ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ የፋጢማ ማሪያም የተገለጸችበት 100ኛ አመትን በግንቦት 05/2010 ዓ.ም አከበሩ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ የፋጢማ ማሪያም የተገለጸችበት 100ኛ አመትን በግንቦት 05/2010 ዓ.ም አከበሩ  (AFP or licensors)

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ የፋጢማ ማሪያም የተገለጸችበት 100ኛ አመትን አከበሩ

ከዚያም ኢየሱስ በወንጌል ለደቀ መዝሙሩ “ይችውልህ እናትህ!” (ዩሐንስ 19፡27) አለው። እናት አለን።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ የፋጢማ ማሪያም የተገለጸችበት 100ኛ አመትን በግንቦት 05/2010 ዓ.ም አከበሩ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በፖርቹጋል ሀገር በሚገኘው ፋጢማ በሚባል ስፍራ የዛሬ አንድ መቶ አመት ገደማ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ለሦስት እረኛ ለነበሩ ሕጻናት በተገለጸችበት የመቁጠሪያዋ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተ መቅደስ ለሁለት ቀን የምቆይ መንፈሳዊ ጉዞ ለማድረግ በግንቦት 5/2009 ዓ.ም. ላይ ወደ እዚያው አቅንተው እንደ ነበረ ይታወሳል። በወቅቱ በዚሁ የመቁጠሪያዋ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተ መቅደስ ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው አስናድተነዋል፣ ተከታተሉን።  

“ከዚህ ቡኃላ ታላቅ አስደናቂ ምልክት በሰማይ ታየ፣ ፀሐይን የለበሰች አንዲት ሴት ታየች፣ እርሱዋም ነብሰጡር ነበረች” (ራእይ 12፡1)። ከዚያም ኢየሱስ በወንጌል ለደቀ መዝሙሩ “ይችውልህ እናትህ!” (ዩሐንስ 19፡27) አለው። እናት አለን። እውነት ነው የምላችሁ እናት አለን! የዛሬ መቶ አመት ማሪያምን ያዩዋት እረኞች እንደ ገለጹት “በጣም የምታምር” እናት አለን። በዛን ምሽት ዣሽንታ (እ.አ. በግንቦት 13/1917 ዓ.ም. ማሪያም ከተገለጸችላቸው ሕጻናት አንዱዋ ናት) ያየችውን ምስጢር ደብቃ መያዝ ስላልቻለች ለእናቷ “ዛሬ እመቤታችንን አየዋት” በማለት ነገረቻት። ሰማያዊቷን እናት አይተዋት ነበር። ብዙ ሰዎች ይህንን ግልጸት ለመጋራት ፈልገው ነበር፣ ነገር ግን ማሪያምን አላዩዋትም ነበር። ቅድስት ድንግል ማሪያም እዚህ የመጣችው ለመታየት ፈልጋ አይደለም። ወደ መንግሥተ ሰማይ በምንሄድበት ወቅት ለዘለዓለም እናያታለን።

የእምቤታችን ትንቢት የምያስጠነቅቀን እግዚኣብሔር የለሽ ሕይወት እንዳንኖር እና ፍጡራን እግዚኣብሔርን እናዳያረክሱት ማስጠንቀቅ ነው። ብዙን ጊዜ የዚህ ዓይነት ሕይወት ወደ ገሀነም እሳት የመምራት አደጋ አለው። ማሪያም የተገለጸችው የእግዚኣብሔር ብርሃን በውስጣችን እንዳለ ልትገልጽ እና ልትጠብቀን ልክ የመጀመሪያው ምንባብ ስነበብ እንደ ሰማነው “ልጇ ግን ወደ እግዚኣብሔር እና ወደ ዙፋኑ ተወሰደ” (ራእይ 12፡5) የሚለውን ለማስረዳት ነው። ከሉቺያ (እ.አ. በግንቦት 13/1917 ዓ.ም. ማሪያም ከተገለጸችላቸው ሕጻናት አንዱዋ ናት) ታሪክ መረዳት እንደተቻለው እነዚህ ሦስቱ ሕጻናት ከእመቤታችን ቅድስት ድንግላ ማሪያም በመነጨው የእግዚኣብሔር ብርሃን ተከበው እንደ ነበረ ያትታል። እግዚኣብሔር በሰጣት ብርሃን ጋርዳቸው ነበር። ሁሉም ባይሆኑም እንደ ብዙኅኑ መንፈሳዊ ተጓዥ ምዕመናን ተመኩሮ እና ልምድ የፋጢማዋ ማሪያም ከዚህም በበለጠ ሁኔታ በልብሶቹዋ እንደምትጋርደን ያስተምሩናል። በማሪያም ጥበቃ ሥር ራሳችንን በማድረግ ቅድስት ድንግል ማሪያም ሆይ ኢየሱስን መመልከት እንድንችል አስተምሪን ብለን ልንጠይቃት ይገባል።

