የመንፈስ ቅዱስ ታድሶ ንቅናቄ አምሳኛ አመት የምስረታ በዓል ተከበረ የመንፈስ ቅዱስ ታድሶ ንቅናቄ አምሳኛ አመት የምስረታ በዓል ተከበረ 

የመንፈስ ቅዱስ ታድሶ ንቅናቄ አምሳኛ አመት የምስረታ በዓል ተከበረ

በመጀመሪያው ዘመን የኖሩ ንዑሰ ክርስቲያን ምስጢረ ጥምቀት ከመቀበላቸው በፊት ለመጠመቅ የነበራቸውን ከፍተኛ ጉጉት እና ምኞት በማስታወስ ያንን መነፍስ አሁንም በዛሬው ዘመን በሚገኙ ንዑሰ ክርስቲያኖች ዘንድ ተፋፍሞ እንዲቀጥል ለማድረግ በማሰብ የዛሬ አምሳ አመት ገደማ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ አንድ እንቅስቃሴ ይጀመራል።

 

የመንፈስ ቅዱስ ታድሶ ንቅናቄ አምሳኛ አመት የምስረታ በዓል ተከበረ

በመጀመሪያው ዘመን የኖሩ ንዑሰ ክርስቲያን ምስጢረ ጥምቀት ከመቀበላቸው በፊት ለመጠመቅ የነበራቸውን ከፍተኛ ጉጉት እና ምኞት በማስታወስ ያንን መነፍስ አሁንም በዛሬው ዘመን በሚገኙ ንዑሰ ክርስቲያኖች ዘንድ ተፋፍሞ እንዲቀጥል ለማድረግ በማሰብ የዛሬ አምሳ አመት ገደማ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ አንድ እንቅስቃሴ ይጀመራል።

ይህ በመንፈስ ቅዱስ ታድሶ የተአኘው ንቅናቄ በዓለማቀፍ ደረጃ በላፈው ቅዳሜ በሚያዝያ 27/2010 ዓ.ም. በሮም ከተማ አቅራቢያ ማክበራቸው የተገለጽ ሲሆን በወቅቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ የማኅበሩ አባላት ተግኝተው ይህንን አምሳኛውን ዓመት የምስረታ በዓል ባከበሩበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በስፍራው ተገኝተው ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት በእናንተ ምድበለ ዘር ውስጥ የተልዕኮ ጥሪ ይገኛል ማለታቸው ታውቁዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በወቅቱ ያደርጉትን ንግግር ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተጉመናዋል አብራችሁን በመሆን እንድተከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ኣና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ

እናንተን በእዚህ ስፍራ ስላገኘኃችሁ እኛ ከእናንተ ጋር በመሆኔ ባጣም ደስተኛ ነኝ! በቅድሚያ ለእግዚኣብሔር ምስጋና ይደርሰው እና ከእናንተም መካከል አንዳንዶቹ በጣም ብዙ ርቀት ተጉዘው እዚህ ደርስ በመምጣችሁ ላማስግናችሁ እወዳለሁ። ቅዱስ ወንጌልን ለመስበክ እና ቅዱስ ወንጌልን በሕይወታችሁ ለመኖር ጌታን ላቀረበላችሁ ጥሪ “አዎንታዊ” ምላሽ በመስጠታችሁ ለማስግናችሁ እወዳለሁ። ይህንን ታልቅ የመነፍስ ቅዱስ ታድሶ ንቅናቄ የዛሬ አምሳ ዓመት ገደማ ለጀመሩም ሰዎች ታልቅ የሆነ ክብር ነው።

