የክቡር አባ ጂልፍሬዶ ማረንጎ ጥናታዊ ጽሑፍ ታትሞ ወጣ የክቡር አባ ጂልፍሬዶ ማረንጎ ጥናታዊ ጽሑፍ ታትሞ ወጣ  

“የሰው ልጅ ሕይወት” የሚለው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ ሐዋርያዊ መልዕክት ጥናት ተደረገበት

ክቡር አባ ጂልፍሬዶ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ፣ ከ50 ዓመታት በፊት “የሰው ልጅ ሕይወት” በሚል ርዕስ ይፋ ባደረጉት ሐዋርያዊ መልዕክት ላይ ክቡር አባ ጂልፍሬዶ ማረንጎ ጥናት ማካሄዳቸው ታውቋል። የክቡር አባ ማረንጎ ሰፋ ያለ ጥናት፣ የቅዱስነታቸውን መልዕክት በማብራራት ለአንባቢዎች የበለጠ ግልጽ እንዲሆን አድርጓል።

ከ50 ዓመታት በኋላ፣ “የሰው ልጅ ሕይወት” የሚል የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ ሐዋርያዊ መልዕክት ጥናት ልዩ ተደረገበት።

ክቡር አባ ጂልፍሬዶ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ፣ ከ50 ዓመታት በፊት የሰው ልጅ ሕይወት በሚል ርዕስ ይፋ ባደረጉት ሐዋርያዊ መልዕክት ላይ ክቡር አባ ጂልፍሬዶ ማረንጎ ጥናት ማካሄዳቸው ታውቋል። የክቡር አባ ማረንጎ ሰፋ ያለ ጥናት የቅዱስነታቸውን መልዕክት በማብራራት ለአንባቢዎች የበለጠ ግልጽ እንዲሆን አድርጓል።

የዚህ ዜና አዘጋጅ ዮሐንስ መኰንን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ፣ ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ማግስት ለመላዋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና በጎ ፈቃድ ላላቸው ሰዎች በሙሉ፣ “የሰው ልጅ ሕይወት” በሚል አርዕስት ይፋ ባደረጉት ሐዋርያዊ መልዕክታቸው

"የሰው ልጅ በመዋለድ፣ ሕይወት እንዲበራከት ማድረግ፣ ሁለት ተቃራኒ ጾታዎች  ከእግዚአብሔር ጋር በመተባበር የሚደረጉት ሙሉ እና ነጻ ውሕደት በመሆኑ ትልቅ ሃላፊነትን ይጠይቃል። ይህ በሁለቱ ተቃራኒ ጾታዎች መካከል የሚደረግ ውሕደት ሃላፊነት የተጣለበት እና ከባድ ቢሆንም፣ ወደር የማይገኝለትን ደስታ ምንጭ ነው። ይሁንና የሰው ልጅ የደረሰበት የእድገት ደረጃ እና ያሳያቸው ለውጦች አንዳንድ ጥያቄዎችን ሳያስነሱ አልቀሩም። እነዚህ ጥያቄዎች ከሰው ሕይወት እና ደስታ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ስላላቸው ምን ጊዜም ቢሆን ቤተ ክርስቲያን ችላ ልትላቸው አይቻላትም።

በዘመናት መካከል የሰው ልጅ የተመለከታቸው ለውጦች ብዙ፣ ጠቃሚ እና የተለያዩ ናቸው። ከሁሉ አስቀድሞ የዓለም ሕዝብ በፍጥነት እየጨመረ መምጣቱ፣ ዓለም ለሰው ልጆች ከምታቀርበው የፍጆታ መጠን ጋር ሲመጣጠን እጅግ ጥቂት መሆኑ ስጋት ላይ ጥሏል። በዚህም ምክንያት በርካታ ቤተ ሰቦች በተለይም በማደግ ላይ ባሉት አገሮች የኑሮ ጫናን ማስከተሉ አይቀርም። በተጨማሪም ይህ ሁኔታ የመንግስት ባለሥልጣናትን አስቸጋሪ የሆኑ ውሳኔዎችን እንዲወስዱ ማሳሰቡ አልቀረም። ይህም የሥራ ዕድልንና በቂ መጠለያ አቅርቦትን ማመቻቸት ወይም ማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን ለበርካታ የቤተ ሰብ ክፍል ወደ በቂ እና ወደ ተሻለ የኤኮኖሚ እና የትምህርት ደረጃ ማድረስ አስቸጋሪ ይሆናል። ከዚህም ጋር ሊዘነጋ የማይገባው ሌላው ጉዳይ፣ በማሕበራዊ ኑሮ ውስጥ ለሴቶች የሚሰጠው ሰብዓዊ ክብር፣ የጋብቻን እሴቶች እና እውነተኛ ፍቅርን መሠረት በማድረግ በሁለት ጾታዎች መካከል ሊኖር የሚገባው ፍቅራዊ ግንኙነት ነው።

