተለመደና የተወደደም እንደሆነ ገልጸዋል።    

06 July 2018, 09:55