አምሳ የሚለው ቁጥር በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ በጣም ወሳኝ የሆነ ቁጥር ነው፣ ለሙታን የተነሳው ጌታ መነፈስ ቅዱስ ከአምሳ ቀናት በኃላ ለሐዋሪያት  እና ለዓለም  የተገለጸብትን ቀን ያስታወሳል።  “የአምሳኛው ዓመት ኢዮቤልዩ ይሁንላችሁ” (ዘሌዋውያን 25:11) ይህ አምሳኛው ቀን በእግዚኣብሔር የተባረከ ቀን ነው። “አምሳኛውን ዓመት ቀድሱ፤ በምድሪቱ ሁሉ ላሉ ነዋሪዎች በሙሉ ነጻነት ዐውጁ፤ ይህም ኢዮቤልዩ ይሁንላችሁ፤ ከእናንተ እያንዳንዱ ወደ ቤተ ሰቡ ርስት፣ ወደ ወገኑም ይመለስ” በማለት ይህ ዓመት የተቀደሰ አመት እንደ ሆነ በመግለጽ  የተመረጡት የእግዚኣብሔር ሰዎች ከጭቆናና የላቀው ተመልሰው ወደ ቤታቸው የኤኡበትን ቀድን የሚያስታውስ አዳዲስ እውነታዎች የታዩበት ቅዱስ አመት ነው። አዎን ከእዚህ የአምሳ አመት ጉዞ ብኃላ እያንዳንዳችሁ ራሳችሁን “ጌታ ሆይ ነጻ ስላወጣህኝ አመስግንሃለሁ፣ ምክንያቱም በቤተክርስቲያን ውስጥ የራሴን ቤተሰብ ስላገኘሁኝ ነው፣ ምክንያቱም በአንተ ምስጢረ ጥምቀት አማክይነት ያለፈ አሮጌ ማንነቴ አልፉል አንዲ ሕይወት አግንኝቻለሁና” በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን ፍቅርህን ለማወቅ የምችልበትን መንገድ ስላሳየህኝ አመስግናለሁ ልትሉት የገባል።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ኣና እህቶቼ፣ በኣዚህ ዝግጅት ማብቂያ ላይ “እግዚኣብሔር ስላሳየን ፍቅር እና ታማኝነት የመስጋና መዝሙር ትዘምራላችሁ። ይህ ነገር በጣም ውብ የሆነ ነገር ነው። እግዚኣብሔር ስላሳየን ፍቅር እና ታማኝነት እርሱን ማመስገን መልካም ነገር ነው። በዙን ጊዜ እግዚኣብሔር ስላደርገልን ነገሮች፣ ስለሰጠን ስጦታ ጭምር እናመስግነዋለን፣ ይህንንም ማድረግ ተገቢ እና መላክም ነገር ነው። ስላሉን ነገሮች በሙሉ ሳይቀር እግዚኣብሔርን ማመስገን ተገቢ ነው ምክንያቱም እግዚኣብሔር በፍቅሩ አመክይነት ታማኝ ስለሆነ ነው። የ?እግዚኣብሔር መልካምነት በእኛ መልክም መሆን የሚወሰን ነገር አይደለም። ምንም ዓይነት ነገር ብንፈጽም እናኳን እግዚኣብሔር በታማኝነት እኛን መውደዱን ያቀጥላል። ይህ የመተማመን ምንጭ፣ የህይወት ማጽናኛ ምንጭ ጭምር ነው። ስለእዚህ በርቱ በፍጹም አትደናገጡ! ብዙ ችግሮች ልክ እንደ ደመና እየከበዱ ሲመጡ የእግዚአብሔር ታማኝ ፍቅር ሁልጊዜ ቢሆን እንደ ፀሐይ እንደማይለያችሁ አስታውሱ። በችግሮች ሁሉ ውስጥ እርሱ ያደርገላችሁን መልካም ነገሮች በማስታወስ፣ የእርሱን ታፋጭ ፍቅር የቀመሳችሁበትን እለት በማስታወስ እግዚኣብሔር በማንኛውም ዓይነት መከራዎች ውስጥ እንደ ሚረዳችሁ አስታውሱ።

