ፈልግ

የሰሃል አገሮች መሪዎች የሰሃል አገሮች መሪዎች 

በሰሃል አገሮች ውስጥ 6 ሚሊዮን ሰዎች ለተመጣጣኝ ምግብ እጥረት እና ለረሃብ መጋለጣቸው ተነገረ

የሰሃል አገሮች በሚባሉ የሰሜን አፍሪቃ አገሮች፣ እነዚህም ቡርኪና ፋሶ፣ ቻድ፣ ማሊ፣ ማውሪታኒኣ፣ ኒጀር እና ሰነጋል፣ በተመጣጣኝ ምግብ እጦትና በረሃብ መጠቃቸውን ካሪታስ የተሰኘ ካቶሊካዊ በጎ አድራጊ የዕርዳታ ድርጅት አስታወቀ።

በሰሃል አገሮች ውስጥ 6 ሚሊዮን ሰዎች ለተመጣጣኝ ምግብ እጥረት እና ለረሃብ መጋለጣቸው ተነገረ።

የሰሃል አገሮች በሚባሉ የሰሜን አፍሪቃ አገሮች፣ እነዚህም ቡርኪና ፋሶ፣ ቻድ፣ ማሊ፣ ማውሪታኒኣ፣ ኒጀር እና ሰነጋል፣ በተመጣጣኝ ምግብ እጦትና በረሃብ መጠቃቸውን ካሪታስ የተሰኘ ካቶሊካዊ በጎ አድራጊ የዕርዳታ ድርጅት አስታወቀ።

የዚህ ዜና አዘጋጅ ዮሐንስ መኰንን

በእነዚህ አገሮች ውስጥ 6 ሚሊዮን ሰዎች ለረሃብና ለተመጣጣኝ ምግብ ማነስ መጋለጣቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያስታወቀ ቢሆንም፣ ቀውሱ እያደገ በመምጣቱ በአንዳንድ አካባቢዎች በጽኑ ረሃብ ምክንያት የሰዎች ሕይወት እያለፈ መሆኑን በአካባቢው በዕርዳታ አቅርቦት ሥራ ተሰማርተው የሚገኙ ሠራተኞች እና የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የወንጌ ልዑካን ገልጸዋል።

በአፍሪቃ አገሮች፣ የኢጣሊያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በጎ አድራጊ ድርጅት ወይም ካሪታስ ኢታሊያና አስተባባሪ የሆኑት አቶ ፋብሪሲዮ ካቫለቲ፣ ከ2004 ዓ. ም. ጀምሮ በሰሃል አገሮች ውስጥ ሰብዓዊ ቀውሶች እየተበራከቱ መምጣታቸውን አስረድተዋል። በከፍተኛ የተመጣጣኝ ምግብ ማነስ ምክንያት 1. 6 ሚሊዮን ሕጻናትን ለሞት አደጋ ተጋልጠዋል ብለዋል። አቶ ፋብሪሲዮ፣ ይህ የሆነበትን ምክንያት ሲገልጹ በአገሮቹ የሚታየው የአየር ንብረት መለወጥና የሕዝቦችን ኑሮ ያደከመዉ የፖለቲካ ቀውስ ነው ብለዋል። እነዚህ እና ሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች ተዳምረው በአገሮቹ ዘንድ የምግብ ዋስትንና አሽቆልቁሎታል ብለዋል። ባለፉት ዓመታት በሌሎች የአፍሪቃ አገሮች የተከሰቱትን ችግሮች ሲገመገሙ፣ የኒኞ ክስተት ውጤት ሲሆን አሁን ደግሞ የሰሃል አገሮችን እያጥቃ ያለው በቂና ተመጣጣኝ ምግብ ማነስ ነው ብለዋል።

የሰሃል አገሮችን የጸጥታ ሁኔታን የዘረዘሩት አቶ ፋብሪሲዮ፣ በአካባቢው ተሰማርቶ የሚገኘው የቦኮ ሃራም አሸባሪ ታጣቂ ሃይል፣ ከሰሜንና ደቡብ ምስራቅ ኒጀር፣ ከካሜሩን እና ከቻድ በመነሳት፣ የሽብር ጥቃት በመፈጸሙ የተነሳ ሕዝቡ ይህን ጥቃት ለማምለጥ አካባቢዉን ለቆ ለመሰደድ ተገዷል ብለዋል። ይህም በአገሮቹ የሚመረተውን የምርት መጠን ዝቅ አድርጎታል ብለዋል። ችግሩ ይባስ ብሎ ልጆች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል። በርካታ ሕጻናት በአሸባሪ ታጣቂዎች በመታገድ ለአስገዳጅ ሥራ ተዳርገዋል፣ እንዲሁም የቤት እንስሳት ተዘርፈው ተወስደዋል።

በየአገሮቹ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ተባብረው የእርዳታ አቅርቦትን በተለይም የምግብ እርዳታን ለማቅረብ እየሰሩ መሆኑን የእርዳታ አስተባባሪው አቶ ፋብሪሲዮ ካቫለቲ ገልጸዋል።

04 July 2018, 12:45