ውድ መንፈሳዊ ተጓዥ ምዕመናን እናት አለን። እንደ ሕጻን ልጅ በእርሷ ላይ ዘንበል በምንልባቸው ወቅቶች ሁሉ በኢየሱስ ላይ መሰረቱን ባደረገ ተስፋ እንሞላለን። በሁለተኛነት ሲነበብ የሰማነው ምንባብ “በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የእግዚኣብሔርን ብዙ ፀጋ ተቀብለው የጸደቁ ሁሉ በድል አድራጊነት ሕይወት ይኖራሉ” (ሮም 5፡17) ይለናል። ኢየሱስ ወደ ሰማይ ባረገበት ወቅት ከቅድስት ድንግል ማሪያም የነሳውን ሰባዊነታችንን ወደ ሰማያዊው እግዚኣብሔር ወሰደ። እስቲ እንደ አንድ ተዋኒያን ራሳችንን በመቁጠር በእግዚኣብሔር አብ ቀኝ እንደ ተቀመጥን አድርገን ተስፋ እናድርግ። ይህ ተስፋችን ሕይወታችንን ይምራው! ይህም ተስፋ ነው ሁልጊዜም እየማራን የሚገኘው።

እዚህ የተሰበሰብነው በዚህ ተስፋ በመሞላት በባለፉት መቶ አመታት ውስጥ ልዩ ልዩ ጸጋዎችን የሰጠንን እግዚኣብሔ ለማመስገን ነው። ሁሉም ሰዎች ከማሪያም መጎናጸፊያ በሚመነጨው ብርሃን ሥር በማለፍ ወደ አራቱም የዓለም መዕዘናት አስረጭተዋል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ተገልጻላቸው የእግዚኣብሔርን ጥልቅ የሆነ ብርሃን እና እርሱን እንድያመልኩ በልግጸቱ ወቅት ያስተማረቻቸውን የቅዱስ ፍራንቸስኮን እና የቅድስት ዣሽንታን አብነት በመከተል ይኖርብናል። ዘወትር ለኃጢያተኞች በሚያደርጉት ጸሎት እና በመንበረ ታቦት ውስጥ በስውር የሚገኘውን ኢየሱስን ለመቀበል በሚያሳዩት ፍላጎት ምክንያት እግዚኣብሔር በቋሚነት በሕይወታቸው ውስጥ ነበረ።

በእርግጥ እግዚኣብሔር የፈጠረን ለሌሎች የተስፋ ምንጭ እንድንሆን ነው። ሁላችንም የተሰጡንን ኃላፊነቶች ትክክለኛ በሆነ መንገድ እንድንወጣ ይጠይቀናል ያሳስበናልም። በማሪያም ጠባቂነት ትክክለኛው የሆነውንና በፋሲካ የበራውን የአዳኛችን የኢየሱስን የፊት ገጽታ በማሰላሰል ለዓለማችን ዘብ መቆም ይኖርብናል። በዚህም መልኩ ሚስዮናዊ በምትሆንበት ጊዜያት ሁሉ የሚበራውን፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ነጻ፣ ድኽ ነገር ግን በፍቅር የበለጸገች ወጣት እና ውብ የሆነውን የቤተ ክርስቲያን ፊትን በድጋሚ እንድንመለከት ትርዳን ።

በወቅቱ እረኞች ለነበሩ ሦስት ሕፃናት እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር የዛሬ 100 ዓመት ገደማ በግንቦት 13/1917 ዓ.ም. በፖርቱጋል በሚገኘው ፋጢማ በሚባለው አከባቢ ልዩ ስሙ ኮቫ ዳ ኢራ በተባለው ሥፍራ ለሶስት ታዳጊ የከብት ጠባቂ እረኞች ለነበሩ ሕፃናት ፍራሲሽኮ፣ ዣሺንታ ማርቶ እና ሉሲያ ለተባሉ ሦስት ታዳጊ ለነበሩ ልጆች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያ የተገለጸችላቸው መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ፒዮስ ሰባተኛ እንደ የአውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በግንቦት 13/1946 ዓ.ም. የእዚህን ግልጸት ትክክለኛነት ከመረመሩ ቡኃላ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ሥም የንግደት ሥፍራ ይሆን ዘንድ ቤተ መቅደስ እንዲሠራ ፈቃድ መስጠታቸውና እስከ ዛሬም ድረስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመናን በሥፍራው ንግደት በማድረግ እንደ ሚገኙም ይታወቃል።