ከእናንተ መካከል አንዳንዶቻችሁ ለተልዕኮ በመዘጋጀታቸው የተነሳ እግዚኣብሔን እናመስገናለን። የወንጌል ተልዕኮው በተመለከተ አንድ ነገር ከልቤ ልንግራችሁ እወዳለሁ፣ ይህም ዛሬ ቤተክርስቲያን ቅድሚያ የሚትሰጠው ጉዳይ ነው። ተልእኮ ለእግዚአብሔር ታማኝ ፍቅር ድምጽ መስጠት ስለሆነ፣ ጌታ የእኛን፣ የአንተን፣ የኤን ለዓለማችን ሳይቀር መላክ እንደ ሚመኝ፣ እኛ  በምንደክምበት ወቅት እንኰና ስይቀር ጌታ ከእኛ ግራ ሆኖ ኣንደ ሚያበረታታን በማመን መጓዝ ያስፈልጋል። የቅዱስ ወንጌል ተልዕኮን መፈጸም ማለት የተሰጠንን ነገር ለሌሎች መስተት ማለት ነው። የወንጌል ተልዕኮ ማድረግ ማለት ኢየሱስ የሰጠንን ተልዕኮ ገቢራዊ ማድረግ ማለት ነው “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ሕዝቦችን በሙሉ የእኔ ደቀ-መዛሙርት አድርጉዋቸው” (ማቴ 18፡19) የሚለውን መፈጸ ማለት ነው።

ሂዱ። አንድ ተልዕኮ መሄድን ወይም መጉዛን ይጠይቃል።  ነገር ግን በሕይወት ውስጥ ትልቁ ፈተነ የሚሆነው ባለንበት ቦታ ለመቆየት መፈለጋችን ሲሆን፣ ይህም ምንም ዓይነት አደጋ ውስጥ ለለመግባት በመስበ ኣና ሁሉንም ነገር በቁጥጥራችን ሥር በማድረግ የሚሰጠን ደስታ ለመቁደስ በመፈለግ ነው። በጣም የሚያስደስተን ነገር የሚሆነው በቤታችን ለእኛ በጎ ነገር ከሚመኙልን ስዎች ተከበን መኖር የሚያስደስተን ሲሆን  በኢየሱስ መነገድ ላይ በመጓዝ ራሳችንን ለአደጋ ማጋለጥ አንፈልግም። ነገር ግን እርሱ ማለትም ኢየሱስ “ሂዱ” በማለት ይልከናል። “ሂዱ” ይህ ሂዱ የሚለው ቃል በክርስቲያኖች ልብ ውስጥ የሚያስተጋብ ወሳኝ የሆነ የጥሪ ቃል ነው። ይህ የጥሪ ቃል በጣም ግልጽ የሆአነ እና ሁልጊዜ በጉዞ ላይ እንድንሆን፣ በዓለም ውስጥ በመጓዝ እስካሁን የእግዚኣብሔርን ፍቅር የማያውቁ ወንድሞችን መፈለግ ማለት ነው።