ይህ ሐቅ እያለ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ የሰው ልጅ የደረሰበትን አስገራሚ የበላይነት ደረጃን ስንመለከት፣ የተፈጣሮ ሕግጋትን ሳይቀር በቁጥጥሩ በማድረግ፣ በራሱን ሕይወት፣ አካል፣ አዕምሮ እና ስሜት ላይ ስልጣንን በመቀዳጀት፣ ከሁሉም በላይ የመዋለድ እና ሕይወት እንዲበራከት የማድረግንም ሥላጣን በግሉ በመያዝ ላይ መሆኑ ነው።

ይህን የመሰለ አዲስ እና እንግዳ የሆነ የሰው ልጅ አስተሳሰብ፣ አዳዲስ ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርጓል። የኑሮ ሁኔታዎችን በማገናዘብ፣ በፍቅር እና እርስ በርስ በመተማመን፣ በጋብቻ በተሳሰሩት ባል እና ሚስት መካከል የሚፈጠረውን አንድነትም በማሰብ፣ እስካሁን ያዛለቁንን፣ መልካም የሆኑ ማሕበራዊ ባሕላዊና እና ስነ ምግባራዊ እሴቶችን ሕግጋትን አሁን በደረስበት አስቸጋሪ ዘመን መለስ ብለን መመልከት እንዴት ይሳነናል?"

በማለት፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ በሐዋርያዊ መልዕክታቸው በኩል ጠይቀዋል።

“የሰው ልጅ ሕይወት” በሚል አርዕስት የሚታወቀው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ ሐዋርያዊ መልዕክት ይፋ ከመሆኑ አስቀድሞ ማለትም ከ1955 እስከ 1960 ዓ. ም. ድረስ አምስት አመታት እንደወሰደ ሲታወቅ፣ የታተመውም ሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 1960 ዓ. ም. እንደሆነ ታውቋል። ከሌሎች ሐዋርያዊ መልዕክቶች በተለየ መልኩ፣ በርካታ ምሁራን ለ50 ዓመታት ያህል ሰፋ ያለ ጥናት አድርገውበታል ተብሏል።

“የሰው ልጅ ሕይወት” በሚለው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ ሐዋርያዊ መልዕክት ላይ ሰፋ ያለ ጥናት ካካሄዱት ምሑራን መካከል ክቡር አባ ጂልፍሬዶ ማረንጎ አንዱ ናቸው። ክቡር አባ ማረንጎ ብሁኑ ጊዜ በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ጳጳሳዊ የነገረ መለኮት ኢንስቲቱት ውስጥ የጋብቻ እና የቤተ ሰብ ትምህርት መምህር ናቸው። ክቡር አባ ጂልፍሬዶ ማረንጎ፣ በቅርቡ ያሳተሙት መጽሐፍ አርዕስት፣ “የሰው ልጅ ሕይወት” የተሰኘው ሐዋርያዊ መልዕክት በቫቲካን ቤተ መዛግብት እይታ በመባል ይታወቃል። ይህ ሐዋርያዊ መልዕክት ሰፋ ያለ ጥናት እንዲደረግበ እና ግልጽ ማብራሪያ ተሰጥቶበት ለሕትመት እንዲበቃ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መልካም ፈቃድ ሆኗል። በሐዋርያዊ መልዕክቱ በርካታ ክርክሮች ተነስቶበታል፣ አስታያየቶችም ተሰጥተውበታል ያሉት ክቡር አባ ጂልፍሬዶ ማረንጎ፣ ሰፋ ያለ ጥናት እንዲደረግ የተፈለገበትም እነዚህን ክርክሮች ለማስወገድ ነው ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ፣ ባወጡት ሐዋርያዊ መልዕክታቸው፣

