ብጹዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ መንግሥተአብ ለሰላም የአንድ ወር የጸሎት ጊዜ አወጁ ብጹዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ መንግሥተአብ ለሰላም የአንድ ወር የጸሎት ጊዜ አወጁ 

ብጹዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ መንግሥተአብ ለሰላም የአንድ ወር የጸሎት ጊዜ አወጁ

የሰባዊ ሕይወት ክብር ሰላምን ይሻል።

ብጹዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ መንግሥተአብ ለሰላም የአንድ ወር የጸሎት ጊዜ አወጁ

በቅርቡ በኢትዮጲያ እና በኤርትራ መንግሥታት መከካል የነበረው ፍጥጫ ተወግዶ በሁለቱም ሀገራት መካከል የሰላም አየር መንፈስ ከጀመረ እነሆ በርካታ ቀናት ተቆጥረዋል። በሁለቱም ሀገራት የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በሁሉቱ እህት ሀገራት ውስጥ ሰላም ይሰፍን ዘንድ በተደጋጋሚ ሲማጸኑ እና ጸሎት ሲያደርጉ እንደ ቆዩ ይታወሳል። እነሆ የሰላም አለቃ በሆነው በእግዚኣብሔር ፈቃድ፣ በምዕምናን ጸሎት እና በጎድ ፈቃድ ባላቸው ሰዎች መልካም ፈቃድ እንዲሁም በሁለቱ ሀገራት መንንግሥታት በጎ ፈቃድ በአሁኑ ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ልዩነት እየተወገደ የሰላም ንፋስ መንፈስ ጀምሩዋል፣ ግንኙነቱ በተለያዩ በማሕበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፖሌቲካዊ ዘርፎች እየተሻሻለ መምጣቱ ይታወቃል።

በቅርቡ በኤርትራ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የአስመራ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፅዕ አቡነ መንግሥተአብ ተስፋማሪያም በኢትዮጲያ እና በኤርትራ መንግሥታት መካከል የተጀመረው ሰላማዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማሰብ በኤትራ እና በመላው ዓለም የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን እና በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ሁሉ ከሐምሌ 1 እስከ ነሐሴ 6/2010 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ወር ያህል ማለት ነው ጸሎት እንዲደረግ ማወጃቸውን ከስፍራው ለቫቲካን ሬዲዮ ከደርሰው መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

በኤርትራ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የአስመራ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፅዕ አቡነ መንግሥተአብ ተስፋማሪያም ለእዚህ ለአንድ ወር ያህል ለሚቆየው የጸሎት ዝግጅት አስተንትኖ ይሆን ዘንድ የመረጡት መልእክት የተወሰደው ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምሕርተ ክርስቶስ ከቁጥር 2304 ላይ የተወሰደውን እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኃለን።

“የሰባዊ ሕይወት ክብር ሰላምን ይሻል። ጦርነት ባለመኖሩ ወይም የባለጋርዎች ኃይል በመመጣጠኑ የተነሳ ሰላም ይረጋገጣል ማለት አይደለም። የሰዎች ጥቅም እና በሰዎች መካከል የሚካሄደው ነጻ ግንኙነት በሚገባ ካልተጥበቀ ለሰዎች ሰብዓዊ ክብር እና ለሕዝቦች ከበሬታ ካልተሰጠ እንዲሁንም በሰዎች መካከል የጋለ ወንድማማችነት ካልተመሰረተ በምድር ላይ ሰላም ሊሰፍን አይችልም። ሰላም “የሥርዓት መረጋጋትን” የፈልጋል። ሰላም “የጽድቅ ሥራና የፍቅር ውጤት ነው”። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምሕርተ ክርስቶስ 2304. ”

የሰላም መንፈስ በኤርትራ እና በኢትዮጲያ መካከል ተጠናክሮ እንድቀጥል በማሰብ በኤርትራ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የአስመራ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፅዕ አቡነ መንግሥተአብ ተስፋማሪያም ያስተላለፉትን መልእክት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰንዳተናዋል።

 