ይህንን ግልጸት ከተቀበሉት ሦስቱ እረኛ ሕጻናት ውስጥ ሁለቱ ፍራንቸስኮ እና ዣሽንታ ማርቶ የተባሉት ሁለት ታዳጊ እረኞች ለነበሩ ሕፃናት  በግንቦት 5/2009 ዓ.ም. እንደ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅድስና ማዕረግ የተሰጣቸው መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ሦስተኛው እና በገዳም ሕይወት የኖሩ እና እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 2005 ከእዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሲስተር ሉሲያ የሕይወት ታሪካቸው በመጠናት ላይ እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል።

በወቅቱ ፖርቹጋል እና የተቀረው ዓለም በጦርነት ውስጥ በነበሩበት ወቅት የመቁጠሪያዋ እናታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ለእነዚህ ሦስት እረኛ ሕጻናት በመገለጸ ሁሉም የዓለም ሕዝቦች ንስሐን በመግባት እና የመቁጠርያን ጸሎት አዘውትረው በመጸለይ ለዓለም ሰላም እንዲመጣ መጣር እንዳለባቸው ቅድስት ድንግል ማሪያም ባሳሰበችሁ መሰረት ዛሬም ቢሆን በሚልዮን የሚቆጠሩ ነጋዲያን በፖርቹጋል ሀገር ፋጢማ በሚባለው ስፍራ በመገኘት ሰላም በግለሰብ ደረጃ እና ብሎም በመላው ዓለም ሰላም ይወርድ  ዘንድ በእናታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነት ጸሎታቸውን ወደ እግዚኣብሔር እያሳረጉ ይገኛሉ።

ከእነዚህም ነጋዲያን መካከል በግናባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት እና ብዙን ጊዜ ወደ ፋጢማ ንግደት በማድረግ የሚታወቁት ቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ይገኙበታል። ቅዱስ የሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩበት ወቅት ለሳምንታዊው የጠቅላላ አስተምህሮ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተገኙበት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በሚዘዋወሩበት ወቅት መሐመድ አሊ በተባለ ቱርካዊ እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በግንቦት 13/1981 ዓ.ም. አራት ጊዜ በጥይት ተመተው የወደቁበት ቀነ፣ የመቁጠሪያዋ ማሪያም ለእነዚህ ሦስት ሕጻናት እረኞች ከተገለጠችበት ቀን ጋር በመገጣጠሙ ከእዚህ ክፉ አደጋ ከሞት የተረፍኩት በፋጢማዋ ቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነት ነው ብለው አምነው እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ ከፍተኛ የሆነ አክብሮት እና ፍቅር ለቅድስት ድንግላ ማሪያም በማሳየት ይህንንም እምነታቸውን የመቁጠሪያን ጸሎት አዘውትረው በመጸልይ ተግብረውታል።

እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በግንቦት 13/2000 ዓ.ም ቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ለመጨረሻ ጊዜ ቅድስት እናታችን ማሪያም የተገለጠችበትን የፋጢማን ቅዱስ የንግደት ስፍራ መጎብኘታቸው እና እናታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በሕይወታቸው ላደረገችላቸው ጥበቃ እና አማላጅነት ምስጋናን አቅርበው እንደ ነበር ይታወቃል። በእዚህ የመጨርሻ ጉብኚታቸው ወቅት እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በግንቦት 13/1917 ዓ.ም ቅድስት ድንግል ማሪያም ከተገለጸችላቸው ሦስት ሕጻናት እረኞች መካከል ብቸኛዋ በሕይወት የነበረችሁ ሉቺያ በእለቱ እንደ ነበርች እና ከእዚያም ከጥቂት ዓመታት በኋላ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2005 ዓ.ም ከእዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የሚታወቅ ሲሆን ሕይወታቸው ታላቅ ምስክርነትን ጥሎ ያለፈ ወቅት እንደነበር ይታወሳል።

 

 

 

13 May 2018, 11:40