"እንግዳ የሆኑ የሰው ልጅ አስተሳሰቦችን እና ጥያቄዎቻቸውን በቸልታ መመልከት አያስፈልግም በማለት፣ ቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ እና የተፈጥሮ ሕግጋትን መሠረት ያደረጉ የጋብቻ የሚመለከቱ ትምህርቶችዋን የበለጠ እንድታስብ እና እንድታሰላስል አድርጓታል ብለዋል። ከምዕመናን መካከል ማንም ቢሆን፣ ቤተ ክርስቲያን ተፈጥሯዊ የሆኑ ስነ ሞራላዊ ትምህርቶችን በትክክል ማስረዳት ወይም መተንተን ይሳናታል ማለት አይችልም። ከዚህ በፊት የነበሩ የእምነት አባቶች፣ አበይት ነጥቦችን በግልጽ ተናግረዋል። አንደኛ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮታዊ ሃይሉ፣ ሐዋርያው ጴጥሮስ እና የተቀሩት ሐዋርያትን ወደ ዓለም ሁሉ እንዲሄዱ እና እንዲያስተምሩ ተናግሮአቸዋል። ሁለተኛ፣ እውነተኛ አስተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የተቀበሉትን ሞራላዊ የተፈጥሮ ሕግጋትን በትክክል የመተርጎምና የመጠበቅ አደራን ሰጥቷቸዋል። ሦስተኛ፣ የተሰጣቸው ሞራላዊ የተፈትሮ ሕግ በእግዚአብሔር ፈቃድ በመሆኑ ለሰዎች ዘለዓለማዊ ደህንነት አስፈላጊ መሆኑንም ገልጾላቸዋል። አራተኛ፣ ይህን ተልዕኮ ቤተ ክርስቲያን ጠንቅቃ በማወቅ፣ የጋብቻን ክብር የሚገልጹ፣ ምን ጊዜም ትክክለኛነቱን ያረጋገጠ የሁለት ተቃራኒ ጾታዎች ውሕደት ባልና ሚስት እንዲያከብሩ የሚጠይቁ ሰነዶችን ስታቀርብ ቆይታለች"

በማለት ሐዋርያዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።                                                   

“የሰው ልጅ ሕይወት” በሚል የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ ሐዋርያዊ መልዕክት ላይ ጥናታቸውን የጀመሩት መልዕክቱ ይፋ ከመሆነ ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በኋላ ነው ያሉት ክቡር አባ ጂልፍሬዶ ማረንጎ፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ሐዋርያዊ መልዕክት ይፋ በሆነበት ማግሥት በርካታ ክርክሮች መነሳታቸውን አስታውሰው፣ ይህ ሐዋርያዊ መልዕክት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ያወጣውን ሰነድ በመመርኮዝ በቂ ማብራሪያ ተሰጥቶበት ለሕትመት ማብቃት ቀላል አልነበረም ብለዋል። “የሰው ልጅ ሕይወት” ከተሰኘው ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ ሐዋርያዊ መልዕክት አስቀድሞ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ ተፈጥሮአዊ የወሊድ ቁጥጥርን በማስመልከት ያስተላለፉት ትምህርት ያለ ቢሆንም፣ ትምህርታቸው ክርስቲያናዊ ቤተ ሰብን ብቻ ያማከለ ነበር። ይህ ማለት ደግሞ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሰነድ ውስጥ ሌሎች የሚቀሩ ነገር ግን መካተት የሚገባቸው በርካት ጉዳዮች እንዳሉ መገንዘብ ያስፈልጋል። በሌላ ወገን፣ የሰውን ልጅ ሕይወት አስመልክቶ ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በፊት ይፋ የሆነ ጥናታዊ ጽሕፍ ቢኖር ኖሮ ላያከራክር ይችል ነበር ብለዋል ክብር አባ ጂልፍሬዶ ማረንጎ።

በ1959 ዓ. ም. በተካሄደው የመጀመሪያው የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ወቅት በታተመው የሐዋርያዊ መልዕክት ረቂቅ ውስጥ ስለ መወለድ መመሪያን የሚሰጡ ሁለት አዳዳስ ረቂቀ ሃሳቦችን ለማግኘት እንደተቻለ አባ ማረንጎ ገልጸዋል።

ክቡር አባ ጂልፍሬዶ ማረንጎ፣ “የሰው ልጅ ሕይወት” በተሰኘው በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ ሐዋርያዊ መልዕክት ላይ በማትኮር ካደረጉት ጥናት ለመገንዘብ የቻሉትን ነጥብ ሲያስረዱ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ ሐዋርያዊ መልዕክታቸውን የጻፉት ብቻቸውን ሳይሆን፣ ይፋ ከማድረጋቸውም አስቀድመው በርካታ ጠቢባንን እንዳማከሩ፣ አስተያየታቸውን እንደተቀበሉ፣ ብጹአን ጳጳሳትን እንዳሳተፏቸው በግልጽ መረዳት ይቻላል ብለዋል። አስቀድሞ ግልጽ የሆነ ሐሳብ ስለነበራቸው፣ ሃሳባቸውም ከጊዜ ወደ ጊዜ የተጠናከረ በመሆኑ በሐዋርያዊ መልዕክታቸው ምንም ዓይነት ጥርጣሬ እንዳልነበራቸው ገልጸው፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ  ሐዋርያዊ መልዕክታቸውን በሚያዘጋጁበት ወቅት የሐዋርያዊ ሥራ ተባባሪዎቻቸው እገዛን በመጠየቅ እና በማማከር እንደነበር ክቡር አባ ጂልፍሬዶ ማረንጎ ተናግረዋል።       

13 July 2018, 14:11