ታዲያ እንዴት ነው መሄድ የምንችለው? ሁሉንም በቤታችን የሚገኙትን እቃዎች ተሸክመን መሄድ ማለት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱሳችን እንደ ሚያስተምረን እግዚኣብሔር የእርሱ ምርጥ ሕዝብ የነበሩትን ሰዎች ነጻ ባወጣበት ወቅት ይዘውት የሄዱት ቦርሳ ስይሆን በእርሱ በመታመን ብቻ ነበር። እርሱ ራሱ ሰው ከሆነ በኃላ እንደ ድኸ ርሱን ኣናኳን የሚያሳርፍበት ቦታ ስይኖረው በድኽነት ኖሩዋል። እኛም ይህንን የኢየሱስን አብነት እንድንከተል ይጋብዘናል። በሚገባ ለመጓዝ እንችል ዘንድ ሁልጊዜም ቢሆን ቀለል ያለ ሽክም ሊኖረን ይገባል። ወንጌል ለመመስከር የተወሰኑ ነገሮችን አውለቀን መጣል ይኖርብናል። ቤተክርስቲያን ኢየሱስን በሚገባ ለመመስከር የምትችለው ዓለምን ስትክድ ብቻ ነው። ከስልጣን ጥማት እና ከገንዘብ ፍቅር ነጻ የሆነች ቤተክርስቲያን፣ ከኩራት መነፈስ ነጻ የሆነች ቤተክርስቲያን ብቻ ናት ታማኝ በሆነ መልኩ ቅዱስ ወንጌል መስበክ የምትችለው።  በክርስትሶ ፍቅር ታግዞ የሚያልፉ የእዚህን ዓለም ነገሮች በመተው ክቡር የሆነውን የእግዚኣብሔርን ቃል ይዞ የሚጓዝ እርሱ ነጻ ሰው ነው። ከነገሮች ጋር ራሱን በማቆራኘት፣ ለግዜው መልካም የሚመስሉ ነገር ግን ሰላምን የማይሰጡ፣ ልብን በማሳበጥ ያለእግዚኣብሔር መኖር እንደ ሚቻል ከሚንግሩን ስሜቶች መላቀቅ ይኖርብናል።

“ሂዱ” የሚለው የተልዕኮ ጥሪ በተጨማሪ አንድ ነገር ያስታውሰናል፣ ይህም ብዝዕነትን የሚያመልክት መሆኑ ነው። ጌታ “አነተ ብቻ ሂድ፣ ከእዚያን በመቀጠል አንተ ደግሞ ትሄዳልህ. . .ወዘተ ስይሆን ያለን “ሂዱ” በማለት ከአንድ በልይ አድጎ ኣንደ ላከን ማስታወስ ያስፈልጋል፣ ይህም ተልዕኮ የግል ስይሆን የተላክነው በጋር መሆኑን ያስረዳል። አንድ የወንጌል ልዑክ ብቻውን መጓዝ የለበትም በጋ ከሌለኦች ጋር በመሆን እንጂ። አብሮ መጓዝ ማለት በእየለቱ ልንማረው የሚገባን ስነ-ጥበብ እንደ ሆነ ማወቅ ይኖርብናል። ለምሳሌ አንድ ከእኛ ጋር አብሮ የሚጓዘውን ሰው እርምጃው ላለማደናቀፍ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል ማለት ነው። የሌላኛው አብሮን የሚጓዘው ሰው መንገድ ከእኔ ጋር እንደማይመሳሰል በማስታወስ አብሮ መጓዝ እና መጠባበቅ አለብን። እንደምናውቀው አንድም ሰው ከሌላው ጋር አንድ አይነት ፍጥነት አይደለም፣ በእመንትም ደረጃ እንዲሁ ነው፣ ወደ ፊት አበረን መጓዝ የምንችለው ማንም ሰው ስናገል እና የእኛን የአካሄድ ዘይቤ በሌለኦች ላይ ስንጭን መሆን ይኖርበታል፣ ወደ ፊት አረን ለመጓዝ የምችለው በአንድነት እና እንደ አንድ የቤተክርስቲያን አባላት በመሆን የቤተ ክርስቲያን እረኞች ጋር፣ ከሁሉም ወንድሞች ጋር በጋራ በመሆን በጉዞዋችን ወቅት ወደ ኃላ የሚቀር ሰዎች ላይ ባለማጉረምረብ በጋር መጓዝ ይኖርብናል። ከወንድሞቻችን ግራ በጋራ በመሆን የምንጓዝ ነጋዲያን መሆን ያኖርብናል፣ የሌለኦችን እርምጃ እና አካሄድ በሚገባ በመከታተል እና በማክበር ለእያንዳንዱ ሰው እርምጃ ጥንቃቄ በማድረግ ወደ ፊት በጋር መጓዝ ይኖርብናል።

11 July 2018, 09:38