“[የተከበራችው የእግዚኣብሔር ቤተሰቦች “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን” (2ቆሮ. 13፡13)። ሁላችንም እንደምናውቀው ለረጅም ጊዜ ስንፈልገው የነበረውን የሰላም ደስታ በአሁኑ ወቅት እያስተጋባ ይገኛል። ይህም የሁላችንን ደስታ እና ማብርታት የሚይነቃቃ ነገር ነው። ከሁሉም በላይ የሁሉም ጌታ እግዚአብሔርን እና በአጠቃላይ ሰላም እንዲሰፍን የሚሰሩትን ሰዎች ሁሉ ለማመስገን እወዳለሁ። ነገር ግን ከምስጋና በመቀጠል የማያቋርጥ እና ቀጣይነት ያለው ጸሎት ያስፈልገናል። በእዚህ ዓላማ ላይ ተመስርተን እኛ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ከሐምሌ 1 እስከ ነሐሴ 6/2010 ዓ.ም ድረስ በቀጣይነት በቁምስናዎቻችን፣ በአብያተክርስቲያኖቻችን፣ በጸሎት ቤቶቻችን፣ በመንፈሳዊ ማኅበራት እና ገዳማቶቻችን ልዩ እና ከፍተኛ ጸሎት ይቀርባል። በእዚም መሰረት ቆመሳትን፣ የመንፈሳዊ ማኅበራትን እና ገድማት አለቆችን ምዕመኑ ይህንን የጸሎት ጊዜ በተገቢው ሁኔታ እንዲያካሂድ አስፈላጊውን ሁሉ እንድታደጉ እንጠይቃለን። ይህ የጸሎት ጊዜ ከተጠናቀቀ ከጢቂት ቀናት በኃላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ወደ ሰማይ በሥጋ እና በነብስ ያረገችበት የፍልሰታ ማሪያም አመታዊ ክብረ በዓል ስለሚከበር ጸሎታችንን ቀጣይነት እንዲኖረው ያደርገዋል። ሰላምን ለማረጋገጥ የታማኝነት፣ የፍትህ፣ የይቅርታ፣ ከሁኔታዎች ጋር ተጣጥሞ የሚሄድ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ የእውነተኛ እና ትክክለኛ የእርቅ እና ምህረት መንፈስ ማዳበር አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ይህ ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው ጥረታችን በእግዚአብሔር ላይ መሰረቱን ስያደርግ ብቻ ነው። ስለዚህ አሁን የጀመረነው የሰላም ጉዞ ውጤታማ፣ ፍሬያማ እና ከሁሉም በላይ ትክክለኛ እና ለሕዝቦቻችን መልካም የሆነ ነገር ነው። ከጸሎት እና ከጸሎት በተጨማሪ በተለይም ቅዳሜ እና እሁድ በፍትህ፣ በሰላም እና በዕርቅ ጭብጥ ዙሪያ ላይ ማሰላሰል አስፈላጊ መሆኑን እንመክራለን። ይህን ሁሉ የምናደርገው በእግዚአብሔርን ቃል እና በቤተክርስቲያን ሰነዶችን ላይ ተመርኩዘን ነው። በእዚህ በዕየለቱ በምናደርገው የጸሎት በመቀተል በሚካሄደው መስዋዕተ ቅዳሴ ማብቂያ ላይ “የሰላም ንጉሥ የሆንከው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሰላምህን ስጠን” በማለት ጸሎታችንን እንደመድማለን ወይም ደግም ከእዚህ ጋር ተመሳሳይ በሆነው መልኩ “የሰላም ንግሥት ሆይ ለምኝልን” በሚለው ጸሎት እንደመድማለን። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና” (ማቴ 5፡9) ብሎ በማወጁ የተነሳ እኛም አስተማማኝ እና እውነተኛ የሰላም መሳሪያዎች እንድንሆን ይርዳን። እግዚአብሔር በቅርቡ ለእኛ እውነተኛ፣ ዘላቂ እና ገንቢ ሰላም ይሰጠን። ለሁላችሁም እጅግ በጣም የተትረፈረፈ የእግዚአብሔር በረከት እመኝላችኃለሁ።”

በኤርትራ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን

የአስመራ ሊቀ ጳጳስ

ብፅዕ አቡነ መንግሥተአብ ተስፋማሪያም

 

13 July 2018